በቤትዎ ከእሳት አደጋ ይጠበቁ ፤ በአውስትራሊያ ህይወትን ከሚያጠፉ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዴት መከላከል ይቻላል

Brave Fireman of a Burning Building and Holds Saved boy in His Arms. Open fire and one Firefighter in the Background.

Did you know that most preventable fire fatalities in Australia have occurred in owner-occupied houses? Getty Images/Virojt Changyencham Source: Moment RF / Virojt Changyencham/Getty Images

የቤት ውስጥ እሳት አደጋን መከላከል የጭስ ማስጠንቀቂያ ደወሎችን ( አላርሞች ) በመኖራችው ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ከዚያም በላይ መሄድን ይጠይቃል ። በአውስትራሊያ ህይወትን የሚያሳጡ እሳት አደጋዎች የተለመዱ ናቸው ። ከቤትዎ ሊከሰት የሚችለውን እንዴት ማቆም እንደሚችሉ ማወቅ ይኖርብዎታል።


አንኳሮች
  • የማሞቂያ ቁሳቁሶች እና ጭስ በአብዛኛው ከእሳት አደጋ ጋር የተገናኙ ናቸው ፤ ነገር ግን የቤት ውስጥ እሳት በማናቸውም የሙቀት ምንጮች ሊከሰት ይችላል
  • በቤት ውስጥ ተቀጣጣይ በሆኑ ቁሳቁሶች ዙሪያ የተለየ ትኩረትን ማድረግ እሳትን ለመከላከል ቁልፍ አማራጭ ነው ፤
  • ህጻናት በቤት ውስጥ የእሳት አደጋ ጥንቃቄ ፤ መከላከልን እና በአደጋ ጊዜ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል
አብዛኛውን ጊዜ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሆኖ የእሳት አደጋ ይከሰታል ብሎ ማሰብ በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ የሚታሰብ አይደለም ። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ሊከላከሏቸው የሚችሉ ቢሆኑም ፤ የሚያደርሱት አደጋ ግን አሳዛኝ እና የማይተኩ ውድመቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

አደጋዎችን እና የመከላከያ መንገዶችን ማወቅ ማለት በሞት እና በህይወት መካከል ያለ ልዩነት እንደማለት ነው ።

በ2019 አም በተሰራው ጣምራ ጥናት መሰረትም , በአውስትራሊያ በተፈጥሮ አደጋዎች ማለትም በጎርፍ ፤ አውሎነፋስ እና የጫካ እሳት ከሚሞቱት ሰዎች ይበልጥ በቤት ውስጥ የእሳት አደጋ ህይወታቸው የሚያልፈው ይበልጣል።

“ ከ 2003 እስከ 2017 ባሉት አመታት 900 ያህል ሰዎች ሊከላከሉት በሚቻል የቤት ውስጥ የእሳት አደጋ ህይወታቸው አልፏል። ” የሚሉት አንድሪው ጊሲንግ የአውስትራሊያ የተፈጥሮ አደጋዎች ምርምር ዋና ሀላፊ እና የምርምሩ ጥናት ተባባሪ ጸሀፊ ናቸው ።

Boy pouring methylated spirit on barbecue fire
Residential fires can happen any time of the year. Contributing factors leading to preventable fires include an individual’s behaviour and their surrounding environment. Getty Images/Robert Niedring Credit: Robert Niedring/Getty Images/Cavan Images RF/Getty Images
አቶ ጊሲንግ ሲያብራሩም “የምርምሩ ቁልፍ ነጥቦች እንዳመላከቱት ለአደጋዎቹ በዋነኛነት የሚጠቀስ አንድ ምክንያት ብቻ አለመኖሩን ነው ።”

“ ሊከላከሉት በሚቻል አሳዛኝ በሆነ የቤት ውስጥ የእሳት አደጋ ተጠቁዎች የሆኑትን ስንመለከት ፤ እንደ የግል ባህሪያቸው እና የመኖሪያ ቤቱ ሁኔታ አብዛኛውን ጊዜ አብረው የሚከሰቱ የተለያዩ ምክንያቶች በዙሪያቸው እንዳሉ ነው ።”

አያይዘውም ሲገልጹ “ ሊከላከሏቸው የሚቻል የቤት ውስጥ የእሳት አደጋዎች በአብዛኛው የሚነሱት ፤ በሲጋራ ፤ በተበላሹ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ፤ በማሞቂያዎች እና ግልጽ በሆነ ቦታ በሚነዱ እሳቶች አማካኝነት ነው ። ”

LISTEN TO MORE FROM THE SETTLEMENT GUIDE
SG FIRE AND EMERGENCY 2 image

What are Australia’s Emergency Warnings and Fire Danger Ratings and how should you respond?

SBS English

11:31
መሰረታዊ የሆኑ የእሳት አደጋ መከላከያ ዘዴዎች ሲባልም፤ አገልግሎቱ ያልተቋረጠ የቤት ውስጥ ማንቂያ ( አላርም) ከእሳት እንዴት ማምለጥ እንደሚቻል የሚያስረዳ እቅድ እና በሚያበስሉ ጊዜ ሳይጨርሱ ጥሎ አለመሄድ የሚሉትን ያካትታል ።

ነገር ግን እሳት አደጋን መከላከል የሚጀምረው ፤ የሙቀት ምንጮችን ለይቶ ከማወቅ እና ፈጥኖ ምላሽ መስጠት ከሚለው ነው ሲሉ በኩዊንስላንድ የእሳት አደጋ እና ድንገተኛ አገልግሎት የእሳት አደጋ መከላከያ ዋና ሀላፊ ማርክ ሃልቨርሰን ይናገራሉ።

new alarm for senior woman
All Australian states and territories have their own specific smoke alarm requirements. Authorities urge everyone to replace smoke alarm batteries annually. Getty Images/sturti. Credit: sturti/Getty Images
“ እሳት እንዲቀሰቀስ በቅድሚያ ሙቀት መኖር አለበት ፤ይህ ሙቀት ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ቁሳቁሶች በእሳት እንዲያያዙ በቀላሉ ያደርጋል ፤ ”ይላሉ አቶ ሃልቨርሰን

ይህ የሙቀት ምንጭ ከየትኛውም ስፍራ ማለትም ከቤት ውስጥ ማሞቂያ ፤ ከማብሰያ ቁሳቁሶች እና ያለአግባቡ እና ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ በተሞሉ ( ቻርጅ በተደረጉ) ባትሪዎች ጭምር ሊሆን ይችላል ። ”

Smoke coming out from oven
Smoke coming out from oven Credit: Henrik Sorensen/Getty Images

ተቀጣጣይነትን መከላከል

የጥናት ምርምሮች እንደሚያሳዩት ከሆነ ህይወትን የሚያሳጡ አብዛኛዎቹ የእስት አደጋዎች የሚከሰቱት በብርድ ወራት ሲሆን ይህውም ደህንነታቸው ባልተጠበቀ የማሞቂያ ቁሳቁሶች እና ዘዴዎች አማካኝነት ነው ።

“ ሊከላከሏቸው በሚቻል የመኖሪያ ቤት የእሳት አደጋዎች የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚጨምረው በክረምት ወራት ሲሆን የሚከሰቱትም በማሞቂያዎች እና ግልጽ በሆነ ቦታ በሚነዱ እሳቶች አማካኝነት ነው ። ” ሲሉ አቶ ጊሲንግ ተናግረዋል ።

የእሳት አደጋ ባለስልጣናት የማሞቂያ ቁሳቁሶች አምራች ድርጅቶቹ በሚያስቀምጡት የአጠቃቅም መመሪያ መሰረት እንድንጠቀም ያበራታታሉ ፤ ይህም ማለት ከቤት ውጭ ለማብሰያነት የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በቤት ውስጥ አለመጠቀም ፤ እንደ ፈሳሽ ፔትሮልየም ጋዝን እንደ ሀይል ምንጭ አለመጠቀም የሚሉትን ያካትታል ።

ከቤት ውጭ አገልግሎት ተብለው የተሰሩ የማሞቂያ ቁሳቁሶች ለቤት ውስጥ አገልግሎት በፍጹም የሚሆኑ አይደሉም ፤በተያያዥም ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድን እንዲከማች በማድረግ ወደ ኢታኖል ሊቀየሩ ይችላሉ ።

MORE FROM THE SETTLEMENT GUIDE
SG Calling an Ambulance Podcast image

How to call an ambulance anywhere in Australia

SBS English

09:50
በአውስትራሊያ በቅርብ አመታት በቤት ውስጥ የሚከስቱ የእሳት አደጋዎች ቁጥር በከፍተኛ ደርጃ ጨምሯል ፤ ለዚህም ሰበቡ የሊቲየም አዮን ባትሪዎች ሲሆኑ በተለይም ኢ- ስኩተሮች ጥልቅ የሆነ ሀይል (ኢነርጂ) ስለሚጠቀሙ አደጋውን አባብሰውታል።

“ ምክንያቱም የኢ - ስኩተሮች ባትሪ በርካታ ሀይልን አከማችቶ ስለሚይዝ ፤ እሳት በሚነሳ ጊዜ ከሚጠበቀው በላይ ሀይል ይኖራል ፤ በተያያዥም በፍጥነት ለመሰራጨት ከፍተኛ የሆነ እድል ይኖረዋል ። ” ሲሉ አቶ ሃርቨርሰን ይናገራሉ ።


እንደ የክልል ዲፓርትመንት አሀዛዊ መረጃ ከሆነም ባለፉት 18 ወራት ከተከሰቱት ከ450 በላይ የሚሆኑ የእሳት አደጋዎች ከሊቲየም አዮን ባትሪዎች ጋር የተያያዙ ናቸው ።

“ የችግሩ ቁጥር አንድ መንሳኤም ሰዎች ትክክለኛ ያልሆኑ ቻርጀሮችን በመጠቀም ሳቢያ ነው ሲሉ አቶ ሃርቨርሰን ያስጠነቅቃሉ ። ”

የባትሪ ቻርጀሮች ከምንጠቀምባቸው መሳሪዎች ጋር ስለተገናኙ ብቻ ትክክለኛ ቻርጀሮች ናቸው ማለት አይደለም
ማርክ ሃልቨርሰን በኩዊንስላንድ የእሳት አደጋ እና ድንገተኛ አገልግሎት የእሳት አደጋ መከላከያ ዋና ሀላፊ
On Fire Adapter Smart Phone Charger At Plug In Power Outlet At Black Background
From mobile phones and toothbrushes to larger items, such as vacuum cleaners and laptops, many household rechargeable devices run on lithium-ion batteries. Getty Images/Chonticha Vatpongpee / EyeEm Credit: Chonticha Vatpongpee / EyeEm/Getty Images
ተቀጣጣይ እና ነዳጅ ቁሳቁሶች በአብዛኛው የሚገኙት በብዙዎቻችን አጥር ጊቢ እና ጓሮ አካባቢ ነው ፡፡ የደረቁ እንጨቶች እና ጣውላዎችን ፤ ልብሶችና በቀላሉ በእሳት ሊያያዙ የሚችሉ ቁሳቁሶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሌቀመጡ ይገባል ። ሌሎች አደጋኛ ምርቶች እና ኬሚካሎች ፤ የጽዳት መጠቀሚያዎች እና ቀለሞች በአብዛኛው በመኖሪያ ቤት በሚገኙ መጋዘኖች (ሼድ) የሚቀመጡ ናቸው ።

አቶ ሃልቨርሰን እንደሚሉት በመኖሪያ ቤት ነዳጅን ማስቀመጥ የሚፈልጉ ሰዎች (እንደ ለሳር ማጨጃ ማሽን ወይም ለመኪና ጋዝ ) ትክክለኛ በሆነ ማስቀመጫ ጀሪካን መቀመጡን ልብ ማለት ያስፈልጋል፤ እንዲሁም ከሌሎች ቁሳቁሶች ጋር አለማስቀመጥ እና ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ወይም ቀጥታ ከሆነ የጸሀይ ሙቀት መከላከል ያስፈልጋል ።

“ እንደ ጋዝ ያሉ ነዳጆች እና ማዳበሪያ በምንም አይነት በአንድ ስፍራ መቀመጥ የለባቸውም ።” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ ።

“ በመኖሪያ ቤታችን ደህንነታችን ከእሳት ተጠብቆ እንዲኖር በዋነኛነት ማድረግ ያለብን የተለያዩ ኬሚካሎችን በሚገባ ለያይቶ ማስቀመጥ አለብን ። ”
Household hazardous waste products and containers
Careless use or storage of flammable products at home can easily start a fire. Getty Images/NoDerog Credit: NoDerog/Getty Images
ተቀጣጣይ እና ነዳጅ ቁሳቁሶች በአብዛኛው የሚገኙት በብዙዎቻችን አጥር ጊቢ እና ጓሮ አካባቢ ነው ፡፡ የደረቁ እንጨቶች እና ጣውላዎችን ፤ ልብሶችና በቀላሉ በእሳት ሊያያዙ የሚችሉ ቁሳቁሶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሌቀመጡ ይገባል ። ሌሎች አደጋኛ ምርቶች እና ኬሚካሎች ፤ የጽዳት መጠቀሚያዎች እና ቀለሞች በአብዛኛው በመኖሪያ ቤት በሚገኙ መጋዘኖች (ሼድ) የሚቀመጡ ናቸው ።

አቶ ሃልቨርሰን እንደሚሉት በመኖሪያ ቤት ነዳጅን ማስቀመጥ የሚፈልጉ ሰዎች (እንደ ለሳር ማጨጃ ማሽን ወይም ለመኪና ጋዝ ) ትክክለኛ በሆነ ማስቀመጫ ጀሪካን መቀመጡን ልብ ማለት ያስፈልጋል፤ እንዲሁም ከሌሎች ቁሳቁሶች ጋር አለማስቀመጥ እና ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ወይም ቀጥታ ከሆነ የጸሀይ ሙቀት መከላከል ያስፈልጋል ።

“ እንደ ጋዝ ያሉ ነዳጆች እና ማዳበሪያ በምንም አይነት በአንድ ስፍራ መቀመጥ የለባቸውም ።” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ ።

“ በመኖሪያ ቤታችን ደህንነታችን ከእሳት ተጠብቆ እንዲኖር በዋነኛነት ማድረግ ያለብን የተለያዩ ኬሚካሎችን በሚገባ ለያይቶ ማስቀመጥ አለብን ። ”
Man using fire extinguisher on arm chair on fire
It is not advisable to extinguish a fire on your own, unless the fire is localised, and you know how to use the right equipment. Getty Images/Michael Blann Credit: Michael Blann/Getty Images

ህጻናት እና የእሳት አደጋ መከላከያ

እድሜያቸው ከ 65 አመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች እና ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት በእሳት አደጋ ለሚደርስ መቁሰል የተጋለጡ ናቸው ።
ህጻናት በአብዛኛው ለእሳት ቃጠሎ የተጋለጡ ሲሆኑ ፤ አነስተኛ እና በቀላሉ ሊጠፉ የሚችሉ የእሳት አደጋዎች በህጻናት ላይ ከባድ ቃጠሎን እና መቁሰልን ሊያስከትሉባቸው ይችላሉ ሲሉ በሲድኒ የህጻናት ሆስፒታል የህጻናት ጤና ትምህርት ክፍል ሃላፊ ይናገራሉ ።
“ ቆዳቸው ከአዋቂዎች ጋር ሲነጻጸ በጣም የሳሳ ነው ፤ ስለሆነም አነስተኛ የሆነ ሙቀት ቆዳቸውን አልፎ የውስጠኛ አካላቸው በፍጥነት ሊያቃጥል ይችላል ። ”
Little girl turns the oven button
Children are naturally quite curious, so heat-related accidents can happen in seconds if a child is left unattended in the kitchen. Getty Images/tolgart Credit: tolgart/Getty Images
ህጻናትን የእሳት አደጋ ጥንቃቄዎችን በቤት ውስጥ ማስተማር እና ሶስት ዜሮዎችን 000 መደወልን ከማስተማር ከፍ ባለ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየት ግድ ይላል። .

“ የመጀመሪያው ክቤት ውስጥ የእሳት አደጋ እንዴት ማምለጥ እንደሚቻል የሚያስችል እቅድ ሲሆን ፤ ይህንንም ከቤተሰብ ጋር መለማመድ ያስፈልጋል ። “ ይላሉ ወ /ሪት ሱሊቫን
“ በተቻለ መጠን ቀላል እና አዝናኝ ፤ ልጆቹንም የሚያሳትፍ አድርጉት ፤ እንዲሁም በተግባር የሚውሉ እንቅስቃሴዎችንም ለማከል ሞክሩ ፡፡ ”
ወ/ሪት ሱሊቫን አያይዘውም ለህጻናት ቀልብን በሚስቡ እና በማይረሱ ቃላት ማስተማር መልካም ነው ሲሉ ምክራቸውን ይለግሳሉ። “

በእሳት አደጋ ጊዜ ከታች ወደ መሬት ያለው አየር ቀዝቀዝ ያለ እና ንጹህ ስለሆነ ፤ ጎንበስ ብላችሁ ሂዱ፤ ሂዲ፤ ሂዱ በማለት በማይረሷቸው ቃላት አስተምሩቸው ። ”

ልብሳቸውም ድንገት በእሳት ከተያያዘ ቁሙ፤ ጣሉ ፤ተሸፈኑ፤ ከዚያም ተሽከርከሩ ። ”

መሬት ላይ በመቀመጥ ፊት ላይ ሊመጣ የሚችላውን የእሳት ነበልባል መከላከል ይቻላል ፤ፊትን በእጅ መሸፈን ሊከሰት የሚችን የመቁሳል አደጋን ይከላከላል ። ”

AAP
Ensure that every occupant of the house knows what they need to do in case of fire. Getty Images/Imgorthand Source: AAP
ወ /ሪት ሱሊቫን አያይዘው ከልጆችዎ ጋር ስለ እሳት አደጋ መከላከያ የሚደረገው ውይይት ፍርሀት እንዳይሰማቸው በሚያደርግ እና እውቀቱን በደንብ በሚያሰርጽ መንገድ መሆን አለበት ። ”

የጭስ ማስጠንቀቂያ ደወሎችን ( አላርሞችን ) ጠቀሜታ ፤ የት እንዳሉ ፤ እንዴት እንደሚሰሩ ፤ ምን እንደሚመስሉ ፤ እሳት በሚነሳ ጊዜ እና ባትሪያቸው ሲያልቅ ምን አይነት ድምጽ እንደሚያሰሙ ማስረዳት ያስፈልጋል ፤

“ ይህንንም በማድረግም እሳት በሚኖር ጊዜ እንዳይደነግጡ ይረዳቸዋል ፤ ምክንያቱም የሚፈጠረው ድምጽ ምን አይነት እንደሚሆን በቀላሉ መለየት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ምን ማድረግ እንዳለባቸው በደንብ ያውቃሉ ። ”

በቤት ውስጥ የሚከሰት የእሳት አደጋን ለመከላከል ለወላጆች እና ተንከባካቢዎች የሚረዱ መረጃዎች

  • በእሳት አደጋን ላመከላከል ለልጆች የሚሰጥ እንቅስቃሴን ያካተተ ትምህርት 
  • በእሳት አደጋን ላመከላከል ለልጆች የሚሰጥ ትምህርት  
  • የእሳት ቃጠሎ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ – (Translations available in Nepali, Simplified Chinese, Arabic, Farsi, Hindi, Karen, Punjabi, Samoan, Vietnamese)  

Share