ሳኒል ከፌስቡክ ገበያ መኪና ገዛ። ግና መንዳት እንደጀመረ መኪናው ስጋት ፈጣሪ ድምፆች መፍጠር ጀመረ።
ሳኒል ለሻጩ መኪናውን መልሶ እንዲወስድ ጠየቀ። ቆየት ብሎ ግና፤ ሳኒል መኪናውን አስጠግኖ ለማሠራትና የማወራረጃ ክፍያ ለመክፈል ወሰነ።
በአፀፋው "ሻጩ ያስፈራራኝ ጀመር፤ በጠበቃው በኩል እንደሚያናግረኝና ፍርድ ቤት እንደምንገናኝ ነገረኝ።"
"እንዲያም በመሆኑ፤ በእኔ የቪዛ ሁኔታ ሬኮርዴ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት መሔዱ አሰጋኝ። እናም፤ ተጨማሪ ወጪ አውጥቼ መኪናውን እራሴ አሠራሁ" ሲል ለSBS Examines ተናግሯል።
ሳኒል፤ የእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በበርካታ በቪዛ ነዋሪዎች ዘንድ ያለ የጋራ አስተሳሰብ እንደሁ ስገልጥ፤
"የእኔ ማኅበረሰብ ውስጥ ከመቀጮ ጋር በተያያዘ ቪዛችን ይሰረዛል የሚል ፍርሃት አለ። አንዳንዴ መቀጮው የተጣለባቸው ምንም እንኳ የእነሱ ስሕተት ወይም ጥፋት ሆኖ እንዳልሆነ ቢያውቁም ዝም ብለው ይከፍላሉ" ብሏል።
የኢሚግሬሽን ምክርና መብቶች ማዕከል ዋና ጠበቃ አን ኢማኑኤል፤ እንዲህ ያሉቱ በርካታ ፍርሃቶችና የተሳሳቱ መረጃዎች ከፍልሰት ሥርዓቱ ውስብስብነት ጋር የሚያያዙ ናቸው ሲሉ ይናገራሉ።
"ከደምበኞቻችን ስለ ቪዛ ስረዛና ወደ መጡበት እንዲመለሱ ማድረግን የመሰሉ በርካታ ነገሮችን እንሰማለን . . . ከፊሉ ምክንያት የፍልሰት ሥርዓቱ ውስብስብ መሆን፣ ቀጥተኛ ወይም ለመረዳት ቀላል ነገር አለመሆኑ ነው" በማለት ይገልጣሉ።
ወ/ሮ ኢማኑኤል ለቪዛ አግባብ የለሽ ተፅዕኖ የመዳረግ የተለመዱ ክስተቶች የሚፈፀሙት አንድም በመሥሪያ ቤቶች ወይም ከቤት ውስጥ አመፅ ጋር ከተገናኙ ሁኔታዎች በመያያዝ እንደሁ አመላክተዋል።
"ስለ እውነት፤ ቢለቅቁ ወይም ሪፖርት ቢያደርጉ መዘዞቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ትልቅ ፍርሃት አለ" ብለዋል።.
በእዚህ የSBS Examines ክፍለ ዝግጅት በእርግጥ ቪዛዎን ሊያሰርዙ የሚችሉ ምን እንደሆኑና እንደምን የተሳሳተ መረጃ ምን ያህል አግባብ የለሽ የቪዛ ተፅዕኖን እንደሚያሳድሩ እናነሳለን።