አንኳሮች
- ትላልቅ ከሆኑትና እንደ ዕፅዋት ተክል ሥፍራዎች ይዘው ካሉቱ መናፈሻዎች በስተቀር አብዛኛዎቹ የከተማ መናፈሻዎች በማዘጋጃ ቤቶች ኃላፊነት ስር የሚገኙ ናቸው
- በአብዛኛው መናፈሻዎች ውስጥ በተለይ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን የማዘጋጃ ቤት ፈቃድንና ክፍያን ግድ ይላል
- የማኅበረሰብና የሌሎች ጎብኚዎች ፍላጎቶች መገፋፋትን ከመናፈሻ ሥነ ምግባር ጋር አዛምዶ ልብ ማለትን ይሻልሻል
እኒህ አረንጓዴ ሥፍራዎች ከውሻ ጋር የእግር ጉዞ ማድረግን፣ መዝናናትን፣ የአካል እንቅስቃሴ መፈፀምን፣ ማኅበራዊ ስብስብ ማከናወንን፣ የብረት ምጣድ ጥብሶች መጥበስን፣ ኩነቶችን ለማካሔድና ለሌሎችም በርካታ ክንውኖች ይውላሉ።
ሳሚ ዶቢንሰን የሁለት ልጆች እናትና ለልጆችና ለቤተሰቦች በነፃ ወደ ውጪ መውጫ ምክረ ሃሳቦችን ሰጪ የሆነው የ ድረ ገፅ ተባባሪ ዳይሬክተር ናቸው። ከተማቸው ውስጥ የሚገኙ አያሌ አረንጓዴያማ ሥፍራዎችን ጎብኝተዋል።
“ሰዎች ስለሚሔዱበት መዳረሻ፣ ሁሌም ኪሶቻቸውን ለወጪ ሳይዳብሱ በመጠኑ መደሰትን የማወቅ ችሎታ ያሻቸዋል”
“እናም በአብዛኛው፤ መናፈሻ ወደ አዲስ ሠፈር ሲገቡ ቀድሞ የሚነሳ ማረፊያ ሥፍራ፣ ከማኅበረሰቡ ውስጥ ጓደኞችን የማፍሪያና ስለ አካባቢው የተወሰኑ መረጃን ማግኛ ምርጥ ሥፍራ ነው” ይላሉ።
Do report any maintenance issues at your local park by contacting the city council. Getty Images/Marianne Purdie Source: Moment RF / Marianne Purdie/Getty Images
አክለውም “ለምሳሌ ያህል የተወሰኑ ስፍራዎች የሚተዳደሩት በመንግሥትና በውክልና ሲሆን ለተወሰኑ መናፈሻዎችና ገላጣ ሥፍራዎች ኃላፊነትን ይጋራሉ"
“ሆኖም አብዛኛዎቹ መናፈሻዎችና ገላጣ ሥፍራዎች በባለቤትነት የተያዙት ወይም የሚተዳደሩት በከተማይቱ ወይም በዘውድ ጥበቃ አስተዳደር ወይም የውክልና አስተዳዳሪ ነው" በማለት ይገልጣሉ።
እንዲሁም፤ ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ ማዘጋጃ ቤቶች ድንኳኖችን የመትከል፣ መኪናዎችን አስገብቶ ማቆምን የመሳሰሉ አጠቃላይ የሆኑ ደንቦች ያሏቸው ቢሆንም፤ እያንዳንዱ ማዘጋጃ ቤት የየራሱ የሆኑ ሥርዓትና ደንቦች ያሉት መሆኑንም ልብ ማለት ጠቃሚ ነው።
አቶ ጆንሰን “ምናልባትም በአካባቢው የተለያዩ ሁነቶች ወይም መጠቀሚያዎች ወይም የሚካሄዱ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከአካባቢው ማዘጋጃ ቤት ጠይቆ መረዳት በጣሙን ጠቃሚ ነው” ሲሉ ያስገነዝባሉ።
Parents of older kids should be mindful when sharing the playground space with toddlers. Getty Images/Jordan Lye. Source: Moment RF / Jordan Lye/Getty Images
ወ/ሮ ዶቢሰን “ከ 400 መናፈሻዎቻችን 50ዎቹ ጋ ብቻ ነው የውሻዎን ማሰሪያ ፈትተው መልቀቅ የሚችሉት። ይሁንና እናም ከ50 ፐርሰንት በላይ ውሾች የሚለቀቁባቸው የመናፈሻ አካባቢ አለን ማለት ነው” ይላሉ።
ምንም እንኳ ውሾች የሚለቀቁባቸው የመናፈሻ ሥፍራዎች አካባቢ የሕፃናት መጫዎቻዎች ካሉ ውሻዎን ለማሰር ግድ መሰኘትዎ ባይቀርም።
“አንዳንዴ ከተመለከትኳቸው ነገሮች ውስጥ ሰዎች የሕፃናት መጫወቻ ያሉባቸው አካባቢ ውሻዎቻቸውን ይዘው ይመጣሉ። ሆኖም ሁሉም ልጆች ከውሻ ጋር ተግባቢ አይደሉም … እናም ሁሌም ዓይንን አለመንቀል ያሻል” በማለት የሚያሳስቡት ወ/ሮ ዶቢሰን፤ መናፈሻንና የልጆች መጫወቻ ሥፍራዎችን አስመልክቶ፤ በቀላሉ ሥነ ምግባራትን ግብር ላይ የማዋል አዘቦታዊ ግንዛቤ ጉዳይ ነው ሲሉም ልብ ያሰኛሉ።
አክለውም “የሚችሉ ከሆነ ቆሻሽዎችዎን ከእራስዎ ጋር ይዘው መሔድ ወይም ከመሔድዎ በፊት የቆሻሻ መጣያ ፈልጎ እዚያው ውስጥ መጣልን፣ ከተጠቀሙ በኋላ ማፅዳትን፣ ልጆች በዕድሜያቸው ተመጣጣኝ በሆኑ መጫዎች እየተጫወቱ እንደሁ ልብ ማለትን፣ ስለምን በዕድሜ ከፍ ያሉ ልጆች ትናንሽ ልጆች መንሸራተቻ ላይ ከላይ ወደ ታች ተንሸራትቶ መውረድ ያሸማቅቃልና፤ እንዲህ የመሳሰሉ ነገሮችን ልብ ማለት ያሻል” ይላሉ።
በተመሳሳይም የልጅዎን የልደት በዓል በአካባቢዎ መናፈሻ ሥፍራ ሲያከብሩ ‘ስለ ሌሎች ያስቡ’ ዓይነት አቀራረብም ይጠበቅብዎታል።
ይህንንም ሲያመላክቱ “ጫጫታን ልብ ሊሉ ይገባል፣ ጎልቶ የሚጮህ ሙዚቃ ማጫወቻዎንም ይዘው ሊሄዱ አይገባም፣ ልጆች እየተሯሯጡ ሥርዓትን እንዳይጥሱ መቆጣጠር፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የተጠቀሙባቸውን ማሸብረቂያዎች (ማሸብረቂያዎችን ያመጡ ከሆነ) ወደ ቤትዎ መልሰው ይዘው ሊሔዱ ይገባዎታል” በማለት ያሳስባሉ።
For small gatherings, barbeque spots and other areas within parks are typically available on a first in best, best dressed basis. Getty Images/Hero Images Inc Credit: Hero Images Inc/Getty Images
ለተደራጀ የመናፈሻ ኩነት/እንቅስቃሴ ፈቃድ ማግኘት ያስፈልገኛልን?
እንደ ሠርጎችና የዓመት መጨረሻ ፓርቲዎች በመሳሰሉ ዝግጅቶች ላይ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለሚታደሙባቸው እንቅስቃሴዎች አስቀድሞ መመዝገብ ወይም ፈቃድ ማግኘትን ግድ ሊል ይችላል።
በተመሳሳይ መልኩም ንግድ ነክ ለሆኑ እንቅስቃሴዎችም እንዲሁ ተመሳሳይ ሂደቶች እንደሚያሹ የሲድኒ ማዘጋጃ ቤቱ አቶ ጆንሰን ሲናገሩ፤
በተለይም በመናፈሻ ላይ ተፅዕኖዎችን የሚያሳድሩ ትላልቅ የሙዚቃ ትዕይንቶች ወይም ገበያዎች ወይም ከሽያጭ ጋር የተያያዙ የንግድ እንቅስቃሴዎች ፈቃድ ማውጣትን ግድ ይላቸዋል።ጆኢ ጆንሰን
መናፈሻዎች ውስጥ አካላዊ እንቅስቃሴን ወይም የጤና ክፍለ ጊዜያትን የሚያካሂዱ ባለሙያ አሰልጣኞችም እንዲሁ ፈቃድ ማግኘትን ግድ የሚላቸው ሲሆን፤ ሲልም እንደ አጠቃቀማቸው ሁኔታ ክፍያ መፈፀምም ሊጠበቅባቸው ይችላል።
የአካላዊ እንቅስቃሴ እድገት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ የውጪ አካላዊ እንቃስቃሴ ክፍለ ጊዜያት ላይ ያተኮረ የግል ስልጠና ንግድ ባለሙያ የሆኑት ስኮት ሃንት በሶስት ክፍለ አገራት ስልጠናዎችን ይሰጣሉ።
“በአንድ ጊዜ ከ10 ላነሱ ሰዎች ስልጠና የሚሰጡ ከሆነ ፈቃድ ማውጣት ያስፈልግዎታል። ይሁንና ከ10 ሰዎች በላይ የያዘ ቡድን የሚያሰለጥኑ ከሆነ ግና የፈቃድ ክፍያ መፈፀም ይጠበቅብዎታል” ይላሉ።
ዋነኛው በመናፈሻ ሥፍራዎች የማዘጋጃ ቤቶች ድንጋጌዎች የመኖሩ አስባብ የሕዝብ ጤናና ደህንነት ደረጃዎችን ማስጠበቅ ለመቻል ነው።
“ፈቃድ ያስፈልግዎታል የማለቱ ሁነኛ ነገር የግል አሰልጣኞቹ የሙያ ብቃቱ ያላቸውና መናፈሻዎቹ ውስጥ የሚሠሩት ከእነማን ጋር እንደሆነ ለይተው ማወቅ እንዲችሉ እንዲያግዛቸው ነው” ሲሉም ሃንት አክለው ያስረዳሉ።
ይሁንና፤ እኒህ ግዴታዎች መናፈሻዎች ውስጥ ለመዝናናት የሚሰባሰብ ቡድንን ላይ ተፈፃሚ እንዳልሆነ ሲያመላክቱ፤
“እርስዎና ወዳጆችዎ፣ የእግር ኳስ ቡድንዎ ወይም የሥራ ባልደረቦችዎ በእራሳችሁ ጊዜ መናፈሻ ውስጥ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን የምታካሂዱ ከሆነ ለትርፍ የምትከውኑት ባለመሆኑ ገደቦች የሉባችሁም። መናፈሻዎቻችን የተዘጋጁት፣ ግብሮችንም የምንከፍለው ለእዚያ ነውና” ብለዋል።
Getty Images/Traceydee Photography Source: Moment RF / Traceydee Photography/Getty Images
ማዘጋጃ ቤቶች የሚከታተሉት እነማንን ነው? እርምጃ የሚወስዱት ቅሬታዎችን ብቻ ተከትለው ነው። ማኅበረሰቡን ቅር ካላሰኙ፤ በችግር ፈጠራ ተጠያቂ አይሆኑም።ስኮት ሃንት
“አዘቦታዊ የሆነ ጨዋነትና ከበሬታ ይኑርዎት፤ የእርስዎ መናፈሻ ሳይሆን የማኅበረሰቡ መናፈሻ መሆኑን ተገንዝበው አካባቢውን ሊንከባከቡ ይገባል” ሲሉም ይመክራሉ።
በአካባቢዎ ማዘጋጃ ቤት የብረት ምጣድ መጥበሻ ይጠቀማሉን?
የመናፈሻ ሥነ ምግባር ቀጥተኛ፣ በአዘቦታዊ ግንዛቤና የጨዋነት መርሆዎች የሚመራ ነው። ያልተደነገጉ ደንቦቹ የሚከተሉት ናቸው፤
- ለደህንነት ቅድሚያ ይስጡ፤ የእራስዎን ታጣፊና ተዘርጊ የብረት ምጣድ መጥበሻ ይዘው የሚመጡ ከሆነ በቅድሚያ እንዲያ ማድረጉ ተፈቃጅ መሆንና አለመሆኑን ከአካባቢዎ ማዘጋጃ ቤት ያጣሩ።
- ንፅህናን አያጓድሉ፤ ምንም እንኳ ማዘጋጃ ቤት የብረት ምጣድ መጥበሻ ማፅዳት ተግባራትን የሚፈፅም ቢሆንም፤ ለቀጣዩ ተጠቃሚ በማሰብ ፀድቶ ካገኙት የበለጠ የተጠቀሙበትን ሥፍራ አፅድተው መሄዱ ከፍ ያለ ጨዋነት ይሆናል።
- መጋራት መተሳሰብ ነው፤ "ቀድሞ የመጣ፤ ቀድሞ ተጠቃሚ ይሆናል" በሚለው አጠቃላይ የሕዝባዊ ሥፍራዎች አጠቃቀም መርህ ተግባራዊ ይሆናል። ይሁንና አያሌ መናፈሻዎች ለሁሉም እንዲዳረስ በሚል ዕሳቤ በርካታ የጥላ መንሸራሽሪያዎችና የሚግሉ መጥበሻዎችን ያቀርባሉ።