ፖለቲካዊ ውክልና የዲሞክራሲ ሁነኛ አካል ነው። የፓርላማ ውሳኔ ላይ የመድረስ ሂደት ውስጥ ሁሉም ድምፆች የመስተጋባታቸው ማረጋገጫ ነውና።
ይሁንና፤ አውስትራሊያ ገና እዚያ ደረጃ ላይ አልደረሰችም።
በፍሊንደርስ ዩኒቨርሲቲ የሥነ መንግሥት መምህር የሆኑት ዶ/ር ኢንቲፋር ቾውድሪ፤ የሕዝቡን ገፅታ የሚያንፀባርቅ ፓርላማ ማኅበራዊ ውሁድነትን ለማሻሻል ወሳኝ እንደሆነ ሲናገሩ፤
“የፖለቲካ ፓርቲ ዝንቅ ዝርያ ያላቸውን ሰዎች አስተማማኝ ወደ ሆነም ሆነ ወደ አልሆነ የምክር ቤት ወንበር አሳላፊ ቁልፍ ያዥነት ተግባራት ያሉት ነው” ብለዋል።
SBS Examines በእዚህ ክፍለ ዝግጅት የፖለቲካ ሥርዓቱ እውነተኛ የሕብረተሰቡ መስተዋት መሆንን የማስቻል አንዳች ተስፋ ያለው እንደሁ ይመለከታል።