አንኳሮች
- በአውስትራሊያ የቤተሰብ ሕግ መሠረት የልጆች ጥቅሞች ወሳኝ ናቸው
- በርካታ ወላጆች በግል ከስምምነት ላይ ይደርሳሉ
- ወላጆች ከስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ በሽምግልና ሊዳኙ ይችላሉ
- የቤተሰብ ፍርድ ቤት የመጨረሻው አማራጭ ነው፤ በሂደቱ ሊመርዎ የሚችሉ አጋዦች አሉ
የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌ ለተጋቢዎች፣ ያለ ጋብቻ አብረው ለሚኖሩና ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች፤ እንዲሁም እንደ አያት ላሉ ተከባካቢዎች ሁሉ እኩል ነው።
ልጆች ከሁለቱም ወላጆቻቸው ስለ ፆታ ወይም በቤተሰብ ውስጥ ስላላቸው የወላጅነት ሚናዎች አንዳችም የይሆናል ዕሳቤ ሳይኖራቸው ከወላጆቻቸው ጋር ትርጉም ያለው ዘላቂ ግንኙነቶች እንዲኖሯቸው ያስችላል።
ይህም ማለት፤ ከመለያየት በኋላ ማናቸውም ወላጆች ወዲያውኑ ልጃቸውን ለመከባከብ ወይም ለሌላው ወላጅ ውሳኔዎችን የመወሰን ድርሻ ይኖራቸዋል።
በርናዴት ግራንዲኔቲ፤ የቪክቶሪያ የሕግ እርዳታ ተጠባባቂ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ናቸው። በቤተሰብ ሕግ ድንጋጌ መሠረት የወላጅነት ኃላፊነትን እኩል መጋራት የሚል ዕሳቤ አለ ይላሉ።
የወላጅ ኃላፊነትን ከግምት ውስጥ የማስገባቱ መነሻ ነጥብ የሚጀምረው፤ ማለትም በተጋሪ ወላጆች መካከል እኩል የጋራ የወላጅነት ኃላፊነትን፣ ስለ ልጆች የረጅም ጊዜ ዋነኛ ውሳኔዎች ላይ ከመድረስ ነው።በርናዴት ግራንዲኔቲ፤ የቪክቶሪያ የሕግ እርዳታ ተጠባባቂ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ
እንደ የቤት ውስጥ ጥቃት ካሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሁኔታ አንደኛው ወላጅ ልጆችን ማየት እንዳይችል ማገድ የሚችለው ፍርድ ቤት ብቻ ነው።
የጋራ ኃላፊነት ማለት ልጁ ከእያንዳንዱ ወላጅ ጋር እኩል ጊዜን ያሳልፋል ማለት አይደለም። ወላጆች በጋራ በመምከር አመቺው ሁኔታ ምን እንደሚሆን ይወስናሉ።
ልጁ ከየትኛውም ወላጅ ጋር ይኑር፤ ሁለቱም ወላጆች ልጃቸውን በገንዘብ ለመደገፍ ግድ ይሰኛሉ።

Equal shared parental responsibility means both parents must support the child financially. Credit: PeopleImages/Getty Images
የወላጅነት ዕቅዶች
በርካታ የተለያዩ ወላጆች ከአስገዳጅ ሕግ ጋር ባልተያያዘ መልኩ የወላጅነት ኃላፊነቶቻቸውን እርስ በእርሳቸው በቃል ተነጋግረው ያመቻቻሉ።
እንዲሁም ወላጆች 'የወላጅነት ዕቅድ' ሊሰኝ ከሚችል በፅሑፍ የሠፈረና በፊርማ የፀደቀ ስምምነት ላይ መድረስ ይችላሉ።
የወላጅነት ዕቅዶች ሕጋዊነት ያላቸው አይደሉም። ትልማቸው መለያየትን ተከትሎ በወላጆች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን ግጭት ለመቀነስ ነው። ዕቅዶቹ በዘላቂ መልኩ ገንዘብንና የአኗኗር ሁኔታዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
በአውስትራሊያ መዲና ግዛት የሴቶች የሕግ አገልግሎት ገዲብ ጠበቃ የሆኑት ሺሪን ፋግሃኒ “ለምሳሌ ያህል፤ ልጆች ከእናታቸው ጋር በእኒህ ቀናት፤ ከአባታቸው ጋር በእኒያ ቀናት ይኖራሉ የሚል”
“ወላጆች አንዳቸው ካንዳቸው ጋር በምን መንገድ መነጋገር እንደሚችሉ የተወሰነ መመሪያ ሊያበጁ ይችላሉ” ብለዋል።
የወላጅነት ዕቅዶች የልጅዎ ፍላጎቶች ሲለወጡ አብረ መለወጥ የሚችሉ ናቸው።
ሕጋዊነት እንዲኖረው ከተስማማችሁና ከውሳኔ ላይ ከደረሳችሁ፤ በኦንላይን ለፌዴራል ወረዳና የአውስትራሊያ ቤተሰብ ፍርድ ቤት ልታመልከቱ ትችላላችሁ።

Little girl feeling sad while her parents are arguing in the background. Credit: skynesher/Getty Images
የቤተሰብ አለመግባባት አፈታት
ወላጆች ከስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ቀጣዩ ደረጃ ሽምግልና ወይም የቤተሰብ አለመግባባት አፈታት ነው።
በየእያንዳንዱ ክፍለ አገራትና ግዛቶች ለገንዘብ እርዳታ መሥፈርትን ለሚያሟሉ ሰዎች ሕጋዊ የሽምግልና እገዛና የግል ሽምግልና አገልግሎቶችን ያደርጋሉ።
የቤተሰብ ፍርድ ቤት ወላጆችን ለፍርድ ቤት ሂደት ከመዳረግ ለመርዳት ያቀርባል። እንዲሁም፤ እንደ የመሰሉ የሕግ እርዳታ አገልግሎቶችና አጋዦች መጠቀም ይችላሉ።
እንደ የፌዴራል ወረዳና የአውስትራሊያ ቤተሰብ ፍርድ ቤት ገዲብ የዳኞችና ተባባሪ ዳኞች ረዳት አስተዳደሪ አን-ሜሪ ራይዝ አባባል “ለልጆች መረጋጋትን ለመፍጠር በወላጆች መካከል የሚከወኑ የድርድር ስምምነቶች ግጭቶችን በማስወገድና ለልጆች መረጋጋትን በመፍጠር ይበልጡን ውጤታማ መሆናቸው ይታወቃል።"

L'aumento del costo della vita sta avendo ripercussioni su migliaia di famiglie in Australia. Source: Moment RF / LOUISE BEAUMONT/Getty Images
የቤተሰብ አለመግባባት አፈታት ባለሙያዎች አድራሻዎችና የክፍያ ዋጋዎችን አካትቶ በ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። የግል ሸምጋዮችም ይህንኑ አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን፤ የክፍያ ዋጋቸው ግና በአብዛኛው ከፍተኛ ነው።
በቤተሰብ አለመግባባት አፈታት ላይ ለመገኘት ጠበቃ ይዘው መቅረብ አያሻዎትም። የቤተሰብ አለመግባባት አፈታታ ባለሙያዎች የቤት ውስጥና የቤተሰብ ጥቃትን አካትቶ ማንኛውም ዓይነት ድርድር ከመካሔዱ በፊት ድርድሩ ደኅንነትን ያስጠበቀ፣ ማናቸውንም ነገሮች ያለ ስጋት ወይም የአደጋዎች አለመደቀንን አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ከእርስዎ ጋር በግል ይወያያሉ። አስተርጓሚ እንዲያቀርብልዎትም መጠየቅ ይችላሉ።
ከሌላኛው ወላጅ በቤተሰብ አለመግባባት አፈታት ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙ፤ በጥሞና ያጢኑ፤ ጥያቄዎች ካለዎትም የሕግ ምክር ይጠይቁ።
መገኘት ካልፈለጉ፤ የእርስዎ አስተያየት ሳይታከልበት ከውሳኔ ላይ ሊደረስ ይቻላል።
የቤተሰብ ፍርድ ቤት
ምንም እንኳ ከአለመግባባት ላይ በመድረስዎ ሳቢያ ወደ ፍርድ ቤት ቢሔዱም፤ ከዳኛ ፊት ለፍርድ ሂደት የመቅረብዎ አጋጣሚዎች በጣሙን ውስን ስለመሆኑ የዳኞችና ተባባሪ ዳኞች ረዳት አስተዳደሪ ራይዝ ያስረዳሉ።
ፍርድ ቤቱ ለእርስዎና ለልጆችዎ ከሚበጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንዲችሉ ደኅንነት የተመሉባቸውን መንገዶችን በማፈላለግ ይረዳዎታል።የፌዴራል ወረዳና የአውስትራሊያ ቤተሰብ ፍርድ ቤት ገዲብ የዳኞችና ተባባሪ ዳኞች ረዳት አስተዳደሪ አን-ሚሪ ራይዝ
የፌዴራል ወረዳና የአውስትራሊያ ቤተሰብ ፍርድ ቤት ወላጆች ልዩነቶቻቸውን በተቻለ ማለፊያ ሁኔታ እንዲፈቱ የማገዝ ግዴታ አለበት። ምንም እንኳ ፍርድ ቤት ተመራጭ አማራጭ ባይሆንም።
ራይዝ “በቤተሰብ ሕግ ሥርዓት ዘርፍ የሠራ ሁሉ ፍርድ ቤት የመጨረሻ አማራጭ ሥፍራ እንደሆነ ይናገራል ... ማንም ለመደበኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚያመለክት ግለሰብ በቅድሚያ ከሌላኛው ወላጅ ጋር ከስምምነት ላይ ለመድረስ መጣር አለበት፤ ልጁ ለአስቸኳይ ሁነትና ከፍተኛ አደጋ የተጋለጠ ካልሆነ በስተቀር”
“ያም ማለት ሕጋዊ ፈቃድ ካለው የቤተሰብ አለመግባባት አፈታት ባለሙያ ዘንድ ለሽምግልና መቅረብንና ከስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻልን ግድ ይላል” ይላሉ።
የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ልጆቻቸውን ወይም የገንዘብ ጉዳዮችን በተመለከተ ወላጆች ምን ሊያደርጉ እንደሚገባ የሠፈረበት መደበኛ የፅሑፍ ሰነድ ነው። ትዕዛዞች ከችሎት ስሚ በኋላ በወላጆች ስምምነት ወይም በዳኞችና ተባባሪ ዳኞች ረዳት አስተዳዳሪ ወይም በዳኛ ሊሰጡ ይችላሉ። አስገዳጅ ሕጋዊነትን የያዙና ልጆች ዕድሜያቸው 18 እስኪሞላ የሚፀኑ ናቸው።
ፍርድ ቤት ትዕዛዞችን በእጅጉ የሚያስከብር ስለሆነ ጥሶ መገኘት ብርቱ የሆኑ መዘዞችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

When planning to move overseas or interstate with your child, consent from the other parent is required unless you are seeking a court order. Credit: MoMo Productions/Getty Images
ከልጅዎ ጋር ሌላ ሥፍራ መሥፈር
ወደ ባሕር ማዶ ወይም ክፍለ አገር ከልጅዎ ጋር ለመሔድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከሌለዎት በስተቀር ከሌላኛው ወላጅ ስምምነትን ማግኘት ግድ ይላል።
ሺሪን ፋግሃኒ “በእዚህ ወቅት ነው ከሕግ ባለ ሙያ ጋር መነጋገር ያለብዎት” በማለት አበክረው ያሳስባሉ።
አክለውም “ፍርድ ቤቱ ወደ ሌላ ሥፍራ ሔዶ መኖር ማለት ከደኅንነት ጥበቃ አኳያ ስለመሆኑ፤ ከቤተሰብ ጋር ቅርብ ለመሆን፣ ከእርዳታ ወይም ከገንዘብ ረገድ የመሆኑን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ አስገብቶ ይመለከታል” ብለዋል።
ሕጋዊ ምክር
ሥርዓተ ሕጉ አዋኪ ሊሆን ይችላል፤ ይሁንና በውስጡ ለማለፍ እገዛዎች እንዳሉ በርናዴት ግራንዲኔቲ ሲመክሩ፤
“የተለያዩ ከሆነና ምን ማድረግ እንዳለብዎት የማያውቁ ከሆነ ወይም በወላጅነት ኃላፊነት እንዲስማሙ ጫናዎች የተደረገብዎት መስሎ ከተሰማዎት፤ ከመስማማትዎ በፊት ሕጋዊ ምክር ይጠይቁ። በተለይም የቤተሰብ ጥቃት የገጠምዎት ከሆነ” ይላሉ።