አንኳሮች
- ከሰሎሞን ደሴቶች ወደ አውስትራሊያ
- የመንፈስ ሁከት
- የዳግም ሠፈራ ሕይወትና ትልሞች
ከናሩ ወደ ብሪስበን
ቤተልሔም ጥበቡ፤ ከሁለት ዓመታት የናሩ አግልሎ ማቆያ ማዕከል ምሬት የተመላበት ሕይወት በኋላ ለሕክምና ወደ ብሪስበን - አውስትራሊያ እንድትሔድ ተደረገ።
በ2015 ከናሩ ዕገታ ማዕከል በሕክምና አስባብ ብትወጣም ከብሪስበን አግልሎ ማቆያ ማዕከል ግና አላመለጠችም።
ብሪስበን እንደደረሰች ሕክምናዋን ጀመረች።
ለስድስት ወራት ያህል የመንፈስ ሁከቷ አልቀለልም።
ከመንፈቅ ሕክምና በኋላ ግና ትኩረቷ በሕይወት የመኖር ውሳኔ ላይ አረፈ።
በ2017 ለሁለት ዓመታት ተገልላ ከቆየችበት ማዕከል ነፃ ተለቀቀች።
ያለ ልዋጭ ገላዋን የሸፈነውን ልብስ ብቻ ለብሳ ናሩ የገባችውና ለመኝታ የተሰጣትን አንሶላ ሰፍታ ለመልበስ ግድ ተሰኝታለች የነበረችው ቤተልሔም፤ ብሪስበን ላይ አዲስ ሕይወት ጀመረች።
ራስን ችሎ የመኖር ጅማሮ ግና ግርታን ፈጠረባት።
ከአራት ዓመታት ራስን በራስ ማስተዳደር መለየት በኋላ የቴሌቪዥን፣የስልክ አጠቃቀምና ምግብ ማብሰል ጋር ራሷን ዳግም ማላመድ ያዘች።
ትንሽ ቆይታም ሌሎች ጥገኝነት ጠያቂና ስደተኞች እሷ ባለፈችባቸው የፈተና መንገዶች እንዳያልፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ በመሆን ድምጿን ማሰማት ጀመረች።
የብሪስበን ሕይወት እምብዛም ስላልጣማት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አያሌ ፍልሰተኞች ወደሚኖሩባት ሜልበርን ከተማ አመራች።
የዳግም ሠፈራ ሕይወቷ ከአውስትራሊያውያን ከመገለል፤ ከቶውንም አውስትራሊያውያን ተገቢ ቲኬት ይዘው በሕዝብ ትራንስፖርት ይጓዙ እንደሁ ተቆጣጣሪ ለመሆን በቃች።
መንገዱ ውስብስብና ረጅምም ቢሆን የፓርላማ አባል በመሆን ለአውስትራሊያውያን ማለፊያ የሕይወት ለውጥ ለማስገኘት ተልማ አለች።