አንኳሮች
- ራስዎን የነባር ህዝቦችን ማህበረሰብ ታሪክ በተመለከተ ያስተምሩ ፤ እንዲሁም ከተቀረው ማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይረዱ
- እርስዎ የሚኖሩበት መሬት ባህላዊ ባለቤቶችን በተመለከተ ይረዱ
- የመድብለ ባህላዊው ማህበረሰብ ሊወስድ የሚችለውን ልምድ እና የሚመሰርተውን የጋራ መሰረት ይውቁ
የነባር ህዝቦች ረዳት መሆን ማለት ግለሰቦች በራሳቸው አነሳሽነት በመነሳት ነባር ህዝቦችን የሚያሳስባቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፍ ማለት ነው ሲሉ የዮርታ ዮርታ ሴት የሆኑት ዶ/ር ሰመር ሜይ ፊንሌይ ያስረዳሉ፡፡

ዶክተር ሰመር ሜይ ፊንሌ።
ራስዎን ያስተምሩ
እንደ ማንኛውም አይነት ግንኙነት ፤ጥሩ ተባባሪ እና ረዳት ለመሆን “ ሰዎችን በቅርብ ማወቅ” አስፈላጊ ነው የሚሉት የቡንድጃሉንግ ሴት እና የሪኮንስሌሽን አውስትራሊያ ዋና መሪ ካረን ሙንዲ ናቸው ፡፡
“ ግንኙነቱን እና እኛ ያለንበትን ሁኔታ ለመረዳት ሂደቱ መጀመር የሚቻለው ቀረብ ብሎ ከመረዳት ነው፡፡ የነባር ህዝቦች እና የተቀረው የአውስትራሊያ ማህበረሰብ ፤ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ያለፋችሁበት መንገድ ማለት ነው፡፡ ”
ይህ ሂደት ማንኛውንም አውስትራሊያዊ የሚያበለጽግ ነው ፤ ብለዋል፡፡
“ ከሰዎች ፤ ካሉበት ስፍራ እና ከሀገሪቱ ጋር የራሳቸውን ግንኙነት ለመፍጠር እንዲችሉ እድሉን ይፈጥርላቸዋል ፤ ” ሲሉ ሚስ ሙንዲን ተናግረዋል፡፡
CEO of Reconciliation Australia, Karen Mundine Credit: Reconciliation Australia Credit: Joseph Mayers/Joseph Mayers Photography
“ እኛ ቁጥራችን ሶስት በመቶ ብቻ ስለሆነ ፤ እኛን መርዳት ማለት ሰዎች ራሳቸውን ለማስተማር ጊዜ ወስደው ተምረው ተገኝተው ሲረዱን ማለት ነው፡፡” ይላሉ
“ ነገር ግን እኛ በራሳችን ተነስተን ሁሉንም እናስተምር ካልን ሌላ ምንም አይነት ስራን መስራት አንችልም ፡፡ "
ስለነባር ህዝቦች ለመማር በርካታ መረጃዎች እንደመኖራቸ መጠን ፤ መቅደም ያለበት ግን ሰዎች የሚኖሩበትን መሬት ባህላዊ ባላቤቶች ማንነት ፤ ከቀደምት ህዝቦች ድርጅቶች እና የአካባቢው ማዘጋጃ ቤቶች መረጃን በማግኘት በመረዳት ፤ መሆን አለበት ብለው ሚስ ሙዲን ያምናሉ ፡፡
ዶ/ር ፊንሌይ ሪኮንስሌሽን አውስትራሊያ ወይም በየከተሞቹ የተመሰረቱት ሪኮንስሌሽን ካውስሎች ከመረጃ ምንጮቹ መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ሁሉንም ሰዎች በእኩል እንመልከት
.። መስራችም ነው፡፡ በድረገጽ የነባር ህዝቦችን ድምዕ ለማውጣት እና ለማጉላት የተመሰረተ ተቋም ነው ፡፡
እያንዳንዱ ሰው ለአወንታዊ ለውጥ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረከት ሁሉ ፤ አጋር እና ተባባሪ የሚሉትን ህሳቦች በእርሱ ስሜት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡

Founder of Indigenous X platform, Luke Pearson
“ ግቡ እና አላማም የእናንት ሳይሆን የነባር ህዝቦችን ኑሮ ማሻሻል ነው ፡፡”