አንኳሮች
- ሻርኮች የባሕር ሥነ ምሕዳርን ሚዛን አስጠብቆ ለማቆየት ወሳኝ ሚና ያላቸው ብርቱ አዳኞች ናቸው
- የባሕር ዳርቻ ጥንቃቄ መመሪያዎችን መከተልና ተዘዋዋሪ ጥበቃ በሚካሔድባቸው የባሕር ዳርቻዎች መዋኘት ለሻርክ የመጋለጥ አደጋን መቀነስ ያስችላል
- ውኃ ውስጥ ከሻርክ ጋር መጋፈጥ አስፈሪ ተሞክሮ ነው፤ ይሁንና ተረጋግቶ በዝግታ መራቅ አስፈላጊ ነው
የአውስትራሊያ ሥነ ምሕዳር እንደ ታላቁ ነጭ ሻርክ፣ ነብር ሻርክ፣ መዶሻ ራስ ሻርክ፣ በሬ ሻርክና የተለያዩ የባሕር ወለል ሻርኮችን በማቀፍ የበለፀገ ነው።
እኒህ ፍጡራን አደገኛ አዳኞችና ሙት በላተኞች ቢሆኑም፤ የባሕር ጤናና ሚዛንን አስጠብቀው ያቆያሉ።
ዶ/ር ፖል ባቸር እንደ ሻርክ ሳይንቲስትነታቸው፤ ስለ ሻርኮችና ባሕሪያቸው ማለፊያ ግንዛቤና አረዳድ መኖር ከሻርክ ጋር የመጋፈጥ ተጋላጭነትን ለመቀንስ እንደሚያስችል ሲያስረዱ፤
“ሻርኮች ቀዳሚ የባሕር ምግብ ሰንሰለት ላይ ያሉ ናቸው። የታዳኝ ዝርያዎችን ቁጥር በመቆጣጠር ያግዛሉ፣ የተወሰኑ ከባሕር ወለል በታች ነዋሪ ፍጡራንን ከመጠን በላይ እንዳይበዙ ቅድመ መከላከል በማድረግና ብዝሃነትን ጠብቆ በማቆየት፤ በተዘዋዋሪም መላው የምግብ ድር ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ” ይላሉ።
የሻርክ ባሕሪይን መረዳት
እንደ ዋና ተመራማሪነት ሚና፤ የዶ/ር ቡቸር ምርምር የሚያተኩረው ወደ ባሕር ዳርቻ የሚሔዱቱ ከሻርክ ጋር የመጋፈጥ አደጋን ለመቀነስ ሳይንስን መሠረት ያደረገ የተሻለ የጥበቃ ፕሮግራም በማቅረብ ላይ ነው።
እኒህ ፍጡራንን ለውቅያኖሶቻችንና በጥቅሉ የተፈጥሯዊ አካባቢን ጤና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ላላቸው ጠቀሜታ ዕውቅናን መቸር ጠቃሚ ነው። ከአስፈሪ ገፅታቸው ባሻገር፤ ሻርኮች የእኛ ከበሬታና ጥበቃ የሚገባቸው እውነተኛ ድንቅ እንሰሳት ናቸው።ዶ/ር ፖል ባቸር

A shark seen from the Surf Life Saving aerial surveillance helicopter – Image: Surf Life Saving Australia.
አክለውም “ሻርኮች የኒው ሳውዝ ዌይልስ ውኃ ውስጥ ዓመቱን ሙሉ ይገኛሉ። ነጭ ሻርኮች መጠነ ሰፊ በሆነ የባሕር ወለል የሙቀት መጠን፣ የበሬ ሻርኮች የውኃው መጠን ከ20 ዲግሪዎች በላይ ሲሆን ይገኛሉ። ነጭ ሻርኮች በአብዛኛው ከባሕር ዳርቻዎቻችን በኪሎ ሜትር ርቀት ረፋዱ ላይ ከ11 am ግድም አንስቶ እስከ ከሰዓት በኋላና ከእኩለ ቀን እስከ ምሽት ይገኛሉ” ብለዋል።
ዶ/ር ባቸር የሻርክ አደጋን ለመቀነስ፤ ልንከተላቸው የሚገቡ ጥቂት ጠቃሚ የባሕር ዳርቻ የጥንቃቄ መመሪያዎች እንዳሉ ይናገራሉ።
ተዘዋዋሪ ጥበቃ በሚደረግባቸው የባሕር ዳርቻዎችና በባንዲራዎች መካከል ብቻ ይዋኙ፤ ምክንያቱም የባሕር ዳር ሕይወት ታዳጊዎችና ሕይወት ጠባቂዎች ባሕር ዳርቻዎችንና የውኃ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም የሁሉንም የባሕር ዳርቻ ተጓዦች ጥንቃቄን ከፍ ለማድረግ እዚያ ይገኛሉና። ብቻዎን ሳሉ ወይም በርካታ የማጥመጃ አሳዎችና ቁልቁል በራሪ ወፎች ባሉበት ወቅት ቀዘፋን ያስወግዱ።ዶ/ር ፖል ባቸር

Dr Paul Butcher – Image: New South Wales Department of Primary Industries.
የባሕር ዳርቻ ጥንቃቄ
ዶ/ር ጃዝ ሎዊስ ኢኮሎጂስትና የባሕር ዳርቻ ጥንቃቄ ተመራማሪና የ ምርምር ቡድን መሪ፤ የባሕር ዳርቻ ጥንቃቄ ሌላ ገፅታዎች እንዳሉት ያስረዳሉ።
በሻርክ የመነከስ አደጋን ለመቀነስ ማለፊያው ምክር ጀምበር መጥለቂያ ላይ፣ በምሽት ወይም ጎሕ ሳይቀድ በፊት መዋኘትን ያስወግዱ ነው። እንዲሁም፤ ብቻዎን መዋኘትን ለማስወገድ ከጓደኛዎ ጋር ይዋኙ ስንል ምክረ ሃሳባችንን እንቸራለን።ዶ/ር ጃዝ ሎዊስ
ውቅያኖስ ውስጥ ሳሉ ሻርክ ቢቀርብዎ፤ ረግቶ መቆየት አስፈላጊ ነው።
ዶ/ር ፖል ባቸር “እንደ ሁኔታው፤ የሻርክ ባሕሪይን በማጤን ምላሽ ማድረግ ይችላሉ። ቅብጥብጥነት ወይም ቁጣ፣ ፍጥነት ማሳየት፣ የተዛቡ እንቅስቃሴዎች ወይም የነውጥ ባሕሪ ካሳየ፤ በተቻለ መጠን ውኃውን በእርጋታ ግና በፍጥነት ለቅቀው ይውጡ። ማንቦራጨቅና ድምፅ መፍጠርን ለመቀነስ ይሞክሩ፤ ሻርክን በጭራሽ አይፈታተኑ” ብለዋል።
በማያያዝም፤ የሻርክ ጥቃቶች የሚደርሱት በጣም ውስን በሆኑ ጊዜያት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፤ ይሁንና ዝግጁ መሆንና እንደምን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ማወቅ ብልህነት ነውም ይላሉ።

Lifesavers on patrol at the beach – Image: Surf Life Saving Australia.
እንዲሁም፤ ሻርክን የመግቻ የግል ቁሶች አሉ፤ ይሁንና ዶ/ር ቡቸር ምርቶቹ ከሻርኮች ጋር የሚኖረውን መቀራረብ ይቀንሱታል እንጂ 100% ፍቱን እንዳልሆኑ ይናገራሉ።
አውስትራሊያ ወደ ባሕር ዳርቻ ሐጂዎችን የሚታደግ፤ የቀዘፋ ሕይወት አዳኞችና የሕይወት ጠባቂዎችን ያቀፈ አገር አቀፍ የቀዘፋ ሕይወት አድን አውስትራሊያ አውታረ መረብ ያላት በመሆኑ ዕድለኛ ናት።
“የቀዘፋ ሕይወት አዳኞችና ሕይወት ጠባቂዎች ከባሕር ዳርቻ ሆነው ሻርኮችን በአጉሊ መነፅሮች ክትትል ያደርጋሉ፤ የተወሰኑትም እንደ ድሮኖች ወይም ሔሊኮፕተሮችን የመሰሉ ልዩ የቅኝት ቴክኒኮችን ይጠቀማሉ። ሻርክን ከተመለከቱም የአደጋ ማንቂያ ድምፅ ወይም ደወል ያሰማሉ፤ ቀይና ነጭ ባንዲራዎችን በማውለብለብም ከውኃ ውስጥ በፍጥነት እንዲወጡ ይጠይቅዎታል” ሲሉም ያስረዳሉ።

Impact ecologist and beach safety researcher Dr Jaz Lawes from Surf Life Saving Australia – Image: Surf Life Saving Australia.
ምርምርና ጥበቃ
የተወሰኑ የአውስትራሊያ ክፍለ አገርና ግዛት መንግሥታት የሻርክ መለያ በማያያዝ፣ ፕሮግራሞችን በመቆጣጠር፣ የሻርክ መረብን በመዘርጋት፣ ድሮኖችንና ሔሊኮፕተሮችን ለአየር ቅኝት በመጠቀም የሻርክ አደጋዎችን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስትራቴጂዎች አሏቸው።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት ሻርክ አካል ላይ ተያያዥ የመቆጣጠሪያ ፕሮግራም በማያያዝ ከዓለም በትልቅነቱ ቀዳሚ ሥፍራ ይዟል። ያም ማለት አካሉ ላይ የመቆጣጣሪያ ቁስ የተያያዘበት ሻርክ ወደ አካባቢው ሲቃረብ ወደ ባሕር ዳርቻ ተጓዦች አሁናዊ ማስጠንቀቂያዎችን ያገኛሉ ማለት ነው ሲሉ ዶ/ር ባቸር ይናገራሉ።
“የማዳመጫና መለያ ሻርኮች ላይ የሚያያዘው በእኛ ተቋራጮች ነው። ሁሉም የማዳመጫ መለያዎች የተያያዙባቸው ሻርኮች በኒው ሳውዝ ዌይልስ ባሕር ጠረፍ ባሉ 37 አሁናዊ የሻርክ ማዳመጫ አውታረ መረብ ጣቢያዎች የት እንዳሉ ተለይተው ይደመጣሉ"
አንድ ሻርክ የማዳመጫ ጣቢያዎች ከአሉበት 500 ሜሮች አካባቢ ሲዋኝ ቅፅበታዊ ማስጠንቀቂያ ወደ ይላካል። ን ጨምሮ በሌሎች ክፍለ አገራትም በተመሳሳይ መልኩ አሉ።
ዶ/ር ባቸር፤ ሻርክ ጥበቃ አስፈላጊ ነው፤ መጠንቀቅ እንጂ አለመደናገጥንና እኒህ የባሕር ውስጥ አደገኛ አዳኞች ከበሬታን ማሳየትን አለመዘንጋት ወሳኝ እንደሆነ ያሳስባሉ።
“ሻርኮች በመላው ዓለም የሰዎችን ምናብ፤ በተለይም ነባር ዜጎችን ለሺህ ዓመታት ማርከው ይዘው ቆይተዋል። ይህ ማራኪነት ለግንዛቤ ከፍ ማለት አስተዋፅፆ አድርጓል፤ እንዲሁም የባሕር ጥበቃ ፍላጎትን አሳድሯል። ያም ጠቃሚ ነው” ብለዋል።

It is crucial to be prepared and know how to respond in case of a shark encounter in the water. Source: Moment RF / Khaichuin Sim/Getty Images
በባሕር ዳርቻ ሲዋኙ ደህንነትን ጠብቆ የመቆየት ዋነኛ ጥቆማዎች፤
- ተዘዋዋሪ ጥበቃ በሚደረግባቸው የባሕር ዳርቻዎች በቀይና ቢጫ ባንዲራዎች መካከል ይዋኙ
- ልጆች ውኃ ውስጥና በውኃ ዙሪያ ሳሉ ያለማቋረጥ ይቆጣጠሩ
- ከመቆረጥ ወይም ከመቁሰል የደም መፍሰስ ሲገጥምዎ ከውኃ ውስጥ ይውጡ
- ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆኖ መዋኘት፣ መጥለቅ ወይም መቅዘፍ የተሻለ ነው
- በውኃ አካባቢ ሳሉ አልኮል አይጠጡ ወይም አደንዛዥ ዕፆችን አይጠቀሙ
- ከቀዘፋ ሕይወት አዳኞች ወይም ሕይወት ታዳጊዎች ምክርን ይጠይቁ
- የማጥመጃ አሳዎች መኖራቸውን ከሚያመላክት አካባቢ ወይም የአሳ ምገባ እንቅስቃሴዎች ያሉባቸውን አካባቢዎች ያስወግዱ፤ ጠላቂ የባሕር ወፎች የአሳ እንቅስቃሴ ስለመኖሩ ጥሩ ጠቋሚዎች ናቸው
- ዶልፊኖች የሻርኮችን አለመኖር አያመላክቱም፤ በአብዛኛው ሁለቱም ተመሳሳይ ምግብ ይመገባሉ፤ ሻርኮች ዶልፊኖችን እንደሚበሉ ይታወቃል
- የግል መከላከያ መጠቀምን ከግምት ውስጥ ያስገቡ
- ውስንነቶችንና ሁኔታዎችን ይወቁ
- የአካባቢዎን በማነጋገር በጎ ፈቃደኛ ይሁኑ
- ይጎብኙ ወይም የበለጠ ለመረዳት ን ይጫኑ