አውስትራሊያ ውስጥ ስለ ኦንላይን ሸመታ ሊያውቋቸው የሚገቡ

Overhead View Of Young Woman Doing Online Shopping With Laptop

Although technology has made shopping easier, it comes with risk. Source: Moment RF / Oscar Wong/Getty Images

የኦንላይን ሸመታ ለደንበኞች የቁጠባ አመቺነትን አክሎ በርካታ ትሩፋቶችን ለሸማቾች ያስገኛል፤ ሆኖም ለተጋላጭነትም ይዳርጋል። አያሌ ሕጋዊ ቸርቻሪዎች የግለሰቦችን ዳታ እንደሚሰበስቡት ሁሉ ዳታ ጠላፊዎችም እያደገ የመጣውን የኤሌክትሮኒክ ንግድ አጋጣሚን ተጠቅመው ተጋላጭ የሆኑ አውስትራሊያውያንን ያታልላሉ።


አንኳሮች
  • የኤሌክትሮኒክ ንግድ አውስትራሊያ ውስጥ እያደገ መሔድን ተከትሎ የኦንላይን ሸማቾች ለመጭበርበር ተጋላጭነትም አብሮ ከፍ ብሏል
  • ቅናሽ የሚቸሩ የበርካታ ቸርቻሪዎች የታማኝነት ፕሮግራሞች የግለሰቦችን ዳታ ለገበያ ማስተዋወቂያ ዓላማነት ይውላል
  • ዳታ ጠላፊዎች እንዲህ ባሉ ዳታዎችን ወደ ስውር ገበያ ወስደው ለመሸጥ ስለሚሹ ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው
  • የሳይበር ወንጀለኞችም እንዲሁ የሰዎችን ገንዘብና ማንነቶችን ለመስረቅ የሐሰት የኦንላይን ሸመታ ሱቆችን ይከፍታሉ
ምንም እንኳ የኦንላይን ሸመታ ባለፈው አንድ አሠርት ዓመት እያደገ የመጣ ቢሆንም፤ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ግና እጅጉን አሻቅቧል።

በቅርቡ አንድ ከአምስት አንድ አውስትራሊያውያን ቢያንስ ግሮሰሪዎቻቸውን በኦንላይን ሸምተዋል። ሌሎች ጥናቶችም በፊናቸው በወረርሽኙ ወቅት የኦንላይን ሸመታዎች በሶስት እጥፍ ማሻቀባቸውን አመልክተዋል።

በታዝማኒያ ዩኒቨርሲቲ የንግድና ምጣኔ ሃብት ኮሌጅ ገዲብ የገበያ ማስታወቂያ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሉዊዝ ግሪመር የተወሰኑ መልካም ቸርቻሪዎች ከወረርሽኙ በፊት የኦንላይን ሱቆችን አቁመው እንደነበር አመልክተው፤ ቀውሱ በተጨማሪ በርካታ ቸርቻሪዎች የዲጂታል ሱቅና አገልግሎቶቻቸውን እንዲያሻሻሉ ግድ ስለማሰኘቱም ሲጠቅሱ፤

“ከወረርሽኙ በፊት የኦንላይን ሸመታ ያደርጉ የነበሩ አውስትራሊያውያን 40 ፐርሰንት ነበሩ። አሁን ግና ወረሽኙን ተከትሎ የኦንላይን ሸማቾች ቁጥር 50 ፐርሰንት ደርሷል’’ ብለዋል።

ዶ/ር ግሪም አክለውም፤ በርካታ ቸርቻሪዎች ደንበኞቻቸውን ይዘው ለመቆየት ማማለያ ትሩፋቶችን ጨምረው አገልግሎቶቻቸውን ከፍ አድርገው ለማበርከት ድረ ገፆቻቸውን፣ አገልግሎቶቻቸውንና አቅርቦቶቻቸውን እያያሻሻሉ እንደሆነና ያም ዋጋን ጠያቂ መሆኑን ተናግረዋል።

የኦንላይን ችርቻሮ ድረ ገፆች በአብዛኛው የቅናሽ ሽያጮችን በማስተዋወቅ ወይም የነፃ መሸመቻ አነስተኛ የገንዘብ ዋጋ ያላቸውን ካርዶች በመቸር፣ የሸመቱት ካልተስማማቸውም መመለስ እንዲችሉ በማድረግና ልዩ ቅነሳዎችን በማድረግ ደንበኞች ገንዘብ እንዲቆጥቡ ያስችላሉ።

ይሁንና ደንበኞች ቸርቻሪዎች የታማኝነት ፕሮግራሞችን እነሆኝ ሲሏቸው በሌላ በኩል የግለሰብ ዳታንና የሸመታ ባሕሪይን እየሰበሰቡ መሆኑን ልብ ሊሉ ይገባል።

እውነት ነው፤ በድረ ገፆቻቸው ምን እያደረጉ እንደሁ ይከታተልዎታል፤ የተወሰኑ የግል መረጃን እየቸሯቸው መሆኑ ግልፅ ነው።
ዶ/ር ሉዊዝ ግሪመር፤ በታዝማኒያ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ምጣኔ ሃብት ኮሌጅ ገዲብ መምህርና ተመራማሪ
Blue silhouette hacker
Source: Getty / Getty Images
የዳታ ቋቶች የደንበኛን መረጃ መያዥና የሸመታ ልማዶቻቸውን ሕጋዊነት ላለው የገበያ ማስታወቂያ ዓላማ ዳታ መሰብሰቢያ ናቸው። እንዲሁም፤ ተጠቃሚው ስምምነቱን የገለጠ ከሆነ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው ሊሸጡት ይችላሉ።

በሌላም በኩል፤ ይህ የሳይበር ወንጀለኞችና ዳታ ጠላፊዎችም ለራሳቸው ጥቅም ማግኛ እንዲሆናቸው የሚሹት መረጃ ነው። የግለሰብ መረጃ በስውር ገበያ የሚሸጥና ትርፍም አስገኚ ነውና።

የሐሰት ኦንላይን ሱቆችና የማንነት ስርቆት

በኦንላይን ሸመታ ውስጥ አንዱ ትልቅ ተጋላጭነት ገንዘብ ወይም የግለሰብ ማንነትን ለመስረቅ በአጭበርባሪዎች የቆሙ የሐሰት ሱቆች ናቸው።

ይህንን አስመልክቶ የአውስትራሊያ ፉክክርና ደንበኛ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ደሊላ ሪካርድ ሲናገሩ “በአሁኑ ወቅት አጭበርባሪዎች የሐሰት ሱቆችን አንድም በኢንተርኔት፤ አብዝተውም በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል እያቆሙ ነው" ብለዋል።

ወ/ሮ ሪካርድ የሐሰት ድረ ገፆችን ለመለየት በእጅጉ አዋኪ እንደሆነ ያስጠነቅቃሉ። የኦንላይን አጭበርባሪዎች አዘውትረው ተአማኒነት ለማግኘት የአውስትራሊያ ድርጅቶችንና አርማዎቻቸውን አስመስለው እንደሚጠቀሙም ልብ ያሰኛሉ።
አዘውትረው በጣሙን ዝቅ ባሉ ዋጋዎች ምርቶቻቸውን ወይም እውነት ይሆን በሚያሰኝ መልኩ ትሩፋቶችን ያስተዋውቃሉ።
“በአብዛኛው የአውስትራሊያ ኩባንያ መስለው ይቀርባሉ፤ እንዲሁም የተሰረቁ የአውስትራሊያ የንግድ ቁጥርን ይጠቀማሉ" ሲሉም ወ/ሮ ሪካርድ ያክላሉ።

ድረ ገፁ እንደ ክሪፕቶከረንሲ ወይም ቫውቸሮችን የመሰሉ ያልተለመደ ወይም እንግዳ የሆነ የክፍያ ዘዴዎችን ከጠየቀ ከማጭበርበር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችልም አመላክተዋል።

መጭበርበር ሲገጥምዎት ለባንክዎ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁም ምክረ ሃሳባቸውን ይቸራሉ።
መጭበርበርዎን እንደተረዱ በአስቸኳይ የተጭበረበሩ መሆኑን ለባንክዎ በማስታወቅ ራስዎን በተሻለ መልኩ።
ደሊላ ሪካርድ፤ አ ፉክክርና ደንበኛ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር
ወ/ሮ ሪካርድ በማከልም ከምርት አቅርቦት መዘግየት ጋር ተያይዞ ለደንበኞች የተጭበረበሩ ስለመሆንና አለመሆናቸው ወይም ሕጋዊ ሆኖ የዘገየባቸው ስለመሆኑ ለመረዳት አዋኪ እያደረገባቸው እንደሁም ሲያክሉ፤

“በአሁኑ ወቅት በኦንላይን ሽያጭ የተጭበረበሩ መሆንና አለመሆንዎን ለመለየት በአቅርቦት ችግሮች ሳቢያ አዋኪነቱ እየጨመረ ነው። ይህም ማለት ነገሮች የሚዘገዩ መሆኑን እየተላመድን መሆኑም አንዱ ታካይ ችግር ሆኗል” ብለዋል።

መጭበርበር ሲደርስብዎ ምን ማድረግ ሊያደርጉ እንደሚገባ

በርካታ የኦንላይን መጭበርበሮች የተተለሙት የግለሰቦችን ዕድሜ፣ ስሞችና አድራሻዎችን ለመጥለፍ ነው። ሌላው በእጅጉ የሚሹት የመንጃ ፈቃድና የፓስፖርት ቁጥሮችን ነው።

እኒህን ማጭበርበሮች በአብዛኛው የሚጠቀሙባቸው የግለሰቦችን ማንነቶች ለመስረቅ ነው።

“የእርስዎን ስም፣ አድራሻ፣ የልደት ቀን ምናልባትም የስልክ ቁጥርዎ ካላቸው ወደ እርስዎ የገንዘብ ተቋማት እርስዎ ተመስለው መሔድ ይችላሉ” ሲሉ በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዩተርና መረጃ ፕሮፌሰር ሻንቶን ቼንግ ያሳስባሉ።

አክለውም “ሁሉም ሕጋዊ ተቋማት እርስዎ ማን እደሆኑ የሚያጣሩት ለዚይ ነው" ብለዋል።

ወ/ሮ ሪካርድ ማናቸውንም የግል መረጃ ተጭበርብረው አሳልፈው የሰጡ ሰዎች በተቻለ ፍጥነት ለ እንዲያገኙ ያሳስባሉ።

ወ/ሮ ሪካርድ የኦንላይን ሸማቾች አዘውትረው እንዲጎበኙ ወይም በመጎብኘት ስለተለመዱ የማጭበርበር ዘዴዎችን እንዲረዱም ያበረታታሉ። መረጃዎቹ በ10 የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛሉ።

የማንነት ስርቆትን ለመከላከል በመንግሥት የሚደጎመውን መጎብኘትም አንዱ ሌላ አማራጭ ነው።
SCAM CONCEPT
Scam Source: Getty / Getty Images
ዶ/ር ግሪም የኦንላይን ሸማቾች የሚጎበኟቸው ድረ ገፆች ክፍያንና የግለሰብ መረጃን አያያዝ ሬኮርዳቸው የተከበረ ስለመሆኑ ደግመው እንዲያጣሩ ምክረ ሃሳባቸውን ሲቸሩ፤

“የቸርቻሪውን ድረ ገፅ ሲጎበኙ ትንሽዬ የቁልፍ ምልክት መኖሯን ልብ ይበሉ። ስለምን ያ ማለት ድረ ገፁ አስተማማኝ ነው ማለት ነው። እንዲሁም፤ ድረ ገፁ ታዋቂ ስለመሆኑ፣ ክለሳዎቹንና ደረጃዎችን መመርመር ይችላሉ" ብለዋል።

ለኦንላይን ሸመታ አዲስ የሆኑ ሰዎች የሚጎበኟቸው ድረ ገፆች ተአማኒ ስለመሆንና አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ ቤተሰባቸውን ወይም ጓደኞቻቸውን በማማከር እርዳታን ሊያገኙ ይችላሉ።

አጭበርባሪዎቹ እዚሁ አውስትራሊያ ውስጥ ከሆኑ አንዳንዴም ወደ ፖሊስም ሳይኬድ በራስ መከወን ይቻላል።

Share