በወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የምንሟገተው ስለምን ነው?

Untitled design (3).png

The federal government spent almost half a million dollars on Welcomes to Country across two years according to an FOI released earlier this year. Credit: Supplied/AAP Photos

መንግሥት ለወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የሚያወጣው ወጪ በብርቱ ተትችቷል፤ በተወሰኑቱ ዘንድም ባሕላዊው ፕሮቶኮል ለ"ፖለቲካ እግር ኳስነት" መጠቀሚያ ሆኗል የሚል አመኔታንም አሳድሯል።


የተቃዋሚ ቡድኑ ባቀረበው የመረጃ ነፃነት ጥያቄ መሠረት በሁለት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ $450,000 ያህል በ21 የፌዴራል መንግሥት ዲፓርትመንቶች ወጪ ሆኗል።

ወጪውን አስመልክቶ የሰሉ ትችቶችን ከሰነዘሩት ውስጥ አንደኛዋ የተቃዋሚ ቡድኑ የነባር ዜጎችና የመንግሥት ብቃት ቃል አቀባይዋ ጃሲንታ ናምፒጂንፓ ፕራይስ ናቸው።

"ግማሽ ሚሊየን ዶላርስ ያህል ለወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ እና የጭስ ማጠን ሥነ ሥርዓቶች በመንግሥት ዲፓርትመንቶች ወጪ መደረግ የግብር ከፋዩን ገንዘብ በአግባቡ መጠቀም ማለት አይደለም፤ ለተገለሉ አውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ይህ ነው የሚባል ረብ የለውም" ሲሉ ለ SBS Examines ተናግረዋል።

ሴናተሯ፤ ቅንጅቱ በምርጫ ቃሉ "ውጤት የማያበረከት የመንግሥት ብኩንነትን እንደሚከላ" እንዲሁም "የአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ሕይወት ለማሻሻል የተመጠነ ግብርን ለመተግበር ወደ ኋላ አይልም" ይህንንም በተመለከተ "ያለማቋረጥ ግልፅ አድርጓል"

"የመንግሥት የገንዘብ ወጪ ለከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ቀውስ አስተዋፅዖ አበርክቷል፤ አውስትራሊያውያን ገንዘባቸውን ኃላፊነትና ብቃት በተመላው ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚያውል የአውስትራሊያ መንግሥትን ይመጥናሉ" ብለዋል።

በ "ርዕዮተ ዓለማዊ አተያይና ማስመያነት" መንግሥት "ለብዥታ ተዳርጓል" ሲሉም አክለው ተችተዋል።

በመንግሥት ወገን የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስትር ማላርንዲሪ ማክካርቲ በበኩላቸው የሴናተሯን አተያይ አሌ ሲሉ፤

"የአልበኒዚ መንግሥት ትኩረቱ ነባር ዜጎች በሆኑና ባልሆኑ አውስትራሊያውያን መካከል ያለውን ክፍተት ነባር ዜጎችን በምጣኔ ሃብት ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ በማስቻል ማጥበብ ላይ ሲሆን፤ በተቃዋሚው በኩል ተተኩሮ ያለው ወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የባሕል ጦርነቶች ላይ ነው።"

"ፒተር ዳተንና ቅንጅቱ የባህል ጦርነት የሊብራል ዕዳን ከፋይ ሊሆን ይችላል ብለው ካሰቡ ግና፤ አቅላቸውን ስተዋል ማለት ነው" ብለዋል።
ተመራማሪና ደራሲ ፕሮፌሰር ማርሽያ ላንግተን በወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ ዙሪያ የሚካሔደው ክርክር "አስቀያሚ የባሕል ጦርነቶችን" መቀስቀሻ ነው ብለው ያምናሉ።

"ይህ ልክ ቅሌት እንደሆነ ተደርጎ ሪፖርት የሚደረገው ስለምን እንደሁ አይገባኝም . . . . . ይህን አስመልክቶ ከአመላካች ፍንጭነት በላይ የሆነ የዘረኝነት ጉዳይ አለ። ለአውስትራሊያውያን ወደ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ጦር ኮሮች ቀን መሔድ መልካም ነገር ሲሆን ወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ ኩነቶች መሔድ ግና መልካም ተደርጎ አይወሰድም"

"ግልፅ ለመሆን፤ ይህን ሆኖ ያገኘሁት የመረጃ ነፃነቱን መረጃ የቅሌት ግርግር ሆኖ ነው . . . አስቀያሚ የባሕል ጦርነቶችን ጭምብል ለመግለጥ የተደረገ አታሞ ድለቃ ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል የነባር ዜጎች ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር አንቶኒ ዲለን እንኳን ወደ ሀገር መጡ "የፖለቲካ እግር ኳስ" መጠቀሚያ ሆኗል ይላሉ።

"የተወሰኑ ፖለቲከኞች የሆነ ነገር በመምዘዝ ብርቱ ጉዳይ ያስመስሉታል፤ በፖለቲካ እግር ኳስ መንፈስ . . . በነባር ዜጎች ጉዳይ ለተሰላቹ ሰዎች ይህ ወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ ቀላሉ ነገር ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ይዘት ጭንቀት ካሳደረብዎ፤ እባክዎን ወደ ብሔራዊ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ቀጥተኛ የቀውስ መስመር 13YARN ወይም 13 92 76 ይደውሉ።
LISTEN TO
Rumours, Racism and the Referendum image

Rumours, Racism and the Referendum

SBS English

14/10/202407:08

Share