ለሀገር አቀፉ ምርጫ ድምፅዎን እንደምን መስጠት እንደሚችሉ

Un uomo inserisce una scheda elettorale in un'urna.

Un uomo inserisce una scheda elettorale in un'urna. Source: iStockphoto / Sadeugra/Getty Images/iStockphoto

የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን በምርጫ ዕለት በሰዓት አንድ ሚሊየን መራጮች በምርጫ ማዕከላት ውስጥ እንደሚያልፉ ግምት አለው። ምርጫ ከግዴታ ጋር ተያያዥነት ስላለው ማናቸውም አውስትራሊያውያን ከምርጫው ቀን በፊት ስለ ምርጫ ሂደቱ በቂ ግንዛቤ መጨበጥ አለባቸው።


Key Points
  • የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን የእርስዎን የምርጫ ቀጠናና የምርጫ ጣቢያ ለመፈለግ የሚያስችልዎ አጋዥ መንገዶችን በማመላከት ይረዳዎታል
  • በምርጫው ዕለትና ከምርጫው ቀን በፊት የተለያዩ የድምፅ አሰጣጥ አማራጮች አሉ
  • የድምፅ አሰጣጥ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል
  • የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን መምረጥ እንዲቻልዎት የስልክ አስተርጓሚ ያቀርብልዎታል
አውስትራሊያ የምርጫ ሥርዓትን በገለልተኝነት የሚያስተዳድር አካል አላት። ማናቸውም መመዘኛውን የሚያሟሉ ዜጎች ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉና የፌዴራል መንግሥታችንን ቀርፆ ለማቆም እገዛ እንዲያደርጉ የማድረጉ ሚና የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን (አምኮ) ነው።  

የምርጫ ቀጠናዎን ይለዩ  

አውስትራያ ውስጥ 150 የፌዴራል ምርጫ ቀጠናዎች አሉ። የትኛው የምርጫ ቀጠና ውስጥ እንደሚኖሩ መለየት እንዲያስችልዎ አምኮ የኦንላይን እገዛ ያደርግልዎታል። የምርጫ ቀጠናዎን ፈልገው ለማግኘት የአምኮን ድረገፅ ይጎብኙ።

እንዲሁም 13 23 26 መደወል ወይም ማግኘት ይችላሉ።

የምርጫ ጣቢያዎን ፈልገው ያግኙ 

አምኮ በሺህዎች የሚቆጠሩ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ይመራል። በምርጫ ዕለት፤ የአካባቢ ትምህርት ቤቶች፣ የማኅበረሰብ ማዕከላትና ቤተ ክርስቲያናት በምርጫ ጣቢያነት ያገለግላሉ።

የአምኮ ቃል አቀባይ ጄስ ሊሊ “አንዱን በአቅራቢያዎ ያለን የምርጫ ጣቢያ ፈልጎ ማግኘት በእጅጉ ቀላል ነው”

“የእኛ መፈለጊያ ውስጥ ክፍለ ከተማዎንና የፖስታ ቁጥሩን በመፃፍ ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑና የት ሔደው መምረጥ እንደሚችሉ ፈልገው እንዲያገኙ እንረዳዎታልን” ይላሉ።

ድምፅ ለመስጠት ቀላሉ መንገድ ሁሌም ቅዳሜ ላይ የሚውለው የምርጫው ዕለት ወደ አካባቢዎ የምርጫ ጣቢያ ሔዶ መምረጡ ነው። 

ተዘዋዋሪ ቡድኖችም በመጠወሪያ ሥፍራዎች፣ ርቀው በሚኖሩ ማኅበረሰባት ዘንድ፣ ሆስፒታሎችና እሥር ቤቶች ይገኛሉ።
PRAHRAN WERRIBEE BY-ELECTIONS COLOUR
Election corflute signs are seen at the polling booth for the Werribee by-elections at Werribee in Melbourne. Source: AAP / DIEGO FEDELE/AAPIMAGE

በቋንቋዎ ይምረጡ

የምርጫ ጣቢያዎችና የአምኮ ድረገፅ በ   መምሪዎችን ያቀርባሉ።

እርዳታ የሚሹ ከሆነ ከአንድ ተጨማሪ ሰው ጋር አብረው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም፤ በቋንቋዎ መምረጥ እንዲችሉ ማግኘት ይችላሉ።  

ሌሎች ድምፅ የመስጫ መንገዶች 

ከምርጫ ቀን በፊት የቅድሚያ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ክፍት ይሆናሉ።   

በአማራጭነትም፤ በኦንላይን ወይም ወደ አውስራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ቢሮዎች በመሔድ መጠየቅ ይችላሉ። 

የክፍለ አገራት ወይም ባሕር ማዶ ድምፅ አሰጣጥ 

ወደ ክፍለ አገር መሔድ ካለብዎት ያ ችግር አይሆንም። የፖስታ ድምፅ መስጫን መጠቀም ወይም ከአንዱ የክፍለ አገሩ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅዎን መስጠት ይችላሉ።   

ሌላው ቀርቶ ባሕር ማዶ ሆነው እንኳ መምረጥ ይችላሉ። ከእርስዎ ሁኔታ ጋር ተስማሚ ሊሆኑ ከሚችሉ አማራጮች ጋር ከአምኮ ድረገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ። የተወሰኑ የአውስትራሊያ ኤምባሲዎች የምርጫ ጣቢያዎች ይኖራቸዋል።  
Australia Goes To The Polls
A dog stands as voters cast their ballots at a polling station during a federal election in Sydney, Australia, on Saturday, May 18, 2019. Credit: Bloomberg/Bloomberg via Getty Images

የመረጃ ስርጭት 

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች በምርጫ ጣቢያ በራፎች ላይ መረጃዎችን ያሰራጫሉ። ይሁንና የመራጮች ተንታኝ የሆኑት ዊሊያም ቦዊ እንዲያሳስትዎት አይፍቀዱላቸው በማለት ሲያስገነዝቡ፤ 

“ፓርቲዎች በምርጫ ቀን በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው 'ድምፅ እንደምን እንደሚሰጡ' የሚሉ እነሱ በሚሹት መልኩ የድምፅ አሰጣጥ ቅደም ተከተልን የያዙ ካርዶችን ያድላሉ። የግድ በእዚያ መንገድ ድምፅዎን መስጠት የለብዎትም። ያ ከምክረ ሃሳብነት ያለፈ አይደለም” ብለዋል።  

ድምፅዎን ይስጡ 

አንድ አረንጓዴና አንድ ነጭ የድምፅ መስጫ ወረቀት ይሰጥዎታል።  

አረንጓዴ የድምፅ መስጫ 

አረንጓዴው የድምፅ መጫ ወረቀት ለአንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (የታችኛው ምክር ቤት) ድምፅ መስጫ ነው።

እያንዳንዱን መራጭ የሚወክሉ 150 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች አሉ። የታችኛውን ምክር ቤት አብላጫ ወንበሮች ያሸነፈ ፓርቲ መንግሥት ይመሠርታል።   

አቶ ቦዊ “ምንም እንኳ ሰዎች ከምርጫ ጋር በተያያዘ አዘውትረው ሀገር አቀፍ መሪን [ጠቅላይ ሚኒስትር] ስለመምረጥ ቢያስቡም፤ ብሔራዊ መሪ የሚሆነው አብዛኛዎቹን የፓርላማ ወንበሮች ያሸነፈው ፓርቲ ነው የሚሆነው፤ እናም ድምፅ የሚሰጡት ለእዚያ መሪ አይደለም” በማለት ያስረዳሉ።  

በአረንጓዴው የምርጫ ወረቀት ላይ ድምፅዎን ለመስጠት፤ ሊመርጡት ከሚሹት ዕጩ ትይዩ ቁጥር ‘1’ን ይፃፉ፤ ከእዚያም ሁለተኛ ምርጫዎ ከሆነው ዕጩ ትይዩ ‘2’ን በመፃፍ በእዚያው መንገድ በሚሹት ሁኔታ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ሠፍርው ያሉ ቁጥር ማስፈሪያዎች እስከሚጠናቀቁ ቅደም ተከተል አስይዘው ቁጥሮችን ማስፈሩን ይቀጥሉ።  

ነጭ የድምፅ መስጫ 

ነጭ የድምፅ መስጫ ከ76ቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (የላይኛው ምክር ቤት) ወንበሮች ለአንዱ ድምፅ መስጫ ነው። እርስዎ ላሉበት ክፍለ አገር ወይም ክፍለ ግዛት የሕግ መወሰኛ ምክር አባል ይመርጡበታል።   

ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ድምፅ መስጠት በተወሰነ መልኩ ለየት ይላል። ረጅሙ የድምፅ መስጫ ወረቀት እርስዎ የሚኖሩበትን ዕጩዎች በሙሉ በአንድ ላይ አካትቶ ስለሚዝ ሲመለከቱት አስፈሪ መስሎ ይታያል።   

“ይሁንንና ድምፅ አሰጣጡ ቀላል ነው” በማለት ያስረዳሉ አቶ ቦዊ።

“ሁለት የሚከውኑበት መንገዶች አሉ። ቁጥር ማስፈሪያ የሆኑ አራት ማዕዘን ሳጥኖች ከመስመር በላይና በታች አሉ። ከመስመር በላይ ያሉት ለእያንዳንዱ ፓርቲ ድምፅ መስጫ ነው። ቀላሉና ፈጣኑ መንገድ ስድስት የሚሿቸውን ፓርቲዎች መርጠው በሚፈልጉት መንገድ በቅደም ተከተል መምረጡ ነው። በተለይ ለአንድ የተለየ ዕጩ ድምፅዎን መምረጥ ካሹ ከመስመር በታች ያሉ ያሉ በርካታ ሳጥኖችን ለይተው ቢያንስ 12 ያህሉን በቅደም ተከተል ማስፈር ያሻል” ይላሉ።  

የምርጫ ወረቅቱ ላይ በሚሹት መልክ የቁጥር ቅደም ተከተሎችን ማስፈሩ ዓላማ ድምፅዎ ከአንድ ዕጩ አልፎ እንዲሔድ ነው። ይህም ድምፅዎ ሌሎች ዕጩዎችንም እንዲያካትት የሚያስችል "የቅደም ተከተል ድምፅ አሰጣጥ" የሚሰኘው ነው።  

“አንድ ቁጥር ድምፅዎን የሰጡት ሰው ከሌሎቹ ቀዳሚ ተመራጭ ሲሆን፤ በቀጣይነት የሚያሠፍሩት እስከ መጨረሻው ዕጩ ድረስ የቅደም ተከተል ፍሰትን የጠበቀ ተመራጭነት ይኖረዋል” በማለትም የአምኮ ቃል አቀባይ ኢቫን ኢኪን-ስሚዝ ያስረዳሉ።
VOICE REFERENDUM MELBOURNE
A ballot box is seen inside the voting centre at Collingwood in Melbourne, Saturday, October 14, 2023. Credit: CON CHRONIS/AAPIMAGE

ተቆጣሪ የማይሆን ድምፅ 

ድምፅ በሚሰጡበት ወቅት የድምፅ አሰጣጥ መመሪያዎችን በአግባቡ መተግበርዎን በጥንቃቄ ያስተውሉ። ድምፅ የሰጡበት ወረቀት በአግባቡ የተሞላ ካልሆነ 'ተቆጣሪ የማይሆን ድምፅ' ይሆናል፤ እናም የምርጫ ውጤት ላይ ሳይካተት ይቀራል።  

ድምፅ ሳይሰጡ የቀሩ እንደሁ ምን ይከተላል? 

ድምፅ መስጠት ግዴታ ነው። ድምፅ ላለመጠት ተገቢ ምክንያቶች ሊኖርዎት ይገባል፤ ያም በአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን የሚገመገም ይሆናል። ለምሳሌ ያህል የተወሰኑ ባሕር ማዶ ያሉ ሰዎች ድምፅ ለመስጠት የሚሳናቸው ሊሆን እንደሚችል አምኮ ይረዳል።  

“ለምርጫ ተመዝግበው ግና ድምፅ ያልሰጡ ሰዎች ካሉ፤ ድምፅ ያልሰጠ መራጭ ማሳሰቢያ ይደርሳቸዋል”

“ተቀባይነት ያለው ምክንያት ካለዎት ግና ያ ምንም አይደል። ብቻ ያስታውቁን። አለያ የ$20 መቀጮ ያገኝዎታል። ምክንያትዎን የሚያስረዳ ምላሽ ካላገኘን ግና ፍርድ ቤት ቀርበው የ$170 ብር ክፍያ በተጨማሪም የፍርድ ቤት ወጪን አክለው እንዲከፍሉ ይደረጋል” ሲሉ አቶ ኢኪን-ስሚዝ ያስጠነቅቃሉ።  

እውነተኛው ቅጣት ግና ድምፅዎን ሳይሰጡ መቅረትዎ ነው። እናም፤ ሁሌም መጠነኛ ምርምር ያካሂዱና ግንዛቤን የጨበጠ ድምፅ ይስጡ።  

የአምኮ አሳሳች መረጃ መመዝገቢያ 

አምኮ ነፃና ገለልተኛ ነው፤ የምርጫ ሂደቱም በእጅጉ ብርቱ ነው። አምኮ በአውስትራሊያ ምርጫ ሂደት ዙሪያ አሳሳችና አታላይ መረጃን ለመከላከል ይፋ አድርጓል።  

እንደምን ድምፅ እንደሚሰጡ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የአምኮ ድረገፅን ወይም በ 13 23 26 ይደውሉ። 

ይህ ክፍለ ዝግጅት ቀደም ሲል በ2022 የቀረበ ሲሆን፤ የእውነታ ማጣሪያና ወቅታዊ ማሻሻያ ተደርጎበታል።
Subscribe or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.

Do you have any questions or topic ideas? Send us an email to [email protected]

Share