አውስትራሊያ ውስጥ ሥራ እንደምን ይፈልጋሉ?

Australia Explained - Job Applications

Male job applicant talking to manager human resources.man interviewing at company.smiling business men chatting cheerfully Source: Moment RF / Me 3645 Studio/Getty Images

አውስትራሊያ ውስጥ በርካታዎቹ የሥራ ዕድሎች በይፋ ማስታወቂያ አይቀርቡም፤ እናም ሥራ ለመፈለግ የአውስትራሊያን የሥራ ገበያ መረዳትና የእራስዎን ዕድሎች መፍጠርን ግድ ይላል። ድብቅ የሥራ ገበያን ለማለፊያ ጥቅም ማዋልና ስለ ፍልሰተኛ ሥራ አገልግሎቶች በማወቅ ሥራ የማግኘት ተግዳሮቶችን በመክላት ረገድ ሊያግዙ ይችላሉ።


Key Points
  • ወደ ድብቅ የሥራ ገበያ መዝለቅ የሥራ ፍለጋ ዕድሎችዎን ከፍ ያደርጋል
  • የፍልሰተኛና ስደተኛ የሥራ አገልግሎቶች የሥራ ዓለም መንገዶችን ያፋጥናሉ
  • በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ እንደ ክብካቤ፣ መስተንግዶና የሴቶችን የንግድ ዓለም መስኮች ክግምት ውስጥ ያስገቡ
ሥራ ፍለጋ ብርቱ ጉዳይ ነው።

አውስትራሊያ እንደዘለቁ በአስቸኳይ የሥራ መብትዎችዎን መረዳትና ታትረው የሥራ ዕድሎችን መከታተል አስፈላጊ ነው።

አግነስ ኬሜንስ፤ በኤንቢ የፍልሰት ሕግ አማካሪ “ሥራን እነሆኝ ብሎ አንድ ሰው እስኪሰጥዎት ድረስ አይጠብቁ”

“ፍፁም ጠንካራ ሆነው ወጣ ብለው ሥራ ሊፈልጉ ይገባል። ማንም ሰው እርስዎን ሆኖ ሥራን አያፈላልግልዎትም”

የሥራ ድረ-ገፆችና ኤጄንሲዎች

እንደ Seek፣ CareerOne፣ Jora የመሳሰሉ የሥራ ድረ-ገፆችና እንደ LinkedIn የመሰሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ምን ዓይነት የሥራ ዓይነቶች እንዳሉና የትኞቹ የሥራ መስኮች ሠራተኞችን በመቅጠር ላይ እንደሚገኙ ግንዛቤ ያስጨብጥዎታል።

እንዲሁም መልማይና ቀጣሪ ኤጄንሲዎችንም ማነጋገር ይችላሉ። መልማይ ኤጄንሲዎች ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ሥራዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ከቀጣሪዎች ላይ ክፍያን ይወስዳሉ። ሠራተኛ ቀጣሪዎች በቀጥታ የሥራ ዕድል የሚያስገኙልዎ ሲሆን፤ የሚቀጥርዎት ለሌሎች አሠሪዎች ነው።
Australia Explained - Job Applications
Recruitment, Job application, contract and business employment concept. Hand giving the resume to the recruiter to review the profile of the applicant. Source: Moment RF / Narisara Nami/Getty Images

ወደ ድብቅ የሥራ ገበያ መዝለቅ

ስለምን በርካታ ሥራዎች በይፋ ማስታወቂያዎች ላይ አይወጡምና ሥራ ፍለጋ ማለት በቀጥታ ከአሠሪዎችና አውስትራሊያ ውስጥ ከሚያውቋቸው ጋር በመነጋገር የግንኙነት መረብዎችዎን መገንባት ማለት ነው።

ሰዎችን ለመቅጠር የሚሹ የፌስቡክ ማኅበረሰብ ቡድኖችን ወይም ጓደኞችዎን እነሱ መሥሪያ ቤቶች ዘንድ የሥራ ዕድሎች ካሉ እንዲጠቁምዎ መጠየቅ ማለትም ነው።

የፍልሰተኛና ስደተኛ ሥራ አገልግሎቶች

ብሔራዊ አትራፊ ያልሆነው ድርጅት ዓለም አቀፍ የሠፈራ አገልግሎቶች ( ዝንቅ ዝርያ ያላቸው ፍልሰተኞችና ስደተኞች ማኅበረሰባት ላይ ያተኮሩ የስልጠናና የሥራ መንገድ ፕሮግራሞችን ይቸራል።

የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ጆዲ ላዝካንያ ሂደቱን ሲያመላክቱ '10 የስኬት ደረጃዎች’ ብለን እንጠራዋለን” ይላሉ።

“ምን ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ ሰነዶቻቸውን እንደምን በአውስትራሊያ ማስረጃ መሠረት መተርጎም እንደሚገባ፣ የባሕር ማዶ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ዕውቅና ማስገኘት እንዳለባቸው፣ ስለ ንግዶች እንደምን ምርምር ማድረግ እንደሚገባቸው፣ እንደ እኛ ካሉ ነፃና ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ ከሚረዷቸው አገልግሎት ሰጪዎች ጋር እንደምን መገናኘት እንደሚችሉ እናሳውቃቸዋለን” ብለዋል።

ባሕር ማዶ ሥራ የነበረዎት ከሆነ SSI አውስትራሊያ ውስጥ ምን እንደሚመስል ያሳይዎታል።

“ለምሳሌ ያህል፤ መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የበርካታ ቢሊየን ዶላር ፕሮጄክቶች ላይ ይሠሩ የነበሩ የመካኒክ መሐንዲስ ከነበሩ እግርዎን እንደምን ወደ በር ማዝለቅ ይቻልዎታል? የባሕር ማዶ የሥራና ትምህርት ማስረጃዎችዎን ዕውቅና የማስገኘት የሂደት ደረጃዎች፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትዎን በሥራ ቦታ ማዳበር፣ በራስ መተማመንን መገንባትና ማኅበራዊ የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋቱ ረገድ ከአንዱ ሥፍራ ሊጀምሩ ይችላሉ?”

በተጨማሪም SSI እራስዎን መሸጥ እንዲችሉ በአካባቢዎ ካሉ ንግዶች ጋር ያስተዋውቅዎታል። አሠሪዎች ቁራጭ ወረቀት ላይ የሠፈረን ከማየት ይልቅ ተሻጋሪ የሆኑ ክህሎቶችንና ልምዶችን ካካበተ ሰው ጋር መገናኘትን ይሻሉ።

የፌዴራል መንግሥቱን የአውስትራሊያ ሠራተኞች ፕሮግራምንና ሌሎች የግል ተነሳሽነቶችን ተመርኩዞ ነፃ የሥራ ፍለጋ አገልግሎቶችን ለፍልሰተኞችና ስደተኞች ይሰጣል።

ፕሮግራሞቹ ፍልሰተኞች ይዘዋቸው የመጧቸውን ጠንካራ ጎኖች፣ ክህሎቶች፣ የትምህርት ደረጃዎችና ልምዶችን ከመንቀስ ባሻገር የሥራ ፍለጋ ተግዳሮችንም ያመላክታል።
የሥራ አልህቆት ፕሮግራም ፍልሰተኛን ወደ ሥራ ዓለም የማዝለቅ መንገዶችን ያፋጥናል።
ሎሪ ኖዌል፤ የጎልማሳ መድብለ-ባሕል ትምህርት አገልግሎቶች የሕዝብ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ
አቶ ኖዌል አክለውም “የስደተኛ ሠፈራ፣ ትምህርትና ሥራ ባልደረቦቻችንን በአንድ ሥፍራ በማሰባሰብ የእያንዳንዱን ፍልሰተኛና ስደተኛ ጉዳይ መለየት ይችላሉ” ይላሉ።

AMES ባለ ሙያ ፍልሰተኞችን ከአውስትራሊያ የሥራ ዓለም ጋር ለማስተዋወቅ በታካይነት ን ያካሂዳል።
Portrait Of Female Aboriginal Australian Worker
Portrait Of Female Aboriginal Australian Worker On Solar Farm wearing Hi-Vis Workwear Credit: Thurtell/Getty Images

ሴቶች በንግድ ውስጥ

የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት ሴቶችን ከንግድ ጋር የማገናኘት ተነሳሽነት በSSI አማካይነት የሚካሔድ ሲሆን፤ ብቃትና ግንዛቤን ለንግዱና ወደ ንግድ ወይም ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ሴቶች ይገነባል።

ወ/ሮ ላዝካኒ “እና በተለይም ከንግዱና ሴቶች ጋር በመሥራት የንግዱን የምልመላ፣ ሠራተኞችን ለረጅም ጊዜያት በሥራ መስክ የማቆየትና ሴቶች በንግዱ ዘርፍ ራሳቸውን እንዲችሉ በሚያደርግ መልኩ እንሠራለን” በማለት ይናገራሉ።

ተነሳሽነቱ ሴቶችን በፋይንናስ ራሳቸውን እንዲያበቁ ማድረግ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ይገነዘባል፤ ስለምን ሴቶች የሚደግፉት ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ተቀጥላ ቤተሰባቸውንም ይደግፋሉና።

የሴቶች ቁጥር በንግዱ ዓለም ማደግ ማኅበራዊ ለውጡ ምን ያህል ሁነኛ እንደሁ አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን፤ በእዚህ ሙያ ዘርፍ ለመሠማራት ለሚሹቱ እሳቤያቸውን ግምት ውስጥ ማስገባቱን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው።

የክብካቤና መስተንግዶ ኢንዱስትሪዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት

AMES አውስትራሊያ ለሥራ ዕድሎች በርካታ የመግቢያ ደረጃ ያለውን የእጅ ሙያ ዘርፍ ስልጠና ያካሂዳል።

ሎሪ ኖዌል ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ “ሙያዊ የብቃት ማረጋገጫ ከሌላቸው፤ ይሁንና መሥራት ከሚሹ ፍልሰተኞችና ስደተኞች ጋር እንሠራለን። እናም በክብካቤና መስተንግዶ በኩል በፍጥነት ክህሎቶችን መላበስና የብቃት ማስረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ” በማለት ያስረዳሉ።
በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አንዱ የክብካቤ ኢንዱስትሪ ነው። ሁለት ሚሊየን ያህል ሠራተኞች ያህል ያሉት ሲሆን፤ በ2025 ወደ 2.5 ሚሊየን ከፍ ይላል።
[ሎሪ ኖዌል፤ የጎልማሳ ፍልስተኛ ትምህርት አገልግሎቶች የሕዝብ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ]
Australia Explained - Job Applications
A high angle view of a businesswoman talking to one of her colleagues while siting at her desk in the office. Credit: Willie B. Thomas/Getty Images

የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ ትሩፋቶች

አግነስ ኬሜንስ “ራስዎን ያስተዋውቁ፤ ክህሎትዎን ያስተዋውቁ”

“ማናቸውም ወደ እዚህ አገር የዘለቁ ፍልሰተኛች ድንቅ ባሕልና ለተወሰኑ ሥራዎች ለየት ያሉ አቀራረቦችን ይዘው የመጡ ናቸው። ለረጅም ጊዜያት ለ30 40 እና 50 ጊዜያት የሥራ ማመልከቻዎ ውድቅ ሲሆን ይህን ምክረ ሃሳብ በእርግጠኝነት እቸራለሁ”

"እንዲህ ባለ መንገድ፤ እግረ መንገድዎን ልምድን ያገኛሉ፤ ብቃትዎንም ለአሠሪዎች ያረጋግጣሉ" ይላሉ።.

Share