ድምፅ ለመስጠት መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አውስትራሊያውያን በቅርቡ ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል ለነባር ዜጎች ዕውቅና እንዲቸርበትና ለነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ በመባል የሚታወቀው አካል ውክልናን እንዲያገኝ ውሳኔያቸውን እንዲያሳልፉ ጥሪ ይቀርብላቸዋል።
ድምፅ ለፓርላማ ነባር ዜጎች ላይ ጉዳት የሚያሳድሩ ጉዳዮችና ሕጎችን አስመልክቶ ለመንግሥት ምክርን የሚሰጥ አንድ የተመረጠ ቡድን ነው።
የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን (አምኮ) ቃል አቀባይ ኢቫን ኢኪን-ስሚዝ ስለ ሕዝበ ውሳኔው ሂደት ጠቀሜታ ሲያስረዱ፤
“ሕዝበ ውሳኔ አንድ ጉዳይን አስመልክቶ የአውስትራሊያን ሕገ መንግሥት በመለወጥና አለመለወጥ ላይ የሚሰጥ አገር አቀፍ ድምፅ ነው” ብለዋል።
ሕገ መንግሥትን መለወጥ የሚቻልበት አንድ ብቸኛ መንገድ በሕዝብ ድምፅ አማካይነት ነው። ፓርላማ ያንን የማድረግ ስልጣን የለውም።ኢቫን ኢኪን-ስሚዝ
ሕገ መንግሥት የፌዴራል መንግሥቱ እንደምን ተግባሩን እንደሚያከናውን ይመራል። በክፍለ አገራትና የፌዴራል ፓርላማዎች የሕጎች አቀራረፅን አካትቶ፤ የጋራ ብልፅግና፣ ክፍለ አገራትና ሕዝብ ግንኙነታቸው እንደምን እንደሚሆን ይወስናል።
ሕዝብ የሚከተለውን ጥያቄ አስመልክቶ ‘ይሁን’ ወይም ‘አይሁን’ ብለው እንዲመልሱ ይጠይቃል፤
“የተረቀቀ ሕግ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ድምፅን በመመሥረት ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል ዕውቅና መቸር።
ለእዚህ ረቂቅ ማሻሻያ ይሁንታዎን ይቸራሉ?”

A supporter is seen with the Aboriginal flag painted on her face in support of the vote hold placards during a Yes 23 community event in support of an Indigenous Voice to Parliament, in Sydney, Sunday, July 2, 2023. (AAP Image/Bianca De Marchi) NO ARCHIVING Source: AAP / BIANCA DE MARCHI/AAPIMAGE
አቶ ኢኪን-ስሚዝ ይህን ሲያስረዱ “ሕዝበ ውሳኔ እንዲያልፍ፤ አብላጫ የ'ይሁን' አገር አቀፍ ድምፆችንና የክፍለ አገራት አብላጫ 'ይሁን' ድምፆችን ማግኘት ያሻል። ቢያንስ ከስድስቱ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት አራቱ 'ይሁን' ብለው ድምፃቸው ሊሰጡ ይገባል።”
“የአውስትራሊያ መዲና ግዛትና የሰሜናዊ ግዛት ድምፅ እንደ ማንኛውም የአውስትራሊያ ዜጋ ሁሉ 'ይሁን' ወይም 'አይሁን' በሚል የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ይሠፍራል። ግና የሚቆጠረው በአገር አቀፍ አብላጫ ድምፅ እንጂ ሕዝበ ውሳኔው እንዲያልፍ ሁለተኛ መሰናክል በሆነው የክፍለ አገራት ድምፅ አይደለም። እናም፤ የአገረ ግዛት ድምፆች በጣሙን ጠቃሚነታቸው ለአገር አቀፍ አብላጫ ድምፅ ነው" ብለዋል።
የተረቀቀው የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ተወካዮች ቡድን ፆታዊ ሚዛንን የጠበቀ፣ በነባር ዜጎች ማኅበረሰባቸውን ወክሎ እነሱ ላይ ጉዳቶችን ሊያደርሱ በሚችሉ ሕጎች ላይ ፓርላማውን እንዲያማክሩ የተመረጠ ይሆናል።
READ MORE

What is Welcome to Country?
ሕጎችን የማሳለፍ፣ ውሳኔዎችን በድምፅ የመሻር ወይም የገንዘብ ድጎማን የመመደብ ስልጣን የለውም። ፓርላማው በመደበኛ ተግባሩ የሚቀጥል ይሆናል።
ሜጋን ዴቪስ የኮብል ኮብል ሴትና በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ የሕገ መንግሥታዊ ሕግ ፕሮፌሰር ናቸው።
የአቦርጂናልና ቶረስ ደሴት መሽመጥ ሰዎች ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና እንዲቸራቸው የድምፅ ለፓርላማ ረቂቅን ያቀረበው ጠበብት መድረክ አባል ነበሩ።
ሌሎች አገራት ተመሳሳይ ሞዴሎችን በስኬታማነት ግብር ላይ እንዳዋሉ ሲናገሩ፤
“ይኼ መንግሥታት ሕጎችን ሲነድፉና ፖሊሲዎችን ሲቀርፁ የነባር ዜጎችን ድምፅ መስማት በመላው ዓለም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ውስጥ በጣሙን የተለመደ ማሻሻያ ነው" ብለዋል።
አውስራሊያ ውስጥ ክፍተትን መዝጋት እንዲሳኑን ምክንያቶች ከሆኑት አንዱ መንግሥት የሚቀርፃቸው ሕጎችና ፖሊሲዎች የሚመለከታቸውን ማኅበረሰባት የሚያማክረው በጣሙን ውስን በሆነ ወቅት መሆኑ ነው።ፕሮፌሰር ሜጋን ዴቪስ
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የተለያዩ ፖለቲካዊ አተያዮች አሏቸው፤ የተወሰኑቱ በድምፅ ለፓርላማ ረቂቅ የሚስማሙ አይደሉም።
ይህም የድምፅ ለፓርላማ የነባር ዜጎችን ችግሮች ለመፍታት የሚፈይደው ጥቂት ነው የሚሉትን የነባር ዜጎች ፖለቲከኛዋን የሰሜናዊ ግዛት የገጠር ሊብራል ሴናተር ጃሲንታ ፕራይስንና የቀድሞው የሌበር ፓርቲ ፕሬዚደንት ዋረን ማንዲንን ያካትታል።

Country Liberal Party Senator Jacinta Nampijinpa Price walks with a young Indigenous woman wearing an Australian flag ahead of a press conference at Parliament House in Canberra, Wednesday, March 22, 2023. (AAP Image/Lukas Coch) NO ARCHIVING Source: AAP / LUKAS COCH/AAPIMAGE
“በሕዝበ ውሳኔው ቀን በሺህዎች የሚቆጠሩ የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁ ሆነው ይጠባበቃሉ።
“እንዲሁም፤ የቅድመ ምርጫ ቀን የምርጫ ጣቢያዎች ከዋነኛው ምርጫ ቀን በሳምንታት ቀደም ብለው ለድምፅ መስጫነት ዝግጁ ይሆናሉ። እናም፤ በዋነኛው የምርጫ ዕለት መገኘት የማይችሉ ከሆነ፤ የቅድመ ምርጫ ማዕከል በመገኘት ድምፅዎን መስጠት ይችላሉ። የባሕር ማዶና የርቀት ተንቀሳቃሽ ምርጫ ጣቢያዎች፣ የፖስታ ምርጫ፤ እንዲሁም ማየት ለተሳናቸው የስልክ ድምፅ ምርጫ መስጫዎች ስንዱ ይሆናሉ” ብለዋል።
የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ተወካይ ፓት ኮላናን ለመራጮች ስንዱ ስለሆኑ የተለያዩ ምንጮች ሲናገሩ፤
"ከ30 በላይ በሆኑ ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ቋንቋዎች የተተረጎሙ የመረጃ ምንጮች፤ በድረ ገፃችንና በስልክ የአስተርጓሚ አገልግሎቶች በኩል ይገኛሉ"
ብለዋል።
አክለውም፤ ለሌሎች ምርጫዎች የተመዘገበ ግለሰብ ለሕዝበ ውሳኔም ድምፅ ለመስጠት መመዘኛን የሚያሟላ ይሆናል።
ስለሆነም፤ እንደማንኛውም ምርጫ ድምፅ መስጠት ግዴታ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
አያይዘውም “የአውስትራሊያ ዜግነት ያለዎት ሊሆኑ ይገባል፤ ይሁንና የመኖሪያ ሥፍራ ቀይረው ከሆነ ወይም ስለ መመዝገብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ aec.gov.au ድረ ገፃችንን እንዲጎበኙና የምዝገባ ዝርዝሮችን እንዲያረጋግጡ አሳስባለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ኢኪን-ስሚዝ ግለሰቦች በክርክር ላይ መሳተፍና ድምፃቸውንም ከመስጠታቸው በፊት ምርምር ቢያደርጉ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁም ብለዋል።
አያይዘውም “ስለ ጉዳዩ በእጅጉ ያስቡ። ሕዝበ ውሳኔን የሚለየው ይህ ነው። ለመምረጥ ስለሚሿቸው ዕጩዎች ወይም ጉዳይ አይደለም የሚያስቡት" ሲሉ አሳስበዋል።
ምርምርዎን በጥንቃቄ ያካሂዱ። ድምፅ መስጠት የሚሹት ለ 'ይሁን' ወይም 'አይሁን' ስለመሆኑ ያስቡ። ወደ ምርጫ ሳጥን ሲያመሩ በቂ ግንዛቤ ያለዎት መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ።ኢቫን ኢኪን-ስሚዝ
ውጤቱ አሳሪ መሆኑን ልብ ማለት ወሳኝ ነው የሚሉት አቶ ኮላናን ሲናገሩ፤
“በየትኛውም መንገድ ይምረጡ፤ ድምፅዎን ማሰማቱ በጣሙን ጠቃሚ ነው። እንደ አውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ሰዎች ለማንም ይምረጡ ለማን እኛን ግድ አይለንም። ድምፅ ሰጪ ስለሆኑ ሰዎች ግና እናስባለን፤ ስለ እውነት ድምፅን መስጠት መቻል ልዩ ነገር ነው። እናም፤ ሰዎች ያንን በትኩረት ሊወስዱት ይገባል” በማለት አሳስበዋል።
የ2023 የነባር ዜጎችን ድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔን የነባር ዜጎችን አተያዮችን አስመልክቶ ከ NITV እና ከአጠቃላይ SBS አውታረ መረብ መረጃዎችን ያግኙ። የ ድረ ገፅ፤ መጣጥፎችን፣ ቪዲዮችንና ፖድካስቶችን ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ወይም በቀጥታ ስርጭት ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንታኔዎችን፣ ዘጋቢዎችንና መዝናኛዎችን በነፃ ከ ያግኙ።