30 የሽልማት ዘርፎችን ያቀፈው ሥነ ሥርዓት የተካሔድው ዓርብ መጋቢት 6 / 2016 / ማርች 15, 2024 በክራውን ፖላዲየም ነው።
የSBS አማርኛ ፕሮግራም ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ ነገዎና ጋዜጠኛ ሩቺካ ታልዋር ለሜልበርን ፕሬስ ክለብ በመድብለባሕል ጉዳዮችና ሚዲያ ዘርፍ በአውስትራሊያ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ሙያ የላቀ ደረጃ ያለውን 29ኛውን የኩዊል የጋዜጠኛንት ልህቀት ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁት በሚል ርዕስ የኢትዮጵያዊቷን ቤተልሔም ጥበቡ የናሩ ዕገታ ማዕከል ስቃይና የመንፈስ ፅናት አስመልክተው ባቀረቡት መጣጥፍ ነው።
የSBS አማርኛ ፕሮግራም መጣጥፍ ከABC News፣ Herald Sun እና Guardian Australia ጋር ተወዳድሮ ለአሸናፊነት ብቁ የሆነበት ምክንያት "አስደናቂው መጣጥፍ የአውስትራሊያን ቀጪ የኢሚግሬሽን ማዕከል ፖሊሲዎች መርምሯል። ርዕሰ ጉዳዮ ብርቱ ነው፤ እንዲያም ሆኖ ግና ጋዜጠኞች ካሣሁን ነገዎ እና ሩቺካ ታዋር ጥርት ባለ ትረካቸው በጣሙን ሰብዓዊ የሆነ ታሪክ አቅርበዋል።

Kassahun Seboqa Negewo, Executive Producer of the SBS Amharic Program (L), CEO of Gandel Foundation (C), and Shirley Glaister (representative of Journalist Ruchika Talwar - R). Credit: MPC
በዕለቱ በ30 የተለያዩ የጋዜጠኝነት ሙያ ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ የአውስትራሊያ ዋነኛ ፕሮፌሽናል ሚዲያ ዝነኛ ጋዜጠኞች ከወርቅ ኩዊል እስከ የሕይወት ዘመን ሽልማቶችን ተቀብለዋል።

Winners of the Melbourne Press Club’s 29th Quill Awards for Excellence in Victorian Journalism. Credit: MPC