አንኳሮች
- የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት መስኮች በሶስት የተፈረጁ ናቸው፤ የመንግሥት፣ የካቶሊክና የግል
- አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ዝንቅ ቢሆኑም፤ በተለይም የግልና ካቶሊክ ዘርፎች የአንድ ወጥ ፆታ ትምህርት ቤቶች አሏቸው
- ውድ የትምህርት ቤት ክፍያ ሁሌም ለልጅዎ የተሻለ የትምህርት ውጤት ያስገኛል ማለት አይደለም
- ተማሪዎች በማናቸውም ጊዜ ትምህርት ቤት መቀየር ይችላሉ
የአውስትራሊያ የትምህርት ሥርዓት በሶስት ዘርፎች የተከፈሉ ናቸው፤ የመንግሥት እንዲሁም የሕዝብ ትምህርት ቤት ተብለው የሚታወቁት፣ ካቶሊክ ትምህርት ቤቶችና የግል ትምህርት ቤቶች ናቸው።
ሶስት ዘርፎች
የመንግሥት፣ ካቶሊክና የግል ትምህርት ቤቶች በእያንዳንዱ ክፍለ አገር የሚተዳደሩት በተመሳሳይ የአስተዳደር አካላት ነው።
የኒው ኢንግላንድ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ሳሊ ላርሴን "ሁሉም ለተማሪዎች የሚያቀርቡት ተመሳሳይ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ነው፤ መምህራኑም ለማስተማር ይሁንታን የሚያገኙት በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ አልፈው ነው። ልዩነቱ በተወሰኑ ዘርፎች ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት የገንዘብ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ነው" ይላሉ።
በመንግሥት የሚደጎሙ ትምህርት ቤቶች ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት እንዲሆኑ መንግሥት ግድ ይላል። ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ አይደሉም፤ ነፃ ናቸው። ወላጆች ለትምህር ቤት አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች በፈቃደኝነት $100 አንዳንዴም መጠነኛ ተጨማሪ አስተዋፆ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ።
ልጅዎን ካቶሊክ ትምህር ቤት ለማስተማር በዓመት $5000 ያህል ወጪን ይጠይቅዎታል።
ተማሪዎች በግል ትምህርት ቤት ዘርፍ ለመማር $30,000 ወይም ከዚያም በላይ በዓመት መክፈል ይጠበቅባቸዋል።ዶ/ር ሳሊ ላርሰን፤ በኒው ኢንግላንድ ዩኒቨርሲቲ መምህር

Approximately 70% of primary and 60% of high school aged students are educated within the government sector. Credit: JohnnyGreig/Getty Images
ቤተሰብዎ ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል?
በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፋከልቲ ፕሮፌሰር ኢሜሪታ ሄለን ፎርጋስዝ “ከምርጫ አኳያ ለወላጆች ያለው ልዩነት መንግሥታዊ ያልሆኑ ማለትም የግል ትምህርት ቤቶችን ክፍያዎች መክፈል ይችላሉ ወይም አይችሉም ነው" ይላሉ።
ልጅዎ ሃይማኖታዊ ትምህርት በሚሰጥበት ትምህርት ቤት በትምህርቱ እንዲገፋ የሚሹ ከሆነ ምርጫዎ ሰፊ ነው ፤ እንዴት ቢሉ የተለያዩ የሃይማኖት ቡድኖች በተለያዩ ከፍለ አገራት ትምህርት ቤቶች አሏቸውና።በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፋከልቲ ፕሮፌሰር ኢሜሪታ ሄለን ፎርጋስዝ
በመንግሥት ትምህርት ቤት የሃይማኖት ትምህርት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የተካተተ አይደለም። ይሁንና፤ የሃይማኖት ድርጅቶች ሃይማኖታዊ ትምህርትን በሥርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞቻቸው እንዲያካትቱ ይፈቀድላቸዋል።
የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ትምህርት እየሰጡ ማናቸውም ዓይነት እምነቶችን የሚከተሉ ቤተሰቦችን ይቀበላሉ። ማኅበረሰብን በማገናኘትና በዲሲፕሊን በማነፅ የሚታወቁ ሲሆን፤ ክፍያቸውም ከግል ትምህርት ቤቶች ያነሰ ነው።
የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያዎቻቸው ብቻ ሳይሆን ከፍ የሚለው ድንገት ብቅ የሚሉ ድብቅ ወጪዎችም እንዳሏቸው ዶ/ር ላርሰን ሲያመላክቱ፤
“እንደ የግድ ተካች የሆኑ ተጨማሪ የሥርዓተ ትምህርት እንቅስቃሴዎች፣ በጣሙን ውድ የሆኑ የተማሪዎች የደንብ ልብስና ግድ የሚሉ የቴክኖሎጂ ግዢዎች መኖራቸውን ልብ ሊሉ ይገባል"
“ያንን መንገድ ተከትለው እየሔዱ ያሉ የተወሰኑ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች አሉ። የቴክኖሎጂ ግዢን ግድ ይላሉ፤ ይሁንና የቴክኖሎጂ ምርቶችን ለልጆቻቸው የመግዛት አቅሙ ለሌላቸው ወላጆች ድጎማዎችን በማድረግ ረገድ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተሻሉ ናቸው”

The benefits of educating girls and boys separately remain contentious and academic results may not differ significantly. Credit: Fly View Productions/Getty Images
ልጅዎን ወደ አንድ ወጥ ፆታ ትምህርት ቤት ለመላክ ያስባሉ?
ልጃገረዶችንና ወንዶች ልጆችን በተናጠል ማስተማሩ አወዛጋቢ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ከትምህርት ውጤት አኳያም የላቀ ውጤት የሚያሳይ አይደለም፤ ከማኅበራዊ ግንኙነት አኳያ የተወሰኑቱ ያንን የሚመርጡ አሉ። ምናልባትም ይህ ዓይነቱ ምርጫ ከሃይማኖታዊ እምነቶች ጋር ሊያያዝ ይችላል።
አብዛኛዎቹ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች የዝንቅ መማሪያ ናቸው፤ ማለትም ወንዶች ልጆችንና ልጃገረዶችን በአንድ ላይ የሚያስተምሩ።በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፋክሊቲ ፕሮፌሰር ኢሜሪታ ሄለን ፎርጋስዝ
ለምሳሌ ያህል፤ በካቶሊክና የግል ትምህርት ቤቶች የተመሠረቱ የተነጠሉ ትምህርት ቤቶች ልጃገረዶችን ወይም ወንዶች ልጆችን በፆታ ለይተው ያስተምራሉ። በሌላ በኩል፤ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በአብዛኛው ክፍለ አገራት ሁለቱንም ፆታዎች አዛንቀው ያስተምራሉ።
ይሁንና ኒው ሳውዝ ዌይልስ በተለየ መልኩ 30 የነጠላ ፆታ ማስተማሪያ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ሲኖሩት፤ ቪክቶሪያ ውስጥ ቁጥራቸው ያን ያህል ባይበዛም የተወሰኑ የነጠላ ፆታ ማስተማሪያ ትምህርት ቤቶች አሉ። እኒህ የመንግሥት ነጠላ ፆታ ተኮር ትምህርት ቤቶች ግና በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች መማሪያ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን ከግምት ውስጥ በሚያስገቡበት ወቅት የግል ትምህርት ቤቶች በገበያ የቅስቀሳ ዘመቻዎቻቸው ወላጆች ላይ በማተኮር "ልጆቻቸው በመንግሥት ሥርዓተ ትምህርት የተሟላ ትምህርት አያገኙም የሚለው ጭንቀታቸውን የሚያባብሱ መሆኑን" ልብ እንዲሉ ዶ/ር ላርሰን ያሳባሉ።

Students can change school at any time Credit: JohnnyGreig/Getty Images
የግል ትምህርት ቤቶች የተሻሉ ናቸው?
በአንደኛ ደረጃ 70% ያህል በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ 60% ተማሪዎች የተማሩት በመንግሥት ትምህርት ቤት ነው።
ወጪዎቹ እንዳሉ ሆነው ልጆችዎን ወደ ግል ይሁን ወይም ወደ ካቶሊክ ትምህርት ቤት ለመላክ ሲወስኑ የትምህርት፣ ባሕላዊና ቤተሰብ የሚሻቸው ውጤቶች በውሳኔ ላይ ሚና አላቸው። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ዘንድ ተማሪዎችን ለማስመዝገብ በገበያ ቅስቀሳ ዘመቻዎች የሚታዩ ብርቱ ፉክክሮች ማስረጃዎች ናቸው።
በመንግሥት ትምህርት ቤትች ዘንድ የገበያ ፉክክር አለመኖር ማለት፤ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከግል ትምህርት ቤቶች ያነሱ ናቸው ማለት አይደለም።ዶ/ር ሳሊ ላርሰን፤ በኒው ኢንግላንድ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ፋክልቲ መምህር
መልሱ በሶስቱም ዘርፎች እጅግ ማለፊያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ ነው።
የቤት ሥራዎን ይሥሩ
ትምህርት ቤቶች እነሆኝ የሚሏቸውን ይመርምሩ። ውድ የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ማለት ልጅዎ የተሻለ ትምህርት ያገኛል ማለት እንዳልሆነ ፕሮፌሰር ኢሜሪታ ፎርጋስዝ ልብ ሲያሰኙ፤
“ትምህርት ቤት በሚያፈላልጉ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ ቀዳሚው መሥፈርት መሆን የሚገባው የልጃቸውን ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑ ላይ ሊሆን ይገባል” ባይ ናቸው።
የትምህርት ቤት ጉብኝት ጥያቄ ያቅርቡ፤ ጠንካራ ጥያቄዎችንም ለመጠየቅ አይፍሩ። ልጅዎ የተለየ ፍላጎቶች ወይም የሚያስፈልጉት ልዩ ነገሮች ካሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ያንን ሊያሟሉ አይችሉምና ጥልቅ ምርምር ያድርጉ።
ፕሮፌሰር ኤሜሪታ ፎርጋስዝ በማንኛው ወቅት ውሳኔዎን ሊለውጡ እንደሚችሉ ልብ ሊሉ እንደሚገባ ሲያሳስቡ፤
“ልጆችዎ በትምህርት ጊዜያቸው መልካም ውጤቶችን ካላመጡ፤ ከትምህርትና ማኅበራዊ ግንኙነት አኳያ ትምህርት ቤት ቢቀይሩ መልካም ይሆናልን? ብለው ደግመው ይከልሱ” ብለዋል።