ወሲባዊ ይሁንታን እንደምን ማረጋገጥ ይቻላል?

SG Sexual Consent - YOUNG COUPLE

Although sexual assault is considered a major health and welfare issue in Australia, aspects of seeking, giving and denying sexual consent only became a mandatory element of the Australian National Curriculum from 2023. Source: Moment RF / Habitante Stock/Getty Images

አውስትራሊያ ውስጥ በአካልም ይሁን በኦንላይን ያለ ፈቃደኝነት የሚፈፀም ወሲባዊ ድርጊት የወንጀል ተግባር ነው። በተወሰኑ የአስተዳደር አካባቢዎች በወሲባዊ ጥቃት ወይም አስገድዶ ወሲብ በመፈፀም ተጠርጣሪ ወንጀል ፈፃሚዎች ወሲብ ከመፈፀማቸው በፊት ይሁንታን ስለማግኘታቸው ፍርድ ቤት ቀርበው ማረጋገጥን ግድ ይሰኛሉ። ወሲባዊ ግንኙነትን የፈፀሙት በይሁንታ ስለመሆኑ እንደምን ማረጋገጥ ይችላሉ?


አንኳሮች
  • ማናቸውም ዓይነት ያለ ፍላጎት ወይም በጫና፣ በማጭበርበር ወይም በዛቻ አማካይነት የተፈፀመ ወሲባዊ ድርጊት ወሲባዊ ጥቃት ነው።
  • ወሲባዊ ጥቃት አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ስሜታዊ ሊሆን ይችላል። በአካል ወይም በሚዲያ (እንደ ኦንላይን) የደረሰም ሊሆን ይችላል።
  • በተወሰኑ የአውስትራሊያ አስተዳደር አካባቢዎች የወሲባዊ ይሁንታ ሕጎችን የማጠናከር ትርጓሜ ማናቸውም በወሲባዊ አፈፃፀም ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች ሁሉ የተረጋገጠ ይሁንታ ስለማግኘታቸው እርግጠኞች ይሁኑ ነው።
  • የአውስትራሊያ የትምህርት ሥርዓት የወሲባዊ ይሁንታ ትምህርት አሰጣጥ መርሃ ግብሩን እያሻሻለ ነው። የትምሕ
እንደ የአውስትራሊያ ብሔራዊ የቤት ውስጥ የቤተሰብና ወሲባዊ ጥቃት የምክር አገልግሎት፤ 1800 RESPECT የእርዳታ መስመር በመባል በሚታወቀው የወሲባዊ ጥቃት ትርጓሜ የሚገለጠው "ፍርሃት እንዲያድርብዎት ወይም ምቾት እንዳይሰማዎት" የሚያደርግ ማናቸውም የወሲባዊ ፍፀማ ዓይነት ተደርጎ ነው።

ወሲባዊ አመፅ፤ ወሲባዊ ጥቃት፣ መስመር ያለፈ ወሲባዊ ፍፀማ፣ አስገድዶ ወሲብ መፈፀምንና ወሲባዊ ትንኮሳን ያካትታል። አመፅ የሚለው ቃል በአንድ ግለሰብ ላይ በኦንላይን አማካይነት አካላዊ ባልሆነ ወይም አካላዊ ጥቃትን፣ ስሜታዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳትን በአንድ ግለሰብ ላይ መድረስን የሚገልጥ ነው።

የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮአውስትራሊያ ውስጥ ከአምስት አንዲት ሴት ከ15 ዓመት ዕድሜዋ አንስቶ ወሲባዊ አመፅ የገጠማት ናት።
ወሲባዊ ጥቃት ያለ ይሁንታ የሚፈፀም ግብረ አካላዊ ንኪኪ ነው።

የቪክቶሪያ ፖሊስ ገዲብ አምሳ አለቃ ሞኒክ ኬሊ ይህንን ሲያስረዱ፤

“ያለ እርስዎ ነፃ ስምምነት፣ ይሁንታዎን ሳይቸሩ ከየትኛውም አካላዊ ክፍልዎ ጋር ንኪኪ መፈፀም ነው"

"ሁሌም የግድ አካላዊ ንኪኪ መሆን የለበትም፤ በአንድ ግለሰብ ላይ በተለያዩ መንገዶች የሚፈፀሙ የተለያዩ ወሳባዊ ጥቃቶች አሉ። በልዩ የመቀራረብ ስሜት የተነሱ ምስሎችን ያለ ይሁንታ ለሌሎች ማጋራትን የመሰለ" ይላሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ አላስፈላጊ የሆኑ ዝርዝር 'በአጭር የእጅ ስልክ ወሲባዊ ፅሑፍ' በመሰለ የሚከወን 'ታሪክ ነገራ' በሕግ ዘንድ ለወሲባዊ ጥቃት ትርጓሜ ብቁ ይሆናል።
SG Sexual Consent - STOP
On average, there are 85 sexual assaults reported every day in Australia. 90 per cent of victim-survivors do not report their rape to police. Source: Moment RF / Carol Yepes/Getty Images

ወሲባዊ አመፅና ሕግ

ወሲባዊ አመፅ በብርቱ ወንጀልነት ይወሰዳል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ የተወሰኑ የአውስትራሊያ አስተዳደር አካባቢዎች ወሲባዊ ጥቃት ፈፃሚዎች ወሲብ ከመፈፀማቸው በፊት ይሁንታ ስለማግኘታቸው ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያረጋግጡ ግድ የሚያሰኝ የድንጋጌ ለውጥ አካሂደዋል።

የምርመራ ጋዜጠኛ ጄስ ሂል ‘’ በሚል ርዕስ በባለ ሶስት ክፍል ዘጋቢ ፊልሟ ወሲባዊ ይሁንታን ዳስሳለች።

እያንዳንዱ ግለሰብ ወሲባዊ ግንኙነትን አስመልክቶ ስለሚሰማው ጥሩና መጥፎ ስሜት እርግጠኛ መሆን እንዳለበት ተናግራለች።

አንዴ የቱ ጋ እንደቆሙና ወሰኖችዎን ካወቁ በኋላ፤ ስለ ፍቅረኛዎ ስሜት ይጠይቁ። የወሲብ ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው 'እሺ' እና 'እምቢ' ማለትን መልመድ አለባቸው።

ሂል “የማመቻቸት ጉዳይ ነው ‘ሁለታችንም የምንሻው ነገር ነው? ሁለታችንንም ሊያረካን የሚችል ነውን?’ ይሁንታን በማመቻቸት ረገድ ወደ ወሲባዊ መፈላለግ ሲያመሩ በሂደቱ ውስጥ ጥያቄዎችን መጠየቅ ቀላል ነው” ብላለች።
ሊጠይቋቸው የሚችሉ የተወሰኑቱ ጥያቄዎች ይህን ይመስላሉ ‘እዚህ ጋ ብነካሽ ምንም አይደል? ይህን ወድደሽዋል? ይህን እንዳደርግ ትሺያለሽ? እንዲህ ማድረግ እችላለሁ?’ በጥቅሉ፤ ከዝምታ ተግባርነት ይልቅ ማረጋገጥን የሚያካትት ይሆናል።
ጄስ ሂል፤ የምርመራ ጋዜጠኛና ደራሲ
ወሲባዊ ይሁንታን ማረጋገጥ ማለት ወሲባዊ ግንኙነቱ በሚፈፀምበት ወቅት በስሜት የተመላ፣ ሙሉዕ ፈቃድ መኖሩን ሊያረጋግጡ ይገባል ማለት ነው።

በተወሰኑ አስተዳደሮች፤ ወሲብ ሕጋዊነት የተለበሰ እንዲሆን ወሲባዊ ይሁንታን አግኝቻለሁ ብለው ማሰብዎ ብቻውን በቂ መሆኑ ቀርቷል፤ ደጋግመው በነቃ መልኩ መጠይቅን ግድ ይሰኛሉ።

ወሲባዊ ይሁንታን ማረጋገጥ ሌላኛው ሰው ለወሲባዊ እንቅስቃሴ ተስማምቷል ከሚል ግምት በላይ በጣም የላቀ ይሁንተኛነትን ያካትታል።
SG Sexual Consent - couple enjoying a movie at the cinema
Credit: Flashpop/Getty Images
ወሲባዊ ይሁንታ በቃልም ሆነ ያለ ቃል በነፃ ስሜት የተቸረ ስለ መሆኑንና አለመሆኑን ልብ ማለት ይኖርብዎታል። ምክንያቱም ይሁንታን በማንኛውም ጊዜ መንፈግ ይቻላልና። ፍቅረኛዎ በዝምታ ከተዋጠች ወይም አካላዊ ድንዛዜን ካሳየች ያ የተቃውሞ ምልክት ሊሆን ይችላል።

ሂል “በተወሰኑ አካላዊ ቋንቋ ወይም "አይሆንም" ወይም "አቁም" ባለመባልዎ ይሁንታን እንዳገኙ ማሰብ በቂ አይደለም”

“ፀጥ ብለው ወይም ሰውነታቸው እምቢኝ ብሎ ይሆናል። በወሲባዊ ፍላጎት ወቅት ከሰው ጋር ሆነው ምንም ካላሉ ያ በሙሉ ስሜት የተመላ ይሁንታ ነው ማለት አይደለም። 'እርግጠኛ አይደለሁም' ካሉም ምን ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ አይደሉም ማለት ነውና 'ይህን ማድረግ ትፈልጊያለሽ? የግድ ማድረግ የለብንም በማለት ሊያረጋግጡ ይገባል" ብላለች።
SG Sexual Consent - Problems in the relationship
Couple in a difficult moment Credit: Mixmike/Getty Images
የአውስትራሊያ የሕግ ሥርዓት እንዲሁ የትኛው ወሲባዊ ይሁንታ እንደማይቸር ግልፅ አድርጎ አስቀምጧል።

“ለምሳሌ ያህል፤ በስካር ወይም በሆነ መንገድ ራስን በመሳት ወይም የአዕምሮ ሚዛን ጉዳተኛ፣ ምን እንደሚያደርጉ የማያውቁ ወይም መረዳት የማይችሉ ይሁንታን ለመቸር የማይችሉ ናቸው። ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ከሕግ አኳያ ይሁንታን ለመስጠት የሚችሉ አይደሉም” ሲሉ የሕግ ባለሙያና ደራሲ ብራድሊ ይናገራሉ።

ይሁንና፤ አቶ ብራድሊ ተገድዶ ወሲብ መፈፀምን በተመለከተ ሁነቱ በፍርሃት ወይም በጫና በመነጨ ሁኔታ ይሁንታ ስለመቸሩ የሕግ ሥርዓቱ በተወሰነ መልኩ እንደምን ምላሽ እንደሚሰጥ የተወሰነ ችግር መኖሩን ያመላክታሉ።

“የአንድ ሰው ፈቃደኝነት ጫና፣ ኃይል ወይም ግዴታ አድሮበት እንደሆነ መለየቱ ግርጫማ አካባቢ ነው። በተለይም ከቤተሰብና የቤት ውስጥ አመፅ አኳያ እሾሃማ ጉዳይ ነው።

"ወሲባዊ ግዴታን አክሎ አንድ ግለሰብ በአስገዳጅ ቁጥጥር ስር ባለ ግንኙነት ውስጥ ያለ ከሆነ፤ ምናልባትም ከተግባር አኳያ ንቁ ይሁንታ ተሳታፊ ሊሆን ይችላል። ሌላ ከአደጋ የነፃ አማራጭ የሌላቸው መሆኑን በማመን ወይም የነፃ ፈቃደኝነትን አቅማቸውን አጥተው ሊሆን ይችላል፤ እንዲያ ሲሆን ይሁንታ አልተቸረም ማለት ነው"

የወሲባዊ ይሁንታ ትምህርት

ከ2023 አንስቶ ወሲባዊ ፈቃድን መጠየቅ፣ መስጠትና መከልከል በአውስትራሊያ ብሔራዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ። መመሪያው የመጣው ከዘመናዊ እሳቤ ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ገፅታና ወሲባዊ በደልን ቀድሞ ለመከላከል በቂ ትኩረት አልተደረገም ለሚለው ትችት ግብረ ምላሽ ከመስጠት አኳያ ነው።

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በዕድሜ በተመጠነ መልኩ ይሁንታንና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን ለማስተማር ያለመና አስገዳጅነትንና የኃይል ሚዛኖችን አለመጠበቅን የሚሸፍን ነው። እንዲሁም፤ ባሕላዊ የሆኑ የወንዶችና ሴቶች ሥፍራን አካትቶ፤ የጅምላ ፆታ አተያዮችን አተኩሮ የሚቃኝ ነው።
MORE FROM THE SETTLEMENT GUIDE
SG Sexual Health  image

How sexual health is taught in Australian schools and tips for parents to talk about sex with their kids

SBS English

11/10/202211:13
ሪቺ ሃርድኮር፤ ከቤተሰብ ጋር በመሥራትና በቅድመ ወሲባዊ አመፅን መከላከል ዙሪያ በማስተማርና በማንቃት የዓመታት ልምድን ያካበተ ነው። ግልፅ ወሲባዊ ትምህርትንና የይሁንታ ፕሮግራሞችን በመላው አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ያካሂዳል።

ከባሕላዊ ሐፍረትና አይነገሬነት አኳያ ስለ ወሲብ በግልፅ ለመናገር አበረታች ባለመሆን፣ ሴቶችን በወሲባዊ ዒላማነት የመመልከትና አመፅን የተላበሰ በጣሙን ግልፅ የሆኑ የወሲብ ምስሎችንና እንቅስቃሴዎች በልጆች ዘንድ የመመልከት ተደራሽነት እየጨመረ በመምጣት በኩል ልዩነት እንዳለ ያምናል።
SG Sexual Consent - SEX online
SEX online Credit: JLGutierrez/Getty Images
አቶ ሃርድኮር “ገነን ባሕል በአብዛኛው ወሲባዊ ጥቃትንና ወሲባዊ የበላይነት ፆታዊ ተመጣጣኝነት በሌለው መንገድ ተቀባይነት እንዲኖረው እያደረገ ነው። ወንዶች ልጆችና አዋቂ ወንዶች በአብዛኛው በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የበላይነት አላቸው። ሴቶችና ልጃገረዶች የወንዶችን ወሲባዊ ግፊት እንዲቀበሉ ተቀርፀዋል”

“ስለ ወሲባዊ የተፈጥሮ አካል፣ ወሲባዊ ኤጄንሲ፣ የጋራ ወሲባዊ እርካታ፣ እንዲሁም፤ ወሲባዊ ጎጂነት በማስወገድ ስለ ወሲብ መልካም ጎን በመነጋገር የተሻለ ተግባር መፈጸም ይኖርብናል" ብለዋል።
ወሲብ አስደማሚ የሰብዓዊ ፍጡር እንቅስቃሴና ... ማንም አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ጉዳት ሊደርስበት አይገባም።
ሪቺ ሃርድኮር፤ ወሲባዊ ትምህርት ሰጪና አንቂ
ምንም እንኳ ወሲባዊ ይሁንታ በእምቢታ የሚሻር ቢሆንም፤ በርካታ ትውልዶች በወሲባዊ መፈላለግ ሂደት ወቅት ወሲባዊ ይሁንታን መጠይቅን ሳይለምዱ አድገዋል፤ ይህም ማለት አያሌ ወሲባዊ ግንኙነቶች ይሁንታ ላይ መመሥረት እንዳለበት ባለማወቅ ያለ ይሁንታ ተፈፅመዋል።

አቶ ሃርድኮር “እስኪ ለሁሉም የሚያሻቸውን ቋንቋ እንስጥ፤ ከዚያም ይህን ማኅበራዊ ውይይት ማድረጉን ልማዳዊ እናድርግ። በእዚህ ረገድ በርካታ ጉዳቶችን እንከላለልን ብዬ አስባለሁ " በማለት አክሏል።
SG Sexual Consent - Couple Having Sex On Bed At Home
Credit: Beatriz Vera / EyeEm/Getty Images
አያይዞም “ስለ አስገድዶ ወሲብ መፈፀም ስንናገር በአብዛኛው አንድ ቢላዋ የያዘ ሰው ከጥሻ ወጥቶ ሌላውን ሰው ጎትቶ በመውሰድ… ይሁንና በአብዛኛው ወሲባዊ አመፅ የሚፈፀመው ሰለባ የሆነው በሚያውቀው ሰው፣ ወይም በቀጠሮ የተገናኙ ወይም ሌላው ቀርቶ የቆየ ግንኙነት ባላቸው ፍቅረኞች ነው። እናም እንደምን ሰዎች አመፅ ያልተቀላቀለበት፣ የጋራ እርካታ የሰፈነበት፣ በይሁንታ የተመላ ወሲብን ስለ መፈፀማቸው እርግጠኞች መሆን እንችላለን?" በማለት ጥያቄ አንስቷል።

ጄስ ሂል በበኩሏ፤ ተፈጥሯዊ ስሜትን በሚያሳድር መልኩ በወሲብ ዙሪያ ያለን ባሕላዊ ሐፍረትን አቃንቶ በማነፅ፣ ከመስመር የወጣውን በማረቅ፣ ፆታዊ ተጠባቂ ወሲባዊ ተግባርን፣ ሴታዊና ወንዳዊ ጥንታዊ ዕሳቤን በማዘመን ወሲባዊ ይሁንታን እንደምን መጠየቅ እንደሚገባ መማርን ታነሳለች ።

“የራሳቸውን ስሜት በመቅረፅና ማግኘት ረገድ ማስተካከል የሚገባቸው አያሌ ሴቶችና ወንዶች አሉ። ቀላል ተግባር አይደለም። ለዚያም ነው እሺ የማለትን ያህል እምቢ ማለትም አስፈላጊ የሚሆንው” ትላለች።

የስሜት መታወክ ድጋፍ የሚያሻዎ ከሆነ 1800RESPECT ይደውሉ ወይም Lifeline በ 13 11 14 ወይም Beyond Blue ዘንድ በ 1800 22 46 36 ደውለው ያነጋግሩ።


Share