"የስደተኞች ወደ ናሩ ዕገታ ማዕከል መወሰድ ልቤን በጣም ነው የሰበረው፤ የእኛም አውስትራሊያ የመቆየት ጉዳይ የተወሰነ ስላልሆነ ሁላችሁም ፀልዩልን" ቤተልሔም ጥበቡ

Betty Tibebeu Pic.jpg

Bethlehem Tibebu. Credit: B.Tibebu

በናሩና ብሪስበን ዕገታ ማዕከላት ለአራት ዓመትታ የቆየችውና አሁንም በየስድስት ወራት ታዳሽ በሆነ ጊዜያዊ የመቆያ ቪዛ አውስትራሊያ ውስጥ የምትገኘው ቤተልሔም ጥበቡ የስደተኞች መብቶችም ተሟጋች ናት። ሰሞኑን አገር አቀፍ ክርክር በቀሰቀሰው በጀልባ ወደ አውስትራሊያ የዘለቁ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ናሩ የመላክ ውሳኔን አስመልክታ ትናገራለች። የናሩ ቆይታዋ ያሳደረባትንም ተፅዕኖዎች ታነሳለች።


አንኳሮች
  • የናሩ ዕገታ ማዕከል ፈታኝ ሕይወት
  • ስደተኞችን ወደ አውስትራሊያ ለሕክምና የማምጣትና የመከልከል ክርክር አተያዮች
  • እንጥልጥል የወደፊት ዕጣ ፈንታ

Share