አንኳሮች
- የግብር ተመላሽዎን ከማቅረብዎ በፊት የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤትን ከፊል ቅድመ ሙሌት ዳታ በመጠበቅ ጊዜን መቆጠብና ስህተቶችን ማስወገድ ይችላሉ
- የግብር ወኪልን መጠቀም ማለት ከፍተኛ ተመላሽ ማግኘት ማለት አይደለም፤ ይሁንና የግብር ግዴታን ከመወጣትና ሂደቱንም ቀላል በማድርግ ረገድ ይረዳል
- ተመላሾችዎንና የእገዛ አማራጮችዎን ያጣሩ፤ ምናልባትም የግብር ክሊኒክ ወይም የግብር እገዛ ፕሮግራም መመዘኛን ያሟሉ ይሆናል
ገቢዎንና የግብር ተመላሽ መጠይቅዎን የሚያነፃፃረውን ቅፅ ተከትሎ የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ተመላሽ ሊያገኙ ይገባዎ እንደሁ ወይም መክፈል የሚገባዎት ዕዳ እንዳለብዎት አመዛዝኖ ይወስናል።
የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ረዳት ኮሚሽነር ሮበርት ቶምሰን፤ ግብር ከፋዮች የግብር ተመላሽ መጠይቃቸውን አሰናድተው ለማቅረብ በግብር ወኪል በኩል እስከ ኦክቶበር 31 ወይም ያለ ግብር ወኪል ራሳቸው የሚከውኑ ከሆነ ረዘም ያለ ጊዜ እንዳላቸው ልብ ያሰኛሉ።
ምንም እንኳ ከጁላይ 1 አንስቶ የግብር ተመላሽዎን ማቅረብ የሚችሉ ቢሆንም፤ የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት አውቶማቲክ ቅድመ ሙሌት የፋይናንስ መረጃዎችን እንዲያሠፍርልዎት እስከ ወሩ መጨረሻ እንዲጠብቁ ይመከራል።
ይህም፤ የሥራ ክፍያ ማጠቃለያ፣ የገቢ ወለድና የግል ጤና ኢንሹራንስ ዳታን ያካትታል።
Even for data that is automatically pre-filled in your tax return, it is best practice to crosscheck with your records and confirm it is correct Credit: adamkaz/Getty Images
“እናም የግብር ተመላሻቸውን ራሳቸው ይሙሉት ወይም በግብር ወኪል በኩል፤ መረጃው እዚያው ይኖራል” በማለት ያስረዳሉ።
የቅድመ ሙሌት መረጃ የወሰዱትን የድጎማ ክፍያዎች ያካትታል።
የአገልግሎቶች አውስትራሊያ የማኅበረሰብ መረጃ መኮንን ጀስቲን ቦት በበኩላቸው “እርስዎ አንዱ የእኛ ደንበኛ ከሆኑ፤ በጁላይ ወር አጋማሽ ግድም የሴንተርሊንክ ክፍያ ማጠቃለያን ዝግጁ እናደርግልዎታለን” ይላሉ።
የቤተሰብ ግብር ትሩፋት ወይም የሕፃን ልጅ ክብካቤ ድጎማ ተቀብለው ከሆነ፤ እርስዎ አገኘሁት ያሉትን ገቢና ትክክለኛውን ገቢ በማነፃፀር በፋይናንስ ዓመቱ መጨረሻ ።
በአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት የእርስዎ የግብር ተመላሽ ግምገማ ማስታወሻ መሠረት፤ መልሰው ሊከፍሉ አሊያም የሚገባዎትን ተመላሽ ገንዘብ ያገኛሉ። ታሳቢ ገቢዎ ከትክክለኛ ገቢዎ ጋር ተመሳሳይ ከሆነ ማስተካከያ ማድረግ የሚያሻ አይሆንም።
አቶ ቦት “እርስዎ ወይም የፍቅር ጓደኛዎ ለፋይናንስ ዓመቱ የግብር ተመላሽ ማቅረብ የማያሻችሁ ከሆነ አሳውቁን። ስለምን፤ አውቶማቲክ በሆነ መንገድ መረጃው አይደርሰንምና። አንዴ ያንን መረጃ ካገኘን፤ የገቢ ማጣራቱን እኛ እንከውናለን” ብለዋል።
ወደ አውስትራሊያ በቅርቡ የዘለቁ ላለፈው የግብር ዓመት የግብር ተመላሽ ማቅረብ ይገባቸው ወይም አይገባቸው እንደሁ ሊያረጋግጡ ይገባል።
ያም ባይሆን፤ የግብር ተመላሽ የማያሻውን ቅፅ ለአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ማቅረብ ግድ ይላቸዋል።
In Australia, taxpayers are entitled to the tax-free threshold. It means you can earn up to $18,200 each year without paying tax. Credit: jeangill/Getty Images
የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤቱ አቶ ቶምሰን፤ የግብር ተመላሽ ከመጠየቅ በፊት ሶስት ቁልፍ ነገሮችን ልብ ማለት እንደሚያሻ ሲያስቡ፤
- ወጪውን እራስዎ ያወጡ መሆንና ተመላሽ ያላገኙበት ሊሆን ይገባል።
- ያም ወጪ ገቢ ከሚያገኙበት ጋር በቀጥታ ተያያዥ መሆን አለበት።
- ወጪዎን የሚያረጋግጥ የደረሰኝ ሬኮርድ ሊኖርዎት ይገባል፤
ይላሉ።
ከቤት መሥራት
ከቤትዎ ሆነው የሚሠሩ ከሆነ፤ በሰዓት ከቤት ሆነው የሠሩበትን ቋሚ የጊዜ መጠን (ቋሚ የጊዜ መጠን ዘዴ) አሊያም ትክክለኛውን ወጪዎችን (ትክክለኛ ወጪ ዘዴ) በመጠቀም ።
በየትኛውም መንገድ ይሁን፤ መላ ዓመቱን ከቤትዎ ሆነው የሠሩባቸውን ሰዓቶች ሬኮርድ ሊይዙ ይገባል።
“በአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ድረገፅ ላይ ሰዎች ስለምን ለሥራ ዘርፋቸው የግብር ተመላሽ መጠየቅ እንደሚችሉ ወይም እንደማይችሉና ምን ዓይነት ሬኮርዶችን መያዝ እንዳለባቸው የሚያስገነዝቡ አሉን። ”
If working from home, you need to keep records to substantiate any claims for tax deductions on expenses incurred. Credit: MoMo Productions/Getty Images
ስንዱ እገዛ
እንዲሁም፤ ከአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ገለልተኛ በሆነ የፌዴራል ድጎማ ፕሮግራም አማካይነት በመላ አገሪቱ ከ15 በላይ በሆኑ ክሊኒኮች መመዘኛዎችን ለሚያሟሉቱ ምዝገባ ካካሔዱ የግብር ወኪሎች ጋር በመተባበር ነፃ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።
በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ የግብር ሕግ ፕሮፌሰርና ግብርና ንግድ አማካሪ ክሊኒክ መሥራች ዳይሬክተር የሆኑት አን ካዪስ-ኩማር፤ ከደንበኞች አተያይ አኳያ፤ አገልግሎቱ በፋይናንስ ተግዳሮትና ሁከት ውስጥ ላሉ ሰዎች አጋዥ እንደሆነ ሲያስረዱ፤
“ከማኅበረሰብ መስክ ወደ እኛ ይመራሉ፤ በአብዛኛው የሚመሩት በፋይናንስ አማካሪዎች፣ የሕግ አገልግሎቶች፣ ላይፍላይን እና ሌላ የማኅበርሰብ አገልግሎት አማካይነት ነው” ይላሉ።
የግብር ወኪልን መጠቀም
በርካታ አውስትራሊያውያን የግብር ተመላሾቻቸውን ለማሠራት ለግብር ወኪል አገልግሎቶች ክፍያዎችን ይፈፅማሉ፣ እርግጥ ነው፤ ት።
አንድ በፕሮፌሰር ካዪስ-ኩማር አጋር መሪነት የተካሔደ የግብር ወኪልን መጠቀሙ እራስዎ ከሚሠሩት የግብር ተመላሽ ጋር ሲነፃፀር የላቀ የግብር ተመላሽ እንደማያስገኝ አመልክቷል፤ የዓመት ገቢዎ ቢያንስ $180,000 የሚደርስ ካልሆነ በስተቀር።
“ከተባባሪ ደራሲዎቹ ክሪስ ኢቫንስና ያንግዲዮክ ሊም ጋር የአምስት ሚሊየን አውስትራሊያውያንን የአምስት ዓመታት የግብር ተመላሾች ናሙና ተመልክተናል። ሰዎች ከታክስ አማካሪ የሚያገኙት እውነተኛ ጥቅም ሆኖ ያገኘነው፤ አመቺና እርግጠኛ የሆነ እንደ ንግድና የኪራይ ገቢ ወይም ከሽርካነት ወይም ከሶስተኛ አካል የሚገኝ ከፍተኛ ደጓሚ ገቢ ያለዎት ሲሆን ነው” በማለት ፕሮፌሰር ካዪስ-ኩማር ተናግረዋል።
If using a tax agent to file your tax return, make sure that you’ve registered with them by 31 October and that they’ve notified the ATO. Credit: Edwin Tan /Getty Images
በማከልም “የግብር ባለሙያዎች ቦርድ የእርስዎ የመጀመሪያው የስልክ ጥሪ መዳረሻ ነው፤ ይሁንና አንዳቸው የዕውቅና ማረጋገጫቸውን አንግተው ወይም ለጥፈው ያሉትን የተመለከቱ እንደሆነና ፍለጋም በማድረግ ምዝገባ ያካሔዱ የግብር ወኪል መሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ” ብለዋል።
እናም ሁሌም የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ነን ባይ አስመሳዮች ነቅተው መጠበቁን አይዘንጉ።
አቶ ቶምሰን በ2023 የግለሰብ ማንነት መረጃን ለማግኘት የአጭበርባሪዎች ከሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ በ60 ፐርሰንት እንደጨመረ አመላክተዋል።
እኒህም፤ እንደ ስም፣ አድራሻ፣ myGov ID፣ የግብር ማኅደር ቁጥር ወይም የብድር ካርድ ዝርዝሮችን የመሰሉ፤ እርስዎን ተመስለው ለመቅረብ የሚያስችሏቸውን ዝርዝር መረጃዎችን ያካትታል።
“መልዕክቱ ወይም የስልክ ጥሪው የሐሰት መሆኑን አለመሆኑን እራስዎን ይጠይቁ፤ በጭራሽ የእርስዎን MyGov አካውንት ሃይፐርሊንኮች አይጫኑ። ሁሌም የ MyGov ወይም የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት ዝርዝሮችን በእራስዎ መፈለጊያ ይጠቀሙ” በማለት አቶ ቶምሰን ያስጠነቅቃሉ።
አያይዘውም “የሆነ የተሳሳተ ነገር ያለ መስሎ ከታሰብዎት ወይም የአውስትራሊያ ግብር ጽሕፈት ቤት አካውንትዎ ላይ ጥርጣሪዎችን የሚያሳድሩ እንቅስቃሴዎችን ልብ ካሉ እኛን ያነጋግሩ” ብለዋል።
Some Services Australia payments, like those relating to flooding and natural disasters are taxable and you need to add them manually on your tax return. Source: Moment RF / Songsak rohprasit/Getty Images
- ከግብር ጋር ተያያዥ ለሆኑ የሴንተርሊንክ ክፍያዎችና አገልግሎቶች ጉዳዮች በተመለከተ፤ በቋንቋዎ መረጃን ማግኘት ይችላሉ ወይም የሴንተርሊክ መድብለ ቋንቋ ስልክ አገልግሎት ዘንድ በ 131 202 ይደውሉ።
- የቤተሰብ ግብር ጥቅም ወይም የልጅ ክብካቤ ድጎማ ባለፈው የፋይናንስ ዓመት ያገኙ ከሆነ
- ባለፈው የፋይናንስ ዓመት ሌላ ሀገር ግብር ከፍለው ከሆነ፤ አውስትራሊያ ውስጥ የውጭ ግብር ገቢ ማካካሻ ሊጠይቁ ይችላሉ። መመዘኛውን ያሟሉ እንደሁ ያጣሩ።
- ነፃ ሬኮርድን መዝግቦ ለመያዝ የሚጠቅም ነፃ የአውስትራሊያ ግብር ፅሕፈት ቤት ኧፕ ነው።
- የግብር ክሊኒክ ፕሮግራምን ይፈልጉ።
- ከ $60,000 በላይ ወይም በታች ያገኙ እንደሁ የግብር ተመላሽዎን በአውስትራሊያ ግበ ጽሕፈት ቤት የግር እገዛ ፕሮግራም አማካይነት ለማቅረብ መመዘኛውን ያሟሉ ይሆናል። በተጨማሪ ይረዱ።
- ከግብር ጋር ተያይዥነት ያለው መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች በአውስትራሊያ ግብር ፅሕፈት ቤት ድረገፅ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛሉ።