ለግል ብድር ለማመልከት ማጤን ያለብዎት መቼ ነው?

Financial advisor with couple explaining options

Financial advisor with couple explaining options. The agent is using a computer. Couple are casually dressed. They sitting in an office and are discussing something with the agent. Credit: courtneyk/Getty Images

አያሌ አውስትራሊያውያን ከመቼው ጊዜ በበለጠ የኑሮ ወጪዎቻቸውን በራሳቸው መንገዶች ማስተዳደርን እያሹ ባለበት ወቅት፤ በርካቶች ወደ ግል ብድሮች እየተመለሱ ነው። አማራጮችን ፍለጋ ላይ ሳሉ፤ ምርምር ማድረግና ባለ ነጠብጣብ መስመር ላይ ፊርማዎን ከማኖርዎ በፊት ሁኔታዎን በጥንቃቄ ያጢኑ።


አንኳሮች
  • እንደ አበዳሪው፣ የብድሩ ዓይነትና የእርስዎ ሁኔታዎች የወለድ መጠኖችና ክፍያዎች ይለያያሉ
  • የእርስዎ የብድር ደረጃ ለአበዳሪው ስለ እርስዎ ብድርን ኃላፊነት በተመላው መልክ መወጣት ይችሉ እንደሁ ይነግራቸዋል
  • አበዳሪዎች ግድ የሚላቸው የእርስዎ የአውስትራሊያ የብድር ታሪክ ብቻ ነው
የግል ብድር ከፍ ያለ ገንዘብ ተበድረው በጊዜ ሂደት ውስጥ ከወለድ ጋር እንዲከፍሉ ያስችልዎታል።

አዘውትረን የግል ብድርን ከግምት ውስጥ የምናስገባው በተለይ ለመኪና፣ ሽርሽር፣ ሠርግ ወይም የተለያዩ ብድሮችን ወደ አንድ ብድር ማጠቃለልን ከመሰሉት ጋር ነው።

እንደ አንድሩ ዳድስዌል፤ የአውስትራሊያ ደህንነቶችና ሙዋዕለ ንዋዮች ኮሚሽን መኒስማርት ቡድን ተጠሪ “የግል ብድር ጠቀሜታ ወጪዎችዎን በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲያደላድሉ ያስችልዎታል፣ በጀት እንዲመድቡና ገንዘብዎን ደርዝ እንዲያሲዙ ያግዝዎታል”
“የግል ብድር ጎጂነት፤ክፍያና እርግጥ ነው፤ የወለድ ክፍያም ያስከፍልዎታል፤ አብሮ ተያያዞ የሚመጣ ነው” ብለዋል።

የተዘወተረው የብድር መጠን ከ $2,000 እስከ $100,000 ሲሆን፤ መልሶ ክፍያ የመፈፀሚያ ጊዜያቱም ከሁለት እስከ ሰባት ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው።

የግል ብድር መሥፈርትን የሚያሟሉ ነዎትን?

ለማመልከት፤ የአውስትራሊያ ዜጋ ወይም ዕድሜዎ 18 ዓመት ወይም ከዚያ የበለጠ ቋሚ ነዋሪ መሆንን ግድ ይላል።

አቶ ዳድስዌል “የጊዜያዊ ቪዛ ባለቤት ሆነው የግል ብድር ሊያገኙ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች አሉ፤ ይሁንና ታካይ መሥፈርቶች ይኖራሉ” በማለት ያስረዳሉ።

አበዳሪዎች ፍላጎት የሚሳድሩት የእርስዎ የብድር ታሪክ ላይ ብቻ ነው። ስለ አሠሪዎ ዝርዝር መረጃን ይጠይቃሉ፣ የማንነት ማረጋገጫ፣ ምን ዓይነት ንብረቶች እንዳለዎትና የብድር ካርዶችን አካትቶ ያለብዎትን ዕዳዎች ይጠይቃሉ።

እንዲሁም ‘የክሬዲት ደረጃ’ዎን ይመለከታሉ።
Credit report form on a desk with other paperwork.
Credit report form on a desk with other paperwork. There are also a pen, glasses and a calculator on the desk Credit: courtneyk/Getty Images

የክሬዲት ደረጃ ምንድነው?

ኤሚ ብራድኒ-ጆርጅ፤ የፋይንደር የግል ፋይናንስ ተጠባቢ፤ ይህን እንደ እርስዎ ቅንጭብ የአውስትራሊያ ክሬዲት ታሪክ አድርገው ያስቡ፤

“የእርስዎ ክሬዲት ደረጃ ከ 0 እስከ 1000 ያለ ጠቅላላ ቁጥር ነው፤ እናም ለአበዳሪዎች የእርስዎን ብድር ኃላፊነት በተመላው ሁኔታ የመወጣት አቅም አንፃራዊ መለኪያ ይሰጣቸዋል” ሲሉ ያስረዳሉ።
ዝቅተኛ ክሬዲት ደረጃ ማለት ለአበዳሪዎች ከፍ ያለ ተጋላጭነት አለው ማለት ነውና የወለድ መጠኑን ከፍ ያደርጋሉ
ኤሚ ብራድኒ-ጆርጅ
ባለፉት ጊዜያት የብድር ካርዶች ወይም ብድሮች ክፍያዎችን ሳይከፍሉ አስተጓጉለው ከሆነ የክሬዲት ደረጃዎ ዝቅ ይላል።

በአንድ ጊዜ ለተለያዩ አበዳሪዎች ማመልከት ምንም እንኳ አጓጊ ቢሆንም፤ የፋይናንስ ሁከት ላይ እንዳሉ ስለሚያመላክት የከሬዲት ደረጃዎን ዝቅ ያደርግብዎታል።
Caucasian woman examining sports car for sale in dealership
Credit: Jacobs Stock Photography Ltd/Getty Images

ምን ዓይነት የግል ብድሮች አሉ?

የአበዳሪዎችን የወለድ መጠኖች፣ ክፍያዎች፣ መሥፈሮችና የብድር ውሎችን በመመርመር ይጀምሩ።

የ መኒስማርት ድረ ገፅ ላይ ይገኛል።

እንደ ባንኮችና ተባባሪ የፋይናንስ ተቋሞች የተለያዩ የግል ብድሮችን በተፎካካሪ የወለድ መጠኖች ያበድራሉ።

“ባንኮችና የትብብር ፋይናንስ ተቋሞች ተበዳሪ ከአቅም በላይ ለሆነ ብድር እንዳይጋለጥ ለማረጋገጥ ኃላፊነት በተመላው የብድር ሥርዓተ ደንቦች የሚተዳደሩ ናቸው”

“ባንክ ያልሆኑ አበዳሪዎች የግል ብድር ያበድራሉ፤ በጥቅሉ የብድር ግምገማ መሥፈርቶቻቸው ከባንኮች ላላ ያለ ነው። ይሁንና ለብድሩ ከፍተኛ የወለድ መጠኖች ወይም ክፍያዎችን መክፈልን ከግምት ውስጥ ያስገቡ” ሲሉ የአበዳሪ ቅርስና የሕዝብ ምርጫ ተጠሪ ፖል ፋርመር ያስረዳሉ።

ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ሁለት ዋነኛ የግል ብድር ዓይነቶች አሉ፤ ባለ ዋስትናና ዋስትና የለሽ።
  • ባለ ዋስትና ብድሮች እንደ መኪና ያለ ትልቅ ንብረት ለመግዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው። አበዳሪዎ የብድር ግዴታዎን ካልተወጡ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የእርስዎን ንብረት እንደ መተማመኛ ወይም ዋስትና ይጠቀምበታል። ክፍያዎን ካልተወጡ ንብረትዎን መልሶ ይወስደዋል። በጥቅሉ ባለ ዋስትና ብድሮች ቋሚ የወለድ መጠኖች አላቸው።
  • ዋስትና የለሽ ብድሮች የንብረት ዋስትናን ግድ አይሉም፤ እናም በአጠቃላይ የወለድ መጠናቸው ከፍተኛ ነው።
አቶ ፋርመር “አበዳሪው ሊበደሩ የሚችሉትን መጠን ይወስናል”

“አጠቃላይ የብድር መጠኑም ከ $2,000 እስከ $20,000 ነው” ይላሉ።

ለብድር ማመልከት

ብድርዎን መልሶ በመክፈል አቅምዎ የሚተማመኑ ከሆነ፤ ሰነዶችዎን አያይዘው የእርስዎ ምርጫ ከሆነ አበዳሪ ዘንድ በኦንላይን ማመልከት ይችላሉ።

የማመልከቻ ተቀባይነት አለማግኘት ያልተለመደ ነገር አይደለም።

አበዳሪዎ ማመልከቻዎን በሚመረመርበት ወቅት ገቢዎ ከፍያዎን ለማሟላት በቂ አይደለም ብሎ ሊወስን እንደሚችል ወ/ሮ ብራድኒ-ጆርጅ ሲያስጠነቅቁ፤

“ከገቢዎ ጋር የተሳሰረ ነው፤ አስተማማኝ ያልሆነ ሥራ ላይ ተሠማርተው ያሉ ከሆነ ወይም ለረጅም ጊዜ የሥራ ገበታ ላይ ተሠማርተው ያልቆዩ ከሆነ፤ ማመለከቻዎን ውድቅ ለማድረግ እኒህን ሁነቶች ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ ይችላሉ” ይላሉ።
Businessman giving money, Australian dollar bills, to his partner
You can always discuss financial hardship options with your lender if times get tough. Source: iStockphoto / Atstock Productions/Getty Images/iStockphoto

መልሰው መክፈል ከተሳነዎትስ?

አዘግይቶ መክፈል ተጨማሪ ክፍያዎችን ያስከትላል።

የፋይናንስ ሁኔታዎ ከተለወጠና እራስዎን አዋኪ ሁኔታ ውስጥ ፈልገው ካገኙ፤ ከአበዳሪዎ ጋር ስለ አዋኪ የፋይናንስ ሁኔታ አማራጮች መወያየት ጠቃሚ ነው።

እንዲሁም፤ ወደ በ 1800 007 007 በመደወል ከነፃ የፋናንስ አማካሪ ጋር መነጋገር ይችላሉ። .

በእርስዎ ፈንታ ወደ እርዳታ መስመር ሊደውሉልዎት ይችላል።

ከመታለል ይጠንቀቁ

“የግል ብድርን አስመልክቶ የሚያነጋግርዎ ከገጠምዎ፤ የኩባንያውን ወይም እያነጋገርዎት ያለውን ሰው እውነተኛ ማረጋገጫ ያጣሩ”

“ወዲያውኑ ከማናቸውም ስምምነት ላይ አይድረሱ። ሁሌም ተገቢውን ምርመራ ያድርጉ፤ ጥርጣሬ ካለዎት እርዳታን ይጠይቁ” ሲሉ የመኒስማርት ተጠሪው አንድሩ ዳድስዌል ይመክራሉ።

ጭብርብሮችን በመለየት ሊረዳዎና ዒላማ ከሆኑም ምክርን በመለገስ ያግዝዎታል።

Share