አንኳሮች
- አብይ ጾም ፤ ሁዳዴ ፤ ጾመ ኢየሱስ
- ጾም ለሁሉም አማኒ ግዴታ ነውን ?
- በጾም ወቅት ከአማኒያኑ ምን ይጠበቃል ?
መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ወደ ሀይማኖታዊው አለም ለመጓዝ ፈር የቀደዱላቸው የድጓ መምህር የነበሩት አባታቸው መላከ ሰላም ጥኡመ ልሳን ይልማ እንደሆኑ ይናገራሉ ።
በዝዋይ ገዳም ክህነትን ፤ ቅዳሴን እና ሳታትን ከተማሩ በኋላም ወደ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመሄድ የዲግሪ ፕሮግራምን መከታተላቸውን ነግረውናል። ወደ አውስትራሊያ ከመምጣታቸውም በፊትም በአዲስ አበባ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሀላፊ በመሆን ለ17 አመታት አገልግለዋል ። መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ላለፉት አምስት አመታት እና አሁንም በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።