የማኳየሪ ዩኒቨርሲቲዋ ኢሌኒ ፖዩሎስ አውስትራሊያ ከሃይማኖት ጋር ረጅምና ውስብስብ ግንኙት ያላት ስለመሆኑ ያመላክታሉ።
አሁንም፤ ዳግምም ያ ዓይነቱ ግንኙነት ፍንጥቅ ይላል።ኢሌኒ ፖዩሎስ፤ የዩናይቲንግ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪ
ሰዎች ከግብር ቅነሳና የኑሮ ውድነት እፎይታ ቃል ኪዳኖች ይልቅ ይበልጥኑ ዕሴቶቻቸው መሠረት በማድረግ ድምፃቸውን ለመስጠት እንደሚያዘሙ ለSBS Examines ተናግረዋል።
"በተወሰኑቱ ዘንድ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች በግብረገባዊ ጉዳዮች ላይ ያሏቸውን አተያዮች በመመዘን ድምፅ አሰጣጣቸውን ከመለወጥ አኳያ ተፅዕኖ ይኖረዋል" ባይም ናቸው።
በእዚህ ማን ነው ቀኝ ክንፍ? ማን ነው ግራ ክንፍ? ክፍለ ዝግጅታችን እምነት በመጪው የፌዴራል ምርጫ ላይ የሚኖረውን ሚና እንቃኛለን።