አንኳሮች
- አብዛኛዎቹ የኪራይ ቤቶች ማስታወቂያዎች የሚወጡት በዋነኛ ማስታወቂያ አውጪ ገፆች ላይ ነው
- ወኪሎችና የቤት ባለ ቤቶች የእርስዎን የግል መረጃ ስለሚሹ ከማመልከትዎ በፊት ሰነዶችዎን ስንዱ ያድርጉ
- የሚፈልጉትን ለማስረዳት የአከራይ ወኪሎችን በሥራ ሳምንት ውስጥ ይጎብኟቸው፤ ሁሌም ለእነሱ ተመራጭ የሆነውን የማመልከቻ ዘዴ አጥርተው ይለዩ
- የማኅበረሰብዎን ማኅበራዊ ሚዲያ አውታረ መረቦች ይጠቀሙ
አዋኪ የሆነው የኪራይ ቤት ገበያ ልክ እንደ ሥራ ቃለ መጠይቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
ምክረ ሃሳቡ የአውስትራሊያ ትልቁ የኪራይ ድረ ገፅ የሆነው rent.com.au ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ግሬግ ባደር ናችው። ,
ባለ ቤቶችና የኪራይ ወኪሎች እንደ ገቢ ማረጋገጫና ምስክር የሚሆኑ ሰዎችን ስለሚጠይቁ ከባሕር ማዶ በቅርብ ለመጡ ሰዎች መሰናክሎችን እንደሚፈጥሩ ይናገራሉ።
አክለውም “በጣሙን ጠቃሚ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ የቀድሞ የኪራይ ታሪክ ነው። እናም እርስዎ ለእዚህ አገር አዲስ ከሆኑ እርግጥ ነው ያ አይኖርዎትም" ብለዋል።
ይሁንና ይህ ማለት ግና ሁሉም ነገር አበቃ ማለት አይደለምና የሚኖርዎትን አማራጮች ጊዜ ወስደው ይገንዝቡ።
የኦንላይን የቤት ኪራይ ድረ-ገፆች
የኪራይ ቤቶች በሙሉ በቤት ዕቃ የተሟሉ አይደሉም። ምንም አንኳ የኪራይ ጊዜው አዘውትሮ የሚራዘም ቢሆንም የአንድ ዓመት የኪራይ መስፈርትን ማሟላት ግድ ይላል።
ሳምታዊ የኪራይና በአካል ተገኝቶ የመመልከቻ ጊዜያትን ይዘው ከሚወጡቱ ውስጥ , እና ዋነኛዎቹ ድረ - ገፆች ናቸው።
የኪራይ ቤቶችን በሚጎበኙበት ወቅት የጉብኝት ጊዜው 15 ደቂቃ ያህል በመሆኑና በንፅፅሮሽም ከሥራ ቀናት ይልቅ ቅዳሜና እሑድ በቤት ኪራይ ፈላጊዎች ስለሚጨናነቅ እኒህን በአዕምሮዎ ሊይዙ ይገባል።

The number of available rental properties has almost halved compared to two years ago. Source: iStockphoto / mikulas1/Getty Images/iStockphoto
የኪራይ ቤት ማመልከቻ ስለ ማቅረብ
የአውስትራሊያን 800,000 የቤት ኪራይና ግዢ ወኪሎችን አስመልክቶ በወጥነት የተደነገገ የማመልከቻ አገባብ ሂደት ስለሌለ ማመልከቻ አገባቡ በጣሙ ይለያያል።
በአብዛኛው ግና ለኪራይ ቤት በኦንላይን ሲያመለክቱ የሚከተሉትን ሊያሟሉ ይገባል፤
- 100 ነጥቦችን የሚይስገኙቱ የፎቶ መታወቂያ ያላቸው ፓስፖርት እና የመንጃ ፈቃድን የመሰሉ
- የገቢ ማረጋገጫ
- የኪራይ ታሪክና የቀድሞ አክራዮችዎ ስልክ ቁጥርና ኢሜይል አድራሻ
- ስለ እርስዎ መልካም ሰውነት የሚገልጡ ምስክሮች
የአከራይ ወኪሎች በአብዛኛው የሚመርዎት መረጃዎችዎን በኦንላይን እንዲያሠፍሩ ነው። የአመልካቾችን ሰነዶች ከከለሱ በኋላ ተስማሚ የሚሉትን ተከራይ ይመርጣሉ።
ወኪሎች የተለያዩ የማመልክቻ መንገዶችን ስለሚጠቀሙ፤ ማመልከቻዎችዎን በተለያዩ ፋይሎች ማኖር ይገባዎታል።
እንደ ግሬግ ባደር አባባል፤ የእዚህ ፉክክር የበዛበት ገበያ ምስጢር ማመልከቻዎን ከማስገባትዎ በፊት ከአከራይ ወኪል ጋር በቅድሚያ መነጋገር ነው።
የኪራይ ቤትን በሚጎበኙበት ወቅት አንዱ ቀዳሚ ነገር የአከራይ ወኪሉ ተመራጭ የማመልከቻ መንገድ ምን እንደሆነ መጠየቅ ነው። ምክንያቱም ከኢሜይልና ስልክ እስከ ኦንላይን ባሉ የተለያዩ መንገዶች ወኪሉ ማመልከቻዎች ይቀርቡለታልና። በእዚያ መንገድ ቢያንስ እርስዎ በመዝገብ ላይ ከተከራይ ግምት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።ግሬግ ባደር፤ የ rent.com.au ዋና ሥራ አስፈፃሚ

It is important to speak to the realestate agent directly before applying for a rental property. Credit: andresr/Getty Images
አማራጭ የኪራይ መንገዶች
የተከራይ ታሪክ ማስረጃ የሌለዎት ከሆነ ሌሎች አማራጮች አሉ።
ሜልበርን ውስጥ፤ የአነስተኛ ንግድ ባለቤት የሆነው ኒክ የተከራይ ታሪክ ማስረጃ ወይም የገቢ ማረጋገጫዎች የአለመኖር ሁኔታ ገጥሞታል።
ይሁንና ለአካባቢው አከራይ ራሱን የሚያስተዋውቅ፣ ከ20 ዓመታት የቤት ባለቤትነት በኋላ እንደምን ወደ ኪራይ እንዳመራ የሚገልጥ ኢሜይል እንደላከላቸው ሲናገር፤
“የግብር ተመላሾቼን በመስጠት ከረጅም ጊዜያት የራሴ ቤት ነዋሪነት ወደ የኪራይ ቤት ፈላጊነት እንደበቃሁና ለተከራይነት ዕድል ሊሰጡኝ እንደሚገባ በማስረዳት አሳምኛቸዋለሁ” ብሏል።
ግሬግ ባደር የቤት ኪራይ ፈላጊዎች ከቅዳሜና እሑድ ቀናት ይልቅ በአዘቦታዊ ቀናት ከወኪሎች ጋር ቢገናኙ የሚመረጥ መሆኑን አበክረው ያሳስባሉ።
አቶ ባይደር “በኪራይ ቤት ጉብኝት ወቅት እራስዎን ለማስተዋወቅና ግንኙነትን ለመመሥረት በቂ ጊዜ የለም” በማለት “በሳምንቱ አጋማሽ በመሔድና አጋጣሚውን በመጠቀም ምን እንደሚሹ፣ ስለ እራስዎ በመጠኑ በመግለጥና ጓጉተው እንዳሉ ማሳወቁ ብርቱ እገዛ ይኖራቸዋል” ብለዋል።

The number of available rental properties has almost halved compared to two years ago. Source: iStockphoto / chameleonseye/Getty Images/iStockphoto
የኪራይ ቤቶች በማኅበራዊ ሚዲያ
የተወሰኑ የቤት ባለቤቶች የኪራይ ቤቶቻቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ማስታወቅን ይመርጣሉ። ሆኖም ለአጭበርባሪዎች ላለመዳረግ መጠንቀቅም ጠቃሚ ነው።
የኪራይ ቤቱን በአካል ተገኝተው ከመመልከትዎ፣ የሚነጋገሩት ከትክክለኛ የቤት ባለቤት ወይም ሕጋዊ ውክልና ካለው አከራይ ጋር መሆኑን ሳያረጋግጡ በፊት በጭራሽ ቤት ለመከራየት በስልክ ቃል አይግቡ ወይም ገንዘብ አይላኩ።
በሌላም በኩል፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታረ መረቦች እንደ እርስዎ ባለ ሁኔታዎች ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ለመገናኘት ማለፊያ መንገድ ስለ መሆኑ ሲጠቁሙም፤
“እርስዎ የመጡበት አገር፣ ተመሳሳይ ሃይማኖት ወይም ተመሳሳይ የስፖርት ክለብ ማኅበረሰባት በየበኩላቸው የሚያውቋቸው ሰዎች ስለሚኖሩ እነርሱንም ያነጋግሩ” ይላሉ።
በርካታ የቤት ኪራይ ወኪሎች በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች አዲስ የመጡ ሰዎችን ያግዛሉ።ግሬግ ባደር፤ rent.com.au ዋና ሥራ አስፈፃሚ
እገዛ ከሚቸሩ ወኪሎች መካከል አንዱ በሰሜናዊ ሜልበርን የፍቅርና ኩባንያ የኪራዮች ዋና ኃላፊ የሆነው ቢጃን ራሂሚ ነው። የአካባቢው ፋርሲ ተናጋሪ ማኅበረሰብ የቋንቋና ባሕላዊ ተግዳሮቶች ድልድይ በመሆን ሰዎች በስሚ ስሚና ማኅበራዊ ሚዲያ ሕትመቶች ቤቶችን እንዲያገኙ ይረዳል።
“ቋንቋቸውን መናገሩና አመጣጣቸውን ማወቅ ይረዳል"
“የሚኖሩበትን ቤት ማስገኘቱ፣ እዚህ አገር ነገሮች እንደምን እንደሚከወኑ ማስረዳቱ፣ የእነሱ ግዴታዎች ምን እንደሆኑ መግለጡና ክብካቤ እንደሚደረግላቸውም ማስገንዘቡ ጠቅላላ የኪራይ ሂደቱን የተሳለጠ ያደርገዋል” ይላል።
እንደ ያሉ የኪራይ ቤት ምንጮች ማመልከቻ አገባብና ቤት ኪራይ ለማግኘት ቀብድ ከፈላን አካትቶ ስለ ቤት ኪራይ ማወቅ የሚያሻዎትን ፍንጮች ያጋርዎታል።