አንኳሮች
- አውስትራሊያ ውስጥ የደመወዝ ጭማሪ ይገባኛል ብለው ሲያምኑ በማናቸውም ወቅት መተየቅ ይችላሉ
- ለደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ከሠራተኛ ማኅበርዎ፣ ከሥራ ባልደረብዎ ወይም በራስዎ አጋዥነት መሰናዶ ማድረግ ይችላሉ
- የደመወዝ ጭማሪ ከመጠየቅዎ በፊት ምክር ጥየቃን፣ ግንዛቤ ጭበጣንና ያማሳመኛ ዕቅዶችን ያካተተ ተገቢ መሰናዶ ማድረግ ወሳኝ ነው
አለቃዎን የደመወዝ ጭማሪ ለመጠየቅ ውስጥዎን ጫና ቢያድር እርግጥ ነው እርስዎ ብቻዎን አይደሉም።
እንደ የሰው ሃብት ልማት ተጠባቢዋ ኬት ጋትሊይ አባባል በርካታ ሠራተኞች ሁኔታው ምቾት ሰጪ አይደለም። ይሁንና እንዲያ ሊሆን አይገባም።
ወ/ሮ ጌትሊይ፤
“ምቾት ያለ መሰማቱ ይበልጡን እነሱን የሚመለከት ነው፤ አውስትራሊያ ውስጥ አዘቦታዊ ልምድነቱ ወይም ከባሕላዊ አግባብነቱ አኳያ ተቃራኒ በመሆኑ። የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ ምንም አይደለም። ቁልፉ ጉዳይ እንደምን እንደሚከውኑት ማወቁ ነው። የሚሹትን ውጤት ለማግኘት ማለፊያ ተፅዕኖ አለውና" በማለት ይገልጣሉ።
ምንም አንኳ የደመወዝ ጭማሪ እንደ መሥሪያ ቤቶቹ ቢለያይም፤ በጥቅሉ ግና ደመወዛቸውን አስመልክቶ መደራደር ተቀባይነት ያለው ነው።
በ ላ ትሮብ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ፕሮፊሰር (አስተዳደርና የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት) ሱዛን ያንግ፤ የደመወዝ ጭማሪን አስመልክቶ ለመነጋገር መልካሙ ጊዜ የፋይናንስ ዓመት ከማብቃቱ በፊት ባሉት ኤፕሪል እና ሜይ ወራት አካባቢ መሆኑን ልብ ያሰኛሉ።
ለመጪው ዓመት በጀትና ፋይናንስ ስንዱ ሲሆኑ … ያኔ ነው በመጪው ዓመት በጀት ላይ ለማከል፤ የደመወዝ ጭማሪን አንስቶ ለመወያየት የስብሰባ ጥያቄ ሊያነሱ የሚችሉበት ጊዜ።ሱዛን ያንግ፤ በ ላትሮብ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ፕሮፊሰር (አስተዳደርና የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት)
ዓመታዊ የሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ሕጋዊ የይሁንታ መብትን የተላበሰም ሊሆን ይችላል።

If you have signed a job contract, this will likely include conditions about pay rises and their timeline. Credit: djgunner/Getty Images
ለደመወዝ ጭማሪ መብት ያለኝ መሆኑን ማወቅ የምችለው እንደምን ነው?
በርካታ የአውስትራሊያ መሥሪያ ቤቶች በ የብሔራዊ መሥሪያ ቤት የድንጋጌ ጥበቃዎች ሽፋን ያላቸው ናቸው። ይህም በተለዩ ኢንዱስትሪዎችና የሙያ መስኮች የሠራተኞችን ሕጋዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ያካተተ ነው።
በሰዓት ጥቅማ ጥቅሞችን ያካተተ የክፍያ ደመወዝ መብት ያላቸው ሠራተኞች ከሠራተኛ ማኅበር ጋር የደረጉ ድርድሮችን ተከትሎ በ የሚወሰነውን ዓመታዊ ዝቅተኛ ወለል ጭማሪ የማግኘት መብት አላቸው
የሕጋዊ ዝቅተኛ ደመወዝ ጭማሪ ድንጋጌዎች ግብር ላይ የሚውሉት በመሥሪያ ቤቶች ውስጥ የድርጅት ስምምነት ሲኖርና በሠራተኞች ተወካዮችና አሠሪ መካከል መብቶች ላይ የተመረኮዙ ድርድሮች ሲካሔዱ ነው።
ሠራተኞች ጥያቄያቸው ተገቢነት እንዳለው ካሰቡ ከሕጋዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ጭማሪ በላይም ሊደራደሩ ይችላሉ።
“እናም፤ በተመጠነውና ከዚያም በላይ ላለ የደመወዝ ጭማሪ መደራደር ይችላሉ … ወይም ያሉበት የሥራ ኃላፊነት ከሚጠቅሰው በላይ ሚና ያላቸው ከሆነ የሥራ ኃላፊነት ሚናቸው እንዲስተካከል በመደራደር የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ ይችላሉ” ሲሉ ፕሮፌሰር ያንግ ያስረዳሉ።

Lack of pay transparency in a workplace can create disparities between different groups of employees. Credit: Klaus Vedfelt/Getty Images
ውጤታማ ድርድር
ደመወዞችን በሥራ መደቦች፣ እርስዎ በሚገኙበት የሙያ ኢንዱስትሪ አውታረ መረብና መሥሪያ ቤት አካባቢ ማነፃፀር አስፈላጊ ዕውቀትን ለማግኘትና በድርድር ወቅት ውጤታማ ተፅዕኖ ለማሳደር ያበቃል።
ይሁንና፤ በአብዛኛው መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ደመወዝን በተመለከተ ወጣት ሠራተኞችን፣ ሴቶችንና አናሳ ቡድናት ላይ ያልተመጣጠነ ተፅዕኖን የሚያሳድር ምስጢራዊነት አለ።
ፕሮፌሰር ያንግ፤ ከሚተማኑባቸው የሥራ ባልደረቦችዎ ጋር የደመወዝ ጭማሪ ሁኔታዎች ላይ መነጋገር ግንዛቤን ለማስጨበጥና ያልተመጣጠነ ክፍያን ለማንሳት እንደሚያግዝ ይናገራሉ።
አያይዘውም፤
“ በመሥሪያ ቤትዎ የሠራተኛ ማኅበር ተወካይ ካለ፤ እነሱንም መጠየቅ ይችላሉ። ስለምን፤ በመላ መሥሪያ ቤቱ ደመወዝን አስመልክቶ የተሻለ ግንዛቤ አላቸውና” ብለዋል።
ሚሼል ኦኒል፤ የአውስትራሊያሠራተኛ ማሕበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ናቸው።
የሠራተኛ ማኅበር ተወካይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ከእርስዎ ጋር በተመሳሳይ የሥራ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሠራተኞች ምን ያህል ደመወዝ እንደሚያገኙ በማፈላለጉ በኩል ሊረዳዎት ይችላል፤ ያንንም ዳታ ለደመወዝ ጭማሪ ድርድር ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይናገራሉ።
ወ/ሮ ኦኒል የሠራተኛ ማኅበር አባል ሆኖ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በማበር ለተሻለ ደመወዝ መደራደር እንደሚቀልም አበክረው ያስረዳሉ።
“መሥሪያ ቤትዎ ቀደም ሲል ስምምነት የሌለው ቢሆንም እንኳ፤ ከሌሎች የሠራተኛ ማኅበር አባል ሠራተኞች ጋር በመሆን በጋራ እዚህ ለሚሠሩት ሁሉ መደራደር እንፈልጋለን ማለት ይችላሉ" በማለት ያመላክታሉ።

The first step before asking for a pay rise is finding out if you are covered by an award or enterprise agreement, says Prof Young. Credit: AnVr/Getty Images
በራስዎ ለራስዎ የሚጠይቁ ከሆነ ሊያበረክቱ ስለሚችሏቸው ዕሴቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባዎት ፕሮፌሰር ያንግ ሲያሳስቡ፤
“በሥራ ገበታዎ ላይ ያበረከቷቸው ስኬቶች ዙሪያ አበክረው ለመናገር መረጃዎችን ማፈላለግ ላይ ሊያተኩሩ ይገባዎታል። እናም፤ ትልቅ ስኬታማ ውጤቴ ነው የሚሉትን አጉልተው ማሳየት ይችላሉ?"
ወ/ሮ ኦኔል፤ የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ከማቅረብ በፊት ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ሲናገሩ፤
“አበክረው ለማስረዳት ሲያስቡ፤ ለምሳሌ ያህል ለመጨረሻ ጊዜ የደመወዝ ጭማሪ ያገኙት መች እንደሆነ፣ የሥራ መደብዎ እንደምን እንደተለወጠ፣ ተጨማሪ ኃላፊነቶች ያለዎት እንደሆነ፣ ስለሚሠሩባቸው የተለያዩ ሰዓቶች ወይም ስለ ቀሰሟቸው አዳዲስ ክህሎቶች ማሰብ ይገባል” ይላሉ።

Employees and future employees have the right to share or not information about their pay and ask other employees about their pay. Credit: goc/Getty Images
የደመወዝ ጭማሪ የመጠየቅ ስነ ልቦና
እንደ የሰው ሃብት ልማት ተጠባቢዋ ካረን ጋትሊይ፤ የደመወዝ ጭማሪ ሲጠይቁ አቀራረብዎ እንደ የሚሠሩብት ድርጅትና ሥራ አስኪያጅዎ ዘንድ ለመድረስ ያለዎት ምቹ ተደረሽነት አስተዋፅዖ እንዳለው ሲያመላክቱ፤
“በአንድ በኩል፤ አዘውትረው ቢሯቸው የሚቀመጡ ከሆነ፤ በር አንኳክተው ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ጊዜው አመቺ እንደሁ ለመጠየቅ ይችላሉ። በሌላ በኩል፤ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ማስያዝ ተገቢው መንገድ ይሆናል" ብለዋል።
ሆኖም፤ አብዝቶ ማሰብ እንደማያስፈልግምም አሳስበዋል።
“በአዕምሮዎ ውስጥ አዋኪ ሁነት አለመፍጠሩ ስለ እውነት አጋዥ ነው ብዬ አስባለሁ” ሲሉም ምክረ ሃሳባቸውን ቸረዋል።

Pay rise conversations happen always take place in one-one chats. Credit: kate_sept2004/Getty Images
- ዕውቀት ወሳኝ ነው፤ ለእርስዎ የሥራ መደብ አማካይ ደመወዞችን ከማጣራት አልፈው ተጨማሪ ሁሉን አቀፍ ምርምር ያድርጉ።
- ጊዜ ዋጋ አለው፤ የደመወዝ ጭማሪ ለመጠየቅ በድርጅትዎ ውስጥ ማለፊያውን ጊዜ ይጠቀሙ። በአማራጭነትም፤ የድመወዝ ጭማሪ ድርድር ለማድረግ ጥቂት ወራት ቀደም ማለትን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ፣ አለቃዎ ያለ ውጥረት ጊዜ እንዲኖራቸው ማድረግን ያስቡ።
- አዎንታዊና ስልታዊ አቀራረብን ያዳብሩ፤ ስለ ደመወዝ ሲወያዩ፤ ራስዎን በአሠሪዎ ጫማ ውስጥ ያኑሩ። የደመወዝ ጭማሪው እንደምን ለንግዱ ትልቅ እሴትን እንደሚያበረክት ወይም ወጪዎችን ሊቀንስ እንደሚችል አበክረው ያመላክቱ።
ፕሮፌሰር ያንግ እንዲሁ ጉዳይዎን በሚያቀርቡበት ወቅት ሙያዊ ስነ ምግባርን በጠበቀና ተቀባይነት ሊኖረው በሚችል ሁኔታ በማድርጉ አስፈላጊነት ላይ ይስማማሉ።
የደመወዝ ጭማሪ በሚጠይቁበት ወቅት፤ በእውነቱ ስሜታዊ አለመሆን በጣሙን አስፈላጊ ነው። እንዲሁም፤ ለጥያቄዎ ድጋፍ እንዲሆንዎት በመረጃ ያስደግፉ "መልካም፤ በእጅጉ ታትሬ ሠርቻለሁ ወይም በሸማቾች ዋጋ ሰንጠረዥ ሳቢያ መኖር አስቸጋሪ ነው" ከማለት ይልቅ።ሱዛን ያንግ፤ በላትሮብ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር (አስተዳደርና የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት) ፕሮፌሰር
“እንደ እውነቱ የሚያቀርቡትን መረጃ አሰባስበው ስለ መያዝዎ እርግጠኛ መሆንና የሥራ ስነ ምግባርን በመላበስ፤ እየላቁና ታትረው እየሠሩ መሆንዎን ማሳየት ይኖርብዎታል” ብለዋል።
ጠቃሚ አገናኝ ምንጮች
- የፍትሕ ሥራ ኮሚሽን በመሥሪያ ቤት ስምምነቶች ድንጋጌ መሠረት ስለ ደመወዝ ጭማሪ መጠኖችና እንደምን የመሥሪያ ቤት ስምምነትን መፍጠር እንደሚቻል መረጃ አለው። እዚህ
- ስለ ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ተጨማሪ መረጃን ከፈለጉ፤ ይገኛል። ሠራተኞች በሥራ ውል ወይም የመሥሪያ ቤት ፖሊሲ መሠረት ተጨማሪ ደንቦች ይኖሩባቸው ይሆናል።
- አውስትራሊያ ውስጥ ስለሚሠሩ ጠቅላላ የመሥሪያ ቤት ጥበቃዎች መረጃ ይገኛል። ለምሳሌ ያህል፤ አንድ አሠሪ ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ መብት ስላለው (ተገቢ ሆኖ ሲገኝ) ከሥራ ገበታው ሊያባረረው ወይም ሌላ ዓይነት አሉታዊ እርምጃ ሊወስድ አይችልም።
- የፍትሕ ሥራ ዕንባ ጠባቂ FWO ሠራተኞች መቅረትን አካትቶና የመሰለ ነፃ የኦንላይን ኮርስን የመሳሰሉ መጠነ ሰፊ የደረጃ በደረጃ መምሪያዎች አሉት።