የሕግ ሽንቁሩ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ፖለቲካዊ ቅጥፈትን ይፈቀዳል

Advance Australia sign depicting ACT independent Senate candidate David Pocock as a "Greens superman"

Cartaz do grupo conservador Advance Australia retrata o candidato independente ao Senado pelo ACT, David Pocock, como um "super-homem dos Verdes". Source: Twitter / Twitter / David Pocock

የምርጫ ቀን ለሜይ 3 / ሚያዝያ 25 ቀን ከተቆረጠለት ወዲህ የምረጡኝ ዘመቻዎች በይፋ ተጀምረዋል። ይሁንና ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች መዘዋወር ከጀመሩ ወራትን አስቆጥረዋል። እያሉ ያሉትን ያምናሉን?


በምርጫ ድንጋጌው ምርጫ በይፋ ተጠርቶ የምረጡኝ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት አሳሳች ማስታወቂያዎች እንዲዘዋወሩ የሚፈቅድ ሽንቁር አለ።

ይህም ዕጩ የፖለቲካ ተወዳዳሪዎቹን ስም ማጉደፍ ብቻ ሳይሆን፤ የምርጫ ሂደቱም ላይ ጭምር ጉዳት እንደሚያደርስ የመስኩ ጠበብት ይናገራሉ።

በ 2022 የአውስትራሊያ መዲና ግዛት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ገለልተኛ ተመራጭ አባል ዴቪድ ፖኮክ፤ በዲጂታል የተቀናበረ ምስላቸው የምርጫ ቀን ከተቆረጠ አንድ ወር በኋላ በመዘዋወሩ የቅሬታ አቤቱታቸውን ለአውስትራሊያ የምርጫ ኮሚሽን (አምኮ) አቅርበዋል።

በጎዳና ጠርዝ ተተክሎና በምርጫ ጣቢያዎች አቅራቢያ የጭነት መኪናዎች ላይ ተለጥፎ የነበረው ምስል ፖኮክ ሸሚዛቸውን አስፍተው ከፍተው የግሪንስ ፓርቲን መለያ ምልክት ሲያሳዩ ያሳያል።

ምስሉ ለዕይታ እንዲበቃ ይሁንታ የተቸረው በወግ አጥባቂው ጎትጓች ቡድን አድቫንስ አውስትራሊያ ነበር።

አምኮ ምስሉ አሳሳች በመሆኑ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለዕይታ ሊበቃ እንደማይገባው ወሰነ። አድቫንስ አውስትራሊያ በምርመራ ግኝቱ እንደማይስማማ ግና ለዕይታ ላለማብቃት ተስማማ።
dyson_ad.PNG
Digitally altered flyers of Alex Dyson, authorised by Advance Australia, were placed in voter's mailboxes throughout the candidate's electorate of Wannon. Credit: Supplied
ማርች 31 የ2025 ፌደራል ምርጫ ቀን ተቆረጠ፤ የምርጫ ዘመቻም በይፋ ተጀመረ።

እናም አድቫንስ አውስትራሊያ በእዚህ ዓመት አዲስ ፊት ግና በተመሳሳይ መልኩ በዲጂታል የተቀናበረ ምስል ወርኅ ፌብሪዋሪ ውስጥ ለመቀስቀሻነት ለመጠቀም ወሰነ፤ ይሁንና ይህን ሲያደርግ ግና ሕግ እንደጣሰ አልተቆጠረም።

ምስላቸው በዲጂታል ተቀናብሮ ዋነን የምርጫ ክፍለ ከተማ ላይ የግል ተወዳዳሪው አሌክስ ዳይሰን ሸሚዝ ተከፍቶ የግሪንስ ፓርቲን መለያ ምልክት የሚያሳይ በራሪ ወረቀቶች ይታደሉ ነበር።

አቶ ዳይሰን ምስሉ ለዝንቅ አተያዮች መንፀባረቅ አስባብ መሆን መቻሉን አስመልክተው ሲናገሩ፤

“በተወሰኑቱ ዘንድ በደቃቅ ጽሑፍ የአድቫንስ አውስትራሊያን አሰራጭነት ሲመለከቱ ግልፅ ድንጋጤን አሳድሮባቸዋል። በሌሎች የዓይን ምልከታቸው የደበዘዘ ወይም ወይም ደቃቅ ፅሁፉን ልብ ብለው ባላዩቱ ዘንድም እንዲሁ ምክንያቱ ለየት ባለ ሁኔታ ድንጋጤን አሳድሯል" ብለዋል።
በእጅጉ ልቅ ነው።
”የሞናሽ የሕግ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዪ-ፉይ ንግ አድቫንስ አውስትራሊያ "እንዲህ ያለው ተግባር ተፈቃጅ እንዳልሆነ ተነግሮታል፤ ሆኖም ሕጉ ውስጥ ሽንቁር መኖሩን ፈልጎ አግኝቷል" ሲሉ አመላክተዋል።

የአድቫንስ አውስትራሊያ ቃል አቀባይ ለ SBS Examines ስለምን እንደከወኑት ሲናገሩ፤ እንደ አቶ ዳይሰን ዓይነቱ ምስል ስርጭት "የምርጫ ሕጎችን የጣሰ አይደለም" ተብለው በአምኮ እንደተነገራቸው ተናግረዋል።

የምርጫ ድንጋጌ አንቀፅ 329 ድምፅ ሰጪዎችን የሚያታልሉ ወይም የሚያሳስቱ ቁሶችን ማሰራጨት እንደማይቻል ይከለክላል፤ ክልከላው ግና ፅናት ያለው የምርጫ ቀን ከተቆረጠ በኋላ ነው።

የአውስትራሊያ ዲሞክራሲና ተጠያቂነት ተቋም ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢል ብራውን፤ የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን አስመልክቶ የትኞቹ አሳሳቾች እንደሆኑ መለየቱ የተመልካቹ ፈንታ አንደሆነ ሲያመላክቱ፤

“ማስታወቂያን ሲገመግሙ ጤናማ ጥርጣሬን ማሳደር ሁሌም ጥሩ ነው፤ በተለይም ለፖለቲካ ማስታወቂያ፤ እንዲያ ዓይነቱን ጥርጣሬ በእጥፍ ማድረጉ" ብለዋል።

Share