በእንግሊዝኛ ክህሎት መካን፤ የቋንቋ ችሎታዎችዎን የማጎልበቻ ደረጃዎች

SG Improving English - letters

School and education concept Source: Moment RF / Nora Carol Photography/Getty Images

እንግሊዝኛን መማር በሁለት በኩል ያገለግልዎታል። አንድም የተማሪ ቪዛ የማግኛ መመዘኛን ለማሟላት፤ ሁለትም ለቀጣይ ዕውቀት ቀሰማ። እንዲሁም፤ ሙያዎን ከፍ ለማድረግ ወይም የግል ግብዎ ለማድረግም ጠቀሜታ አለው። አያሌ የጥናት አማራጮችና ከመደበኛ ትምህርት ሥርዓት ውጪ ዕድሎች ቢኖሩም የእንግሊዝኛ ክህሎትዎን ለማሻሻል ጥቂት መሰናክሎች አሉ።


አንኳሮች
  • ነፃ ኧፖችና የኦንላይን መማሪያ ቁሶች ዘና ባለ ሁኔታ እንግሊዝኛን ለመልመድ ሊያግዝዎት ይችላሉ።
  • በመንግሥት የሚካሔደው የጎልማሳ ፍልሰተኛ የእንግሊዝኛ ፕሮግራም ጎልማሳ ፍልሰተኞችንና በሰብዓዊ ፕሮግርማ ለዘለቁቱ የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ይረዳል።
  • የግርጌ የፅሑፍ ትርጉም ያላቸውን ፕሮግራሞች መመልከት፣ ማንበብና የኦዲዮ መፅሕፎችን ማድመጥ ልብ ሳይሉ የሰዋሰው ክህሎትዎን ያሻሽልልዎታል።
በእንግሊዝኛ ክህሎት መካን አዋኪ ነው። የአውስትራሊያን የአንጋገር ቅላፄና ፈሊጦችን መረዳት ምን ያህል አዋኪ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን።

ማርሴላ አጉላር የ (ጎፍእፕ) የበጎ ፈቃድ አስጠኚዎች አስተባባሪ ናቸው።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች በርካታ መሰናክሎች ይገጥማቸዋል፤ ከሁሉም በላይ ግዙፉ መሰናክል ፍርሃት እንደሆነ ሲያመላክቱ፤

“ምናልባትም በዕድሜ የገፉ ይሆናሉ ወይም ከሥርዓተ ትምህርት ከተለዩ ረጅም ጊዜ ሆኖ ይሰማቸዋል። እናም፤ ቀደም ሲል ትምህርት ላይ ስላልነበሩ የመማር ስትራቴጂዎች የሏቸውም” ብለዋል።

ልብ ይበሉ፤ እንደ ግለሰቡ ሁኔታ እገዛ አለና ደፍረው ይጀምሩት።
ቢሳሳቱ ሰዎች ግድ የላቸውም። ቋንቋ መግባቢያ ነውና ሰዎች መስማት የሚሹት መልዕክቱን ነው።
ማርሴላ አጉላር

መደበኛ የእንግሊዝኛ ጥናቶች

እንደ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ኮሌጅ ጥናቶች ዳይሬክተር አሊሰን ሊኑን አባባል፤ የእንግሊዝኛ ጥናቶች ጠንካራ የቋንቋ መቅሰሚያ መሠረትን ይጥላሉ።

አክለውም “ተጨማሪ መደበኛ የእንግሊዝኛ ስልጠናን ማግኘት ለወደፊት የሥራ ዕድል፣ ለወደፊት ተዛናቂነትና የወደፊት ጥናቶች በእጅጉ ያዘጋጃቸዋል” ብለዋል።

ቪዛዎ ምናልባትም የእንግሊዝኛ ክህሎት ደረጃዎን የሚያሳይ ማስረጃን ይጠይቅ ይሆናል።

የአውስትራሊያ መንግሥት ለበርካታ የቪዛ እንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ማመልከቻዎች ዕውቅናን ይቸራል። ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቴፍ፣ የግል ኮሌጆችና የቋንቋ ማዕከላት እንደ IELTS*, CAE* እና TOEFL* ያሉ ኮርሶች ምስክር ወረቀትን ይሰጣሉ።
SG Improving English - woman with laptop
Credit: Westend61/Getty Images/Westend61
የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር ሔስተር ሞስተር፤ እንዲህ ያሉ አማራጮች ሲደቀንብዎ የግብዎን መዳረሻ ጠንቅቆ ማወቁ ወሳኝ እንደሆነ ልብ ሲያሰኙ፤

“ለጉዞና ምናልባትም ለመዝናናት እዚህ ያሉ ተማሪዎች የአጠቃላይ እንግሊዝኛ ኮርሶችን መውሰድ ይሹ ይሆናል።

“የተወሰኑ ወደ አገራቸው ተመልሰው ከዩኒቨርሲቲ መመረቅ የሚፈልጉ ተማሪዎች TOEIC እና IELTS ኮርሶችን የሚሰጡ ተቋማትን ይፈልጉ ይሆናል። ለረጅም ጊዜ አማራጭነት ወደ ቴፍ ወይም ዩኒቨርሲቲ ሊያደርሱ የሚችሉ ፕሮግራሞችን የሚያኪያሂዱ ትምህርት ቤቶች አሉ” ብለዋል።

የተማሪ ቪዛ ያላቸው የተለየ መመዘኛዎች አሉባቸው። ለምሳሌ ያህል፤ ተማሪዎች ከአንድ የቋንቋ ትምህርት ቤት በመመዝገብ በሳምንት የግድ ለ20 ሰዓታት በአካል ተገኝተው መማር ይገባቸዋል።
የተወሰኑ የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ለቋንቋ ችሎታ መመዘኛ ፈተናዎች ሊያዘጋጅዎት ይችላሉ።

ለምሳሌ ያህል፤ ቪዛዎን መቀየር ወይም ዩኒቨርሲቲ መመዝገብ ካሹ የIELTS ምስክር ወረቀት እንደሚያስፈልግዎ አሊሰን ሊኑን ሲያስረዱ፤

“በIELTS እናሰለጥናቸዋለን፤ እናም ለIELTS ፈተና ለመቀመጥ የቴክንኮችና ክህሎቶች ብቃት ይኖራቸዋል” ብለዋል።

የጎልማሳ ፍልሰተኛ እንግሊዝኛ ፕሮግራም

በአውስትራሊያ መንግሥት የአገር ውስጥ ጉዳዮች የሚደጎመው የጎልማሳ ፍልሰተኛ እንግሊዝኛ ፕሮግራም (ጎፍእፕ) ጎልማሳ ፍልሰተኞችና በሰብዓዊ ፕሮግራም የዘለቁቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎቶቻቸውን እንዲያሻሻሉ ይረዳል።

እንደ ጎፍእፕ በጎ ፈቃድ አስጠኚ ፕሮግራም አካልነት፤ ማርሴላ አጉላር በጥንቃቄ ተሳታፊዎችን ከአስጠኚዎች ጋር አንድ ለአንድ ያቆራኛሉ። ፕሮግራሙ ለብርቱ የለውጥ ሽግግር የማብቃት አቅም አለው።
የሚቸሩት የቋንቋ ጥናት እገዛን ብቻ ሳይሆን ወዳጅነትንና አንዳንዴም በጣም ተገልለው ያሉ ሰዎችንም ማበረታታትንም ጭምር ነው።
ማርሴላ አጉላር
ቤት ውስጥ፣ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ወይም የሕዝብ መገናኛ ሥፍራ ላይ መገናኘት እንደሚችሉ ሲያስረዱም፤

“ማናቸውንም ከአካባቢያቸው ኮሌጅ በመሄድ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋሪ ከሆኑ ሠራተኞቻችን ጋር እንዲነጋገሩ፤ መመዘኛውንም የሚያሟሉ ከሆነ የመመዘኛ ግምገማ ወስደው አስጠኚ እንዲያገኙ አበረታታለሁ።

“አስጠኚዎች አበረታቾች ናቸውና 'ይህን ማድረግ ትችላላችሁ፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ላግዛችሁ እዚሁ ከጎናችሁ ነው ያለሁት' በማለት ይነግሯቸዋል” በማለት ያሳስባሉ።
SG Improving English - Woman listening to lesson on headphones
A Taiwanese woman is listening to music/a podcast/an audiobook through a pair of white headphones. Credit: Peter Berglund/Getty Images

እንግሊዝኛዎን የማሻሻያ ፍንጮች

የማርሴላ አጉላር ዋነኛ ፍንጮች፤
  • ቴሌቴክስት ቴሌቪዥን ይመልከቱ። የግርጌ ፅሁፍ ትርጉሞችን በማንበብ፣ በመስማት የአውስትራሊያን አዘቦታዊ የአነጋገር ቅላፄና አገላለጦች ይቅሰሙ።
  • እንደ Duolingo, Bitsboard, Oz Phonics እና Book Creator የመሳሰሉ ነፃ ኧፖችን ይጫኑ።
  • ኦዲዮ መፅሐፍትን እያደመጡ ያንብቡ። አነጋገርን፣ ቅላፄና የቋንቋን ሙዚቃ በመልመድ እግረ መንገድዎንም ሰዋሰውን ይቀስማሉ።
የሔስተር ሞስተር ዋነኛ ፍንጮች፤
  • ወደ ሱፐርማርኬት ሲሄዱ ራስዎ በራስዎ ከፍለው መሔድን ይተዉ። ከገንዘብ ተቀባይ ጋር ለመነጋገር ትንሽ ዕድል ይከፍትልዎታልና።
  • ጊዜዎን ከስልክዎ ጋር ከማጥፋት ይልቅ ከታክሲና ኡበር ሾፌሮች ጋር ይነጋገሩ።
  • እንደ ማኅበረሰብና የስፖርት ቡድኖች የመሳሰሉትን ይቀላቀሉ። ማኅበራዊ ግንኙነትን ብቻ ሳይሆን የሚከውኑት የእንግሊዝኛ ክህሎትዎንም ያዳብራሉ፤ እንዲሁም ከማኅበረሰብዎ ጋር ቅርበትዎን ያጠብቃሉ።
SG Improving English - Student with dictionary and textbook
Credit: Image Source/Getty Images

የኦንላይን ትምህርት

በABC እና SBS የሚሰጡትን የመሳሰሉ ነፃ የኦንላይን መማሪያዎችን ይቃኙ።

በቪዲዮዎች፣ ፅሁፎችና ፖድካስቶች የአውስትራሊያን ባሕል እየተማሩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትዎንም ያዳብሩ።

ምሕፃረ ቃሎች

* International English Language Testing System (IELTS)

* Cambridge English: Advanced (CAE)

* Test of English as a Foreign Language (TOEFL)

Share