አውስትራሊያ ውስጥ የቤተሰብ ጥቃትን በፍልስተኛ ማኅበረሰባት ዘንድ እንደምን መግታት እንደሚቻልዎ

Services say the lockdown measures are placing women at increased risk.

Source: Press Association

የቤተሰብ፣ የቤት ውስጥና ወሲባዊ ጥቃት አውስትራሊያ ውስጥ ዋነኛ የጤናና የደኅንነት ጉዳዮች ናቸው። ከ15 ዓመት ዕድሜያቸው አንስቶ ከአምስት ሰዎች ውስጥ አንዳቸው አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል። ይሁንና ፍልሰተኛ ሴቶች እርዳታ በሚሹበት ወቅት ተጨማሪ መሰናክሎች ይገጥሟቸዋል።


እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፤ የቤተሰብ ወይም የቤት ውስጥ ጥቃት የሕብረተሰብ ሳይሆን የግል ጉዳይ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ይሁንና በርካታ አውስትራሊያውያን በቤተሰብ አባላት የጥቃት ሰለባዎች ስለ መሆናቸው በስታቲስቲክ ተረጋግጧል።

በአብዛኛው የቤተሰብ፣ የቤት ውስጥና ወሲባዊ ጥቃት ሰለባዎች ሴቶች ናቸው። ከስድስት ሴቶች አንዷ እና ከስምንት ወንዶች አንዱ በፍቅር ተጓዳኞቻቸው አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል።

በደቡብ አውስትራሊያ የሕፃናት ጥበቃ ማዕከል የቤት ውስጥና የቤተሰብ ጥቃት ተጠባቢዋ ዶ/ር ናዳ ኢብራሂም “የቤተሰብ ውስጥ ጥቃት በቤት ውስጥ ወይም በቤተሰብ መካከል የሚደርሱ የማናቸውም ዓይነት ጥቃቶች መገለጫ ቃል ነው” በማለት ያስረዳሉ።
የቤተሰብ ውስጥ ጥቃት እንደ ... የፍቅር ጓደኛ ጥቃትን፣ ሕፃናትን፣ አረጋውያንን፣ ዘመድን ወይም ወላጅን ማጎሳቆልን ያካትታል። እናም፤ ማናቸውም በቤት ውስጥ የሚደርሱ የጥቃት ክስተት ዓይነቶች።
ዶ/ር ናዳ ኢብራሂም፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የሕፃናት ጥበቃ ማዕከል
ስለ ቤት ውስጥ ጥቃት ስንናገር አካላዊ ስለሆኑቱ ብቻ አይደለም። ጥቃት የፋይናንስ፣ የትንኮሳ ወይም የኃይል ቁጥጥር ማድረግን የመሳሰሉ በርካታ ስነ ልቦናዊ ጉስቅልናን የመሳሰሉ ገፅታዎችን ይይዛል።

ዶ/ር ኢብራሂም፤ እስካሁንም ድረስ ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብ ይዘው ያሉና ጥቃት ከአካላዊ ጥቃት ውጪ በሆነ መልኩ ወይም በተለያዩ መንገዶች እንደሚደርሱ መገንዘብ ያልቻሉ የተወሰኑ ሰዎች እንዳሉ ሲያስረዱ፤

“አንዳንዴ፤ በተወሰነ ባሕል የቤት ውስጥ አመፅን ከአካላዊ ጥቃት ውጪ አለመረዳት ይኖር ይሆናል። አካላዊ ጥቃትን ጎልቶ በመታየቱ ሳቢያ አይታገሱ ወይም አይቀበሉት ይሆናል። ይሁንና ሌሎች የቤት ውስጥ ወይም የቤተሰብ ጥቃትን ለይቶ ለማየት ያውካቸው ይሆናል። በተለይም፤ እንደ በቃላት ለጉስቁልና በመዳረግ፣ በስነ ልቦናዊ ወይም የፋይናንስ ወይም ማኅበራዊ እንግልት ሳቢያ ከማኅበረሰባት መገለልን መለየት ይሳናቸዋል" ብለዋል።

በተወሰኑ መልኩ፤ ሃይማኖታዊ እምነቶች ወይም ከዘመድ አዝማድ የሚደርሱ ጫናዎች በቤት ውስጥ የጥቃት ሁኔታዎች ላይ ውስብስብ ነገሮችን ሊያክሉ ይችላሉ።
ሁሉም የቤተሰብ ጥቃት አገልግሎት ሰጪ ኤጄንሲዎች ባሕል ተሻጋሪ ብዥታዎችን ለመቋቋም ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ይሁንና አውስትራሊያ ውስጥ እንደ ያሉ በፍልሰተኛና ስደተኛ ማኅበረሰባት የቤተሰብና የቤት ውስጥ ጥቃት ጉዳዮች ላይ የተካኑ በርካታ ድርጅቶች አሉ።

የባሕል ተሻጋሪ አማካሪ ድርጅት ኩልቱሬብሪሌ ዳይሬክተር አኑ ክሪሽናን የቤተሰብ ጥቃት ቅድመ መከላከልንና ሌሎችም ጉዳዮችን አስመልክቶ የባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ደንበኞችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ያግዛሉ።

አንዳንዴ የፍልሰት ጫና በራሱ ለቤት ውስጥ ጥቃት ቀስቃሽ ሊሆን እንደሚችል ሲያሳስቡ፤

“በፍለሰተኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ከአዲስ ባሕል ጋር ራሳቸውን የማዋደድ ረብ ያለው ሥራና ሙያዊ ዕድሎችን ፈልጎ የማግኘት ተጨማሪ ጭንቀት አለባቸው። በጣም አዘውትሮም ከአገራቸው በሚለይ መልኩ በፆታ ሚዛናዊነት፣ ለአዲስና ነፃ ለሆነ ባሕል ሙሉ በሙሉ የመጋለጥ ተግዳሮትም ይገጥማቸዋል" ብለዋል።
ወ/ሮ ክሪሽናን አክለውም፤ የቤተሰብ ጥቃት ቅድመ መከላከል ፍቱን የሚሆነው መላው ማኅበረሰብ ተሳታፊ እንደሆነ ሲያመላክቱ፤

“ሴቶች ድፍረት ወይም በራስ መተማመን ኖሯቸው እርዳታን እንዲጠይቁ በርካታ ድጋፍ ሊኖር ይገባል...በአብዛኛው ከፍቅረኛ ጋር የተያያዘን ጥቃት ሪፖርት ማድረግ ከሐፍረት ጋር ስለሚያያዝ ሴቶች ያንን አያደርጉም። ያን ሐፍረት መክላት ይገባናል። መናገር ተገቢ እንደሆነ፣ እነሱ ሊወቀሱበት እንደማይገባ ልንነግራቸው ይገባል” ብለዋል።

[እኛም] ከማኅበረሰቡ ውስጥ ሆነን ግንዛቤ የማስጨበጫ ፕሮግራሞች ሊኖሩን ያሻል። እንዲያ ሲሆን፤ ሌሎች የማኅበረሰብ አባላትም ሊተባበሩና የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባት ሴት የተገለለች ሆኖ እንዳይሰማት ማገዝ ይችላሉ።
አኑ ክሪሽናን፤ የኩልቱሬብሪሌ ዳይሬክተር
ወ/ሮ ክሪሽናን ፍልሰተኛ ሴቶች እርዳታ ሲጠይቁ ተጨማሪ ጋሬጣዎች እንደሚጋረድባቸው ያመላክታሉ። በአብዛኛው የተገለሉና ወዴት መሔድ እንዳለባቸው እንደማያውቁ ሲገልጡም፤

“ሪፖርት ለማድረግ ይፈራሉ። ሪፖርት ቢያደርጉ እንኳ መሔጃቸው የት ይሆናል? የሌሎችን ሰዎች እርዳታ መቀበል ወይም ወደ ሴቶች መጠለያ ማምራትን አልለመዱም። እኒያ መጠለያዎች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ በአዕምሯቸው ውስጥ ቀድመው የተቀረፁ እሳቤዎች አሉ።

"በርካታ ሴቶች የቪዛ ችግሮች አሉባቸው። እናም ለመኖሪያ የሚሆን ወጪያቸው በፍቅር ጓደኛቸው ላይ የተመረኮዘ ይሆናል። አንዳንዴም ልጆቻቸውን ይዘው የመውጣት አቅም የላቸውም" ይላሉ።
ዌንዲ ሎብዊን፤ ፍልሰተኞችን በዳግም ሠፈራ የሕይወት ጉዟቸው ወቅት እገዛ የሚያደርገው የጎልማሳ መድብለባሕል ትምህርት አገልግሎቶች የሴቶች ጥቃት ቅድመ መከላከል ፕሮግራም ገዲብ ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ወንዶችም በእዚህ ተነሳሽነት ቢካተቱ መልካም እንደሆነ ሲናገሩ፤

“እንደ እውነቱ ከሆነ ወንዶች በወንዶችና ሴቶች መካከል መከባበር የተመላበትን ግንኙነቶች፣ በሴቶች ላይ ያሉ የንቀት አመለካከቶችን ወይም ሴቶች ላይ ጥቃት ማድረስን አስመልክቶ አንዳቸው አንዳቸውን በማረቅ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላሉ” ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በቤተሰብ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ፍልሰተኛ ሴቶች በርካታ አገልግሎቶች አሉ።

በርካታዎቹ እኒህ ጉዳዮች በሁሉም ቋንቋዎች በአስተርጓሚ ድጋፍ ይካሔዳሉ።

የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰብዎ ከሆነ ለጠቅላላ ሐኪምዎ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ሐኪምዎ አግባብነት ወዳላቸው አገልግሎት ሰጪዎች ሊመራዎት ይችላል።

ይሁንና ጊዜ ለማይሰጥ አደጋ ተጋልጠው ያሉ ከሆነ ወደ 000 ፈጥነው ለመደወል እንዳያመነቱ ወ/ሮ ሎብዊን ሲመክሩ፤

“በርካታ ሴቶች ፖሊስ በጉዳዩ ሊገባ ይችላል በሚል ፍርሃት የሚዋጡ እንደሁ አውቃለሁ። የቤተሰባቸው መፍረስ ወይም መለያየት ጅማሮ እንደሆነ አድርገውም ያስባሉ። ይሁንና ፖሊስ ስልጠና ያለው ጋብቻን ወይም ግንኙንቶችን በማክሰም ሳይሆን ለሰዎች ደኅንነት ምላሽ በመስጠት ረገድ ነው" ይላሉ።

እርዳታን ከየት ማግኘት እንደሚቻል፤

  • እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የቤተሰብ ጥቃት ሰለባ ከሆነ እርዳታ ለማግኘት ይደውሉ።
  • ለስሜት መታወክ እርዳታን የሚሹ ከሆነ ወደ በ 13 11 14 ወይም በ 1800 22 46 36 ይደውሉ።
  • አስተርጓሚ የሚሹ ከሆነ 13 14 50 ይደውሉ።

ተጨማሪ አገልግሎት ሰጪዎች፤


Share