በአውስትራሊያ ራስዎን ከማንነት መታወቂያ ስርቆት እንዴት መከላከል ይችላሉ ?

Hacker

Experts advise keeping your devices updated with the latest software, including antivirus software. Source: Moment RF / krisanapong detraphiphat/Getty Images

የመታወቂያ ስርቆት በአውስትራሊያ አሳሳቢ የሆነ ወንጀል ነው፤ በየአመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም የዚህ ወንጀል ሰለባ እየሆኑም ነው ። ተጠቂዎቹም በአብዛኛው ከፍተኛ ለሆነ የገንዘብ ኪሳራ ፤ የብድር አቅም ብልሽት እና በህግ ለሚያስጠይቁ ችግሮች ሊጋለጡ ይችላሉ ። የግል መረጃዎችዎ እንዳይሰረቁ ወይም ከእርስዎ ፈቃድ ውጭ ያለአግባብ ለአገልግሎት እንዳይውሉ ሊከትተሏቸው የሚገባዎት መንገዶች እነሆ ።


አንኳሮች
  • መረጃዎች የመስረቅ ዘዴዎች ማለትም የተጭበረበሩ ኢሜሎች፤ የግል መረጃዎችን መውሰድ እንዲሁም መጥለፍ የሚሉትን ያካትታል
  •  የመታወቂያ ስርቆት በኦን ላይን ወይም ያለኦን ላይን ወይም ሁለቱንም ባካተተ መልኩ ሊሆን ይችላል
  • የመታወቂያ ስርቆት ሰለባ እንደሆኑ ከተረዱ ተገቢውን የባለስልጣን መስሪያቤት በአስቸኳይ ማነጋገር አለብዎ
በአውስትራሊያ በመታወቂያ ዙሪያ የሚፈጸም ወንጀል አሳሳቢነቱ እያደገ መጥቷል ። ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ኪሳራን በአውስትራሊያ መንግስት ፤ የግል ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ እንዲደርስ አድርጓል።

በአውስትራሊያ የውድድር እና ተጠቃሚዎች ኮሚሽን በሚንቀሳቀሰው ስካምዋች ዌብሳይት ባወጣው መረጃ መሰረት አውስትራሊያውያን በ 2022 አ.ም ብቻ $568 ሚሊዮን ተጭበርብረዋል ።

አሀዘዊ መረጃው የሚያመላክተውም ባለፈው አመት ከነበረው $ 320 ሚሊያን ጋር ጋር ሲነጻጸር በ80% መጨመሩን ነው ። እንደባለሙያዎቹ አባባልም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የተጭበረበሩ ሰዎች ጉዳዩን አውጥተው ስለማይናገሩ እንጂ ሁሉም ይፋ ቢያደርጉ ይህ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ነው ።
Digtal identity
Criminals could access and drain your own bank account of the funds, or open new bank accounts in your name and take out loans or lines of credit. Credit: John Lamb/Getty Images
ዶ/ር ሲራንጋ ሴንቪራትን በሲድኒ ዪኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ት/ቤት ከፍተኛ መምህር እንደሚሉት ፦

ስርቆት ማለት የአንድ ግለሰብ ግላዊ መረጃዎችን በመስረቅ በተጭበረበረ መንገድ ገንዘብን በማግኘት ተጠቃሚ መሆን ሲቻል ነው ።

“ ይህ በአብዛኛው የሚሆነውም ፤ መረጃ ሰራቂዎቹ የግለሰቦችን የብደር ካርድ ያለፍቃድ መጠቀም ሲችሉ ፤ አንዳንድ ጊዜም የሌሎች ሰዎችን ግላዊ መረጃዎችን በመጠቀም እንደ የታክስ (ግብር ) ምላሽን ፤ ከመንግስት የሚከፈል ክፍያን ፤ወይም ብድርን ማግኘትን ሁሉ ሊያጠቃልል ይችላል ።

የሳይበር ወንጀለኞች ምን አይነት መረጃዎችን ይሰርቃሉ ?

የሳይበር ወንጀለኞች የተለያዩ የግል መረጃዎችን ለመስረቅ አሰሳዎችን ያደርጋሉ ከነዚህም መካከል፦

· ስም

· የልደት ቀን

· የመንጃ ፈቃድ ቁጥር

· አድራሻ

· የእናት የጋብቻ ስም

· የትውልድ ቦታ

· የብደር ካርድ ዝርዘር መረጃዎች

· የታክስ ቁጥር

· የሜዲኬር ካርድ ዝርዘር መረጃዎች

· የፓስፖርት መረጃዎች

· የግል መለያ ቁጥር

· የኦን ላይን አካውንት ዩዘር ኔም እና ሎግ ኢን ዝርዘር

በአውስትራሊያ የውድድር እና ተጠቃሚዎች ኮሚሽን (ACCC) ምክትል ሰብሳቢ ካትሪዮና ሎዊ እንደሚሉት ለሌሎች አነስተኛ የሚባሉ መረጃዎችን መጠላፊዎቹ ካገኙ እንደ ትልቅ መረጃ ይጠቀሙበታል ።

“ ለምሳሌ ስምዎ ፤ አድራሻዎ እና የስልክ ቁጥርዎ ብቻቸውን በራሳቸው ብዙም ነገሮችን ማድረግ አይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች ከሌሎች ጋር ሲቀናጁ እጅግ በጣም ጉልበት ያላቸው መረጃዎች ይሆናሉ ። ” ይላሉ ዶ/ር ሎዊ

ዶ/ር ሎዊ መረጃ ሰራቂዎቹ ሰለ እርስዎ ከህብረተብ ምንጭ መረጃን ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል ፤ ለምሳሌ የእርስዎን እና የቤተሰብዎን ፎቶግራፎች እና መረጃዎች ካለበት እንደ የማህበረሰብ ድረ ገጽ ማግኘት ይችላሉ።


መረጃ ሰራቂዎቹ ፎቶግራፎችን ከማህበረሰብ ድረ ገጽ በመውሰድ የሀሰት አካውንቶችን ሊከፍቱ እና ሊጠቀሙ ይችላሉ ።
ካትሪዮና ሎዊ በአውስትራሊያ የውድድር እና ተጠቃሚዎች ኮሚሽን (ACCC) ምክትል ሰብሳቢ
“ ስለዚህ በድጋሚ የምናገረው ዋነኛው መልእክት ፤ የግል መረጃዎችን በሚለዋወጡ ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄን ያድርጉ የሚለው ነው። ” ይላሉ ዶ/ር ሎዊ
Authorities warn to limit what you share online.
Authorities warn to be cautious about posting personal information on social media platforms. Source: AP / Eraldo Peres/AP

የመታወቂያ ስርቆት የሚከናወንባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ ከነዚህም መካከል ፦

· በኢሜል አማካኝነት ( Phishing )፦  ይህ የሚሆነው ጥቃቱን ፈጻሚው ትክክለኛ ከሆነ ተቋም የሚመስል ኢሜል ወይም መልእክት በመላክ ሲሆን ፤ ለምሳሌ እንደ ባንክ ወይም የመንግስት መስሪያ ቤት ፤ በመምሰል የግል መታወቂያ መረጃዎችን በመጠየቅ ነው ። ጥቃቱን ፈጻሚው ይህንን መረጃ በእጁ ካስገባ ለተጭበረበሩ ጉዳዮች ሊጠቀምበት ይችላል፡

· መረጃን በድብቅ ቀድቶ መውሰድ (Skimming )፦ ይህ ማለት በብድር ወይም በተቀማጭ ካርድ ላይ ያሉትን ማግኔቶች የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ከውስጣቸው መረጃዎችን ቀድቶ መስረቅ ማለት ነው። እነዚህ መሳሪዎችንም በኤ ቲ ኤም ፤ የጋዝ ማደያ ወይም ሌሎች ካርድን ሊያነቡ በሚችሉ ስፍራዎች ላይ በመግጠም መረጃዎችን ቀደተው መውሰድ ይችላሉ።

· ስነልቡናዊ ጫናን መፍጠር፦ የግለሰብን ስሜታዊነት በመጠቀም በማጣደፍ ፤ ሆን ብሎ በማበሳጨት ፤ ውለታን የዋሉ በማስመሰል የግላዊ መረጃን እንዲሰጡ ማስገደድ ማለት ነው ።

· መረጃን መጥለፍ ( Hacking ) ፦ ይህ የኮምፒውተር ሲስተሞችን ያለፍቃድ ዘልቆ በመግባት የግል መረጃዎችን ማለትም እንደ የባንድ መርጃ እና የብድር ካርድ መረጃዎችን መስረቅ ማለት ነው።

ወንጀለኞቹ እነዚህን መርጃዎች ለምን ይጠቀሙባቸዋል ?

በአውስትራሊያ መረጃን በመስረቅ ከሚፈጸሙት ወንጀሎች መካከል በጣም የተለመደው የገንዘብ ጥቅምን ለማግኘት ፤የህክምና ወጪን ለማጭበርበር ፤ የጡረታ ተቀማጭን ለማጭበርበር ፤ ታክስ ለማጭበርበር እንዲሁም የልጆችን የመታወቂያ ለመስረቅ ነው ።

መረጃን በድብቅ ቀድተው የሚወስዱ ምን ሊያደርጉብት ይችላሉ የሚለው የሚወሰነው በሰበሰቡት ግላዊ መረጃዎች ይዘት እና ጥራት የሚወሰን ይሆናል።
በአውስትራሊያ የውድድር እና ተጠቃሚዎች ኮሚሽን (ACCC) ምክትል ሰብሳቢ ካትሪዮና ሎዊ

ወንጀለኞቹ አንድ ጊዜ ይህን መረጃ ካገኙ የሚከተሉትን ሊያደርጉ ይችላሉ ፦

· በስምዎ የብድር ካርድ ሊያወጡ ይችላሉ

· በስምዎ የባንክ ሂሳብ ማጠራቀሚያን ሊከፍቱ ይችላሉ

· የተለያዩ የገንዘብ ጥቅማጥቅሞችን በእርስዎ ስም ሊያመለክቱ ይችላሉ

· እዳ ውስጥ ይከትዎታል ( ለምሳሌ የእርስዎ የብድር ወይም የተቀማጭ ካርድ በመጠቀም እቃዎችን ይገዛሉ )ወይም ብድርን ይወስዳሉ

· የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በስምዎ ያመለክታሉ ( ለምሳሌ ፦ የቤት ማመልከቻ ፤ የታክስ ፤ የገቢ ድጎማ ክፍያ ፤ የስራ ፈላጊዎች ክፍያ ፤ የልጆች ክፍያ )

· በስምዎ የመንጃ ፍቃድን ያወጣሉ

· በስምዎ መኪናን ያስመዘግባሉ

· ቅጥርን / ወይም ስራን በርስዎ ስም ይጠይቃሉ

· ፓስፖርት በስምዎ ያመለክታሉ

· የስልክ ኮንትራት በስምዎ ያመለክታል

ሳራ ካቫንጋ የ IDCARE, በአውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ የብሄራዊ ማንነት እና ሳይበር ድጋፍ አገልግሎት ማናጀር ናቸው።

“ የእጅ( ሞባይል ) ስልክዎ ድንገት መስራቱን ካቆመ እና ወደ SOS ከተለወጠ፤ ሌላ ሰው የእርስዎን የግል መረጃዎች በመውሰድ ሌላ ቁጥር ሊያመለክት እና አካውንትዎን ወደሌላ ሊያስተላልፈ እየሞከረ እንደሆን የሚያሳይ ጠቋሚ ነው።” ሲሉ ወ/ሪት ካቫንጋ ያስረዳሉ ።

Businesswoman using laptop and mobile phone logging in online banking account
Turn on two-factor authentication on your banking, email, and social media accounts. Source: Moment RF / Oscar Wong/Getty Images

ታዲያ ራስዎን እንዴት መከላከል ይችላሉ ?

እንደ ዶ/ር ሎዊ ምክር ከሆነ ለማያውቋቸው ድረ-ገጾች እና ኦን ላይን መደብሮች የግል መረጃዎች ከመስጠታችሁ በፊት ደግመው በጥንቃቄ ማሰብ ይኖርብዎታል ።
አጠራጣሪ የሆኑ የቴክስት መልክቶችንም ሆነ ኢሜሎች አይክፈቱ ፤ተያይዘው የሚመጡ ሊንኮችንም አይጫኑ። የቴክስት መልክቶችንም ሆነ ኢሜሎች ያጥፏቸው ።
Catriona Lowe, Deputy Chair, ACCC 
“ ከአንድ ድርጅት መረጃ ከደረሰዎት ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ በውስጡ ያሉትን መልክቶችንም ሆነ ኢሜሎች አይጠቀሙ ። ገለልተኛ የሆን ምንጭን በመጠቀም ያረጋግጡ ።” ሲሉ ዶ/ር ሎዊ ይመክራሉ

ወ/ሪት ካቫንጋ በበኩላቸው ስልክ እየደወሉ የግል መረጆዎችን ከሚጠይቁ ሰዎች መጠንቀቅ አለባችሁ ይላሉ ።

“ ስልክ በመደወል ኮምፒውትርዎን እንዲጠቀሙ ወይም የእጅ ስልክዎን ይለፍ ወይም አክሰስ ከሚጠቁ ሰዎች ይጠንቀቁ ፤ በተጨማሪም አፖችን ወይም ፕሮግራሞችን በርስዎ ኮምፒውተር ላይ ለመጫን ይለፍ ወይም አክሰስ በፍጹም እንዳይሰጡ ። ” ይላሉ

ወ/ሪት ካቫንጋ አክለውም “ የሚያነጋግሩት ሰው ትክክለኛ መሆኑን ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ መሆን ይኖርብዎታል ። ”
በተጨማሪም የተለየ እና ጠናካራ የይለፍ ቁል (ፓስዎርድ) ሊኖርዎ ይገባል ፤ ለእያንዳንዱ ኦን ላይን አካውንት የተለያየ ፓስወርድ ሊኖርዎት ይገባል ፤አንድ ፓስወርድን ሁለት ጊዜ በፍጹም አይጠቀሙ ።

በተጨማሪም ጉዞን በሚያደርጉ ጊዜ መረጃዎችን በቤትዎ ውስጥ ድብቅ በሆን ስፍራ ማስቀመጥ ይኖርብዎታል። ደግመው የማይጠቀሙባቸውን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ ያጥፏቸው ።

Internet troll
Cybercriminals crack weak passwords – there are even software that guesses billions of passwords per second. Credit: Peter Dazeley/Getty Images

የማንነት መታወቂያዎ ተሰርቋል ብለው ካመኑ ምን ማድረግ ይኖርብዎታል ?

አብዛኛዎች መታወቂያዎቻቸው የተሰረቁባቸው ሰዎች እንዴት ሊሆን እንደቻለ አያውቁም ።

ወ/ሪት ካቫንጋ እንደሚሉት መታወቂያዎቻችን በሌሎች ሰዎች እጅ መግባታቸውን የሚያሳዩ ምልክቶችን ንቁ ሆኖ መከታተል ያስፈልጋል ።

በተጨማሪም መታወቂያዎቻችን ተሰርቀዋል ብለን ከተጠራጠርን IDCARE ማነጋገር ያስፈልጋል ። በዚያ ያሉ አማካሪዎቹም ምን ማድረግ እንዳለብዎ ደርጃ በደረጃ ያሳያዎታል ።

በተጨማሪም ተገቢ የሆኑ ድርጅቶችን በፍጥነት ማነጋገር አስፈለጊ ነው ፤ ከዚያም የኦን ላይን አካውንትን መፈተሽ ያስፈልጋል ሲሉ ካቫንጋ ያስረዳሉ ።

የብድር ሪፖርት ይፋ እንዳይሆን እንዴት መጠየቅ ይቻላል ?

የማንነት መታወቂያ ስርቆት ተፈጽሞብኛል ብለው ካመኑ የሚመለከታቸውን የብድር ሪፖርት ካምፓኒዎችን በማግኘት የብደር ሪፖርትዎ ላይ ክልክላ ወይም እግድ ማስደረግ ይችላሉ ።

በሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ከፍተኛ መምህር የሆኑት ዶ/ር አንድሪው ግራንት እንደሚሉት ፤ አበዳሪ ድርጅቶች ቀድሞ የነበረዎትን የብደር ታሪክ እንዳይጠይቁ ገደብን በማስደረግ፤ ለብደር ማመልከቻዎ እንቅፋት እንዳይሆንብዎት ማድረግ ይቻላል።

Financial Wellness Credit Scores
A low credit score can hurt your ability to take out a loan, secure a good interest rate, or increase a credit card spending limit. Source: AP / John Raoux/AP
በአውስትራሊያ ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉት ሶስት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን እነሱም , , እና .ናቸው።
ይህንን ለማድረግ የሚያስፈልገው በቀጥታ በድረ-ገጻቸው ማመልከት ነው።

“በአውስትራሊያ እያንዳዱ የብድር ሪፖርት ቢሮዎች ስለእርስዎ መረጃ አላቸው ፤ የብድር ሪፖርትዎን ማንም እንዳያገኘው የሚፈልጉ ከሆነ ማመልከቻዎትን በማስገባት ማስቆም ይችላሉ” ሲሉ ዶ/ር ግራንት ይናገራሉ።

የመጀመሪያዎቹን 21 ቀናት የብድር ሪፖርት ክልከላ ገደብን በተመለከተ መረጃዎችን ያስቀመጠ ሲሆን ፤ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እስከ 12 ወራት ድረስ እንዴት ማስረዘም እንደሚቻል ወይም ሙሉ ለሙሉ ማንሳት እንደሚቻል ጨምሮ ያስረዳል።

ወ/ሪት ካቫንግ እንድሚሉትም የብድር ሪፖርትዎን ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ቢመለከቱ ህጋዊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች መከናወን አለመከናወናቸውን በቀላሉ መለየት ይችላሉ ።

“ ይቁሙ ፤ ያስቡ ፤ ይከላከሉ ።”

የትኛውንም አይነት ጥንቃቄን ቢወስዱ የማንነት መታወቂያ ስርቆት በማንኛው ሰው ላይ ሊጋጥም ይችላል።

ዶ/ር ሎዊ እንደሚሉት አጭበርባሪዎች( ስካመርስ) ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የተራቀቁ ሆነዋል ። ስለሆነም ሰዎች ሶስት ቃላትን ማስታወስ ይኖርናቸዋል ፤ ይቁሙ ፤ ያስቡ ፤ ይከላከሉ የሚሉትን ።

“ ይቁሙ ፦ የግል መረጃዎችዎን ወይም የኮምፒውተር መግቢያ አክሰስ ለማንም አይስጡ ፤ ያስቡ ፦በወዲያኛ በኩል ያለውን ወይም የሚከናወነውን አውቀዋለሁ ብለው ያስቡ ? ከዚያም ይከላከሉ ፦ የአጭበርባሪዎች ( ስካመርስ) ሰለባ ሆኛለሁ ብለው ከተጠራጠሩ ለ IDCARE ፤ ባንክን እና Scamwatch, ሪፖርት ያድርጉ።” ሲሉ ዶ/ር ሎዊ ያስረዳሉ ።

ተጨማሪ መረጃዎች

· አጭበርባሪዎችን ( ስካመርስ) በተመለከተ ሪፓርት ለማቅረብ ኦንላይን ቅጽ  ይሙሉ ወይም  ሪፖርት ያድርጉ ።

· የማንነት መታወቂያ ስርቆት ደርሶብኛል ብለው ከተጠራጠሩ   በ1800 595 160 (Aus) or 0800 121 068 (NZ) በስልክ ያነጋግሩ ።

· የማንነት መታወቂያ ስርቆት ወንጀልን እና መጭበርበርን በተመለከተ ለሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች በ   ይገኛል ።

Share