አንኳሮች
- ረመዳን በእስልምና ውስጥ ቅዱስ ወር በመባል የሚታወቅ ሲሆን ጤነኛ የሆኑ እና እድሜያቸው ለአቅመ አዳም እና ሄዋን የደረሱ የእምነቱ ተከታዮች ከንጋት እስከ ጸሐይ መጥለቂያ የሚጾሙት ነው ፤
- ኢድ አልፈጥር ቅዱስ ወር ከተጠናቀቀ በሗላ የሚከበር የሶስት ቀን በአል ነው፤
- አውስትራሊያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ በአልን ሲያከብሩም ድንቅ የሆነ ባህላቸው የሚያሳዩበት ነው ፤
አውስትራሊያ በአለም ካሉት 1.97 ቢሊዮን የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ለ 813.000 ዎች የመኖሪያ ቤታቸው ነች ።
ከተለያዩ ባህሎች እና እምነቶች የመጡ ጓደኞችን ማፍራት ወይም የስራ ባልደረቦች ጋር መስራት መድብለ ባህል በሆነችው አውስትራሊያ በጣም የተለመደ ነው ።
በመድብለ ባህል ማህበረስብ ውስጥ ሲኖሩም የሌሎችን እምነት እና ባህል መረዳት እና ማድነቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ።
በአውስትራሊያ እና በመላው አለም የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች አንድ ወር የሚፈጀውን የጾሙን ወቅትም ጀምረዋል ።
![Man praying in the sunset (Pixabay).jpg](https://images.sbs.com.au/12/06/0fe94722419eb68fc5f32d39a358/man-praying-in-the-sunset-pixabay.jpg?imwidth=1280)
The Islamic Hijri calendar, is based on the cycles of the moon around the Earth. Credit: Pixabay
ረመዳን ምንድን ነው ?
ረመዳን በእስልምና ሉናር የቀን መቁጠሪያ ውስጥ በዘጠነኛ ወር ላይ የሚገኝ ሲሆን ጤነኛ የሆኑ እና እድሜያቸው ለአቅመ አዳም እና ሄዋን የደረሱ የእምነቱ ተከታዮች ከንጋት እስከ ጸሐይ መጥለቂያ የሚጾሙት ነው ።
ተባባሪ ፕሮፌሰር ዙሊሃን ከስኪን በሜልበርን ቻርለስ ስቱዋርት ዪኒቨርሲቲ የእስልምና ጥናት እና ስልጣኔ ማእከል ምክትል ሀላፊ እንደሚሉት ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች በረመዳን ወቅት ከፍተኛ የሆነ ሀይማኖታዊ ትምህርትና እድገት እንዲሁም ስነ ምግባር የሚያሳዩበት ነው ።
ረመዳን ለእስልምና እምነት ተከታዮች እጅግ በጣም ቅዱስ የሚባል ወር ሲሆን ይህም ወሩን በጣም የተለየ እንዲሆን አድርጎታል ።ተባባሪ ፕሮፌሰር ዙሊሃን ከስኪን በሜልበርን ቻርለስ ስቱዋርት ዪኒቨርሲቲ የእስልምና ጥናት እና ስልጣኔ ማእከል ምክትል ሀላፊ
የእስልምና የቀን መቁጠሪያ ሂጅራ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ፤ የተመሰረተውም ጨረቃ በምድር ዙሪያ በምታደርገው ዙር ላይ ነው ። ይህም ከጸሐይ አመት ከ10 እስከ 12 ቀናት የሚያንስ እንደመሆኑ መጠን በእስልምና እምነት ዙሪያ የሚከናወኑ ልዩ በአላትም የመከበሪያ ቀናቸው ከአመት አመት የተለያዩ ናቸው ።
የዚህ አመት የቅዱስ ወር ረመዳንም ከማርች 22 እስከ አፕሪል 20 ባሉት ቀናት ውስጥ ሆኗል።
![Shot of a young muslim woman pouring drinks for her family](https://images.sbs.com.au/04/b6/51fe9ef14331836572ed30cb3586/gettyimages-1330024121-1.jpg?imwidth=1280)
A meal with loved ones during Ramadan. Source: iStockphoto / PeopleImages/Getty Images/iStockphoto
የእስልምና እምነት ተከታዮች ጾምን መጾም ለምን ያስፈልጋቸዋል ?
ጾም በእስልምና 5ቱ የእምነት አምዶች ከሆኑት ማለትም ጸሎት ፤ መስጠት ፤ ጾም እና ሃጅ ወይም ቅዱስ ቦታ መሄድ ከሚባሉት አንደኛው ነው።
በጾሙ ወቅትም የእስልምና እምነት ተከታዮቹ ሲጋራን ከማጨስ ፤ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ከመፈጸም ፤ ቁጣን ከማሳየት እና ክርክር ውስጥ በመግባት ከስነምግባር ውጭ የሆኑ ባህሪያትን ከማሳየት ራሳቸውን ይቆጥባሉ ።
ከዚህ በተጨማሪም ረዘም ያሉ የአምልኮ ልምምዶች ማለትም ጸሎት ፤ቁርአንን ማንበብ እና መረዳት እንዲሁም የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንዲሰሩ ይበረታታሉ ።በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጥጾሙን ከፈቱ (ካፈጠሩ) በኋላ ወደ መስኪድ ይሄዳሉ ።
ለሰው ልጆች የተለየ ክብርን እንድንሰጥ ፤ በድህነት ውስጥ ያሉትን ፤ የሚመገቡትን ለመግዛት የማይችሉትን ሰዎች ህይወት እንድንረዳ እንዲሁም ከተቀረው አለም ጋር ግንኙነት እንዲኖረን የምንማርበት ወር ነው ።በአውስትራሊያ ናሽናል ዩኒቨሪሲቲ የአረብ እና እስልምና ጥናት ማእከል ዳይሬከተር የሆኑት ፕሮፌሰር ካሪማ ላቺር
ከዚህ በተጨማሪም ከጸሎት እና ሐይማኖታዊ ጠቀሜታው ባሻገርም ጾም ለጤና ጠቀሜታም እንዳለው ፕሮፌሰር ላቺር ይናገራሉ ፤
“ ለአካላችን ጤንነት ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ፤ ምክንያቱም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የምግብ ዝውውር ያስተካክላል ፤ እንዲሁም በውስጣችን ያሉ የተመረዙ ነገሮች ያጸዳል ፤ይህም በሙከራ የተርጋገጠ ሲሆን በተለይም ቀኑን ሙሉ በመጾም አንድ ጊዜ ብቻ መመገብ ለአካላችን ጤና ጠቃሚ ነው። ”
![Friends gathering for eating dinner together](https://images.sbs.com.au/e5/36/33fc01ca4989b4b75916c9abd117/gettyimages-1209701666.jpg?imwidth=1280)
Healthy adult Muslims are required to fast from dawn to dusk during Ramadan. Source: Moment RF / Jasmin Merdan/Getty Images
ኢድ ምንድን ነው ?
የእስልምና እምነት ተከታዮቹ ወሩን በሙሉ ከጾሙ በኋላ የኢድ በአልን ያከብራሉ ።
ኢድ የአረብኛ ቃል ሲሆን ክብረ በአል ወይም በአል የሚለውን ቃል ይወክላል ። በእስልምና የቀን መቁጠሪያ ውስጥም ሁለት ኢድ ያለ ሲሆን ፤ ኢድ አል-ፈጥር እና ኢድ አል- አድሀ በመባል ይታወቃሉ ።
ኢድ አል-ፈጥር አነስተኛ ኢድ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የረመዳን ጾም ከተጠናቀቀ በኋላ ለሶስት ቀናት የሚከበር ነው።
ኢድ አል-ፈጥር የእስልምና እምነት ተከታዮች በረመዳን ወር ውስጥ ያስመዘገቧቸውን መልካም ተግባሮች የሚያከብሩበት ነው ።ዶ/ር ዙሊሃን ከስኪን በሜልበርን ቻርለስ ስቱዋርት ዪኒቨርሲቲ የእስልምና ጥናት እና ስልጣኔ ማእከል ምክትል ሀላፊ
የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢድን ሲያስቡም ምጽዋትን እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ይህም ዘካት አል- ፈጢር በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ድሆች በአሉን ማክበር እንዲችሉ ያደርጋሉ ።
ፕሮፊርሰር ላቸር እንደሚሉትም ኢድ አል- ፈጢር “ በጋራ መሆንን እና ይቅር ባይነትን “ መሰረት አድርጎ የሚከበር ሲሆን የእስልምና እምነት ተከታዮን ማህበረሰብ መንፈስ በማነቃቃት ይቅር ባይነትን እንዲለማመዱ የሚያደርግ ነው ።
በተጨማሪም ልጆች ጥሩ ጊዜን እንዲያሳልፉ ፤ አዳዲስ ባልንጀሮችን እንዲያፈሩ እና ባሁሉን እንዲማሩ መልካም እድልን ይፈጥራል ።
![Tradicionalni muslimanski roditelji i njihova djeca dijele lepinju tokom iftara u Ramazanu](https://images.sbs.com.au/c0/89/681682f44d00981a036e2c4cc3e3/gettyimages-1376088706-1.jpg?imwidth=1280)
In most Islamic countries, Eid al-Fitr is a public holiday. Source: iStockphoto / Drazen Zigic/Getty Images/iStockphoto
በዚህ አመት የኢድ አል-ፈጥር በአል ጨረቃዋ እንደምትታይበት ቀን በአፕሪል 21 ወይም 22 ይከበራል ተብሎ ይጠበቃል ። አብዛኛዎቹ የእስልምና እምነት ተከታይ አገራት የኢድ አል-ፈጥር በአል የህዝብ በአክ ቀን ብላው ያከብሩታል ። ።
ኢድ አል- አድሀ በሌላኛው አጠራሩ እርድ የሚከናወንበት ቀን ወይም ታላቁ ኢድ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ፤የሚከበረውም አመታዊው የሀጅ ስነ ስርአት ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን ፤ ተምሳሌትነቱም አብርሃም የአምላኩን ፈቃድ ለመፈጸም ሲል ልጁን እስማኤልን ለመሰዋትነት ማቅረቡን የሚያሳይ ነው ።
![EID AL FITR SYDNEY](https://images.sbs.com.au/80/5f/5575fe514658a286bf9318184c3d/20190605001402853565-original.jpg?imwidth=1280)
Members of the Muslim community celebrate Eid al-Fitr, marking the end of the month-long fast of Ramadan with prayer at Lakemba Mosque in Sydney. Source: AAP / DEAN LEWINS/AAPIMAGE
አውስትራሊያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢድን እንዴት ያከብራሉ ?
የኢድ አል-ፈጥር በአል አካባበር የሚጀምረው በእስልምና የቀን መቁጠሪያ አስረኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ጠዋት በሚደረግ የተለየ ጸሎት ነው።
በጋራ የሚደረጉ የጸሎት ስነ ስርአቶች በየአካባቢው በሚገኙ መስኪዶች እና የማህበረሰብ ማእከላት የሚደርጉ ሲሆን ፤ በዚያም እርስ በእርስ ‘ ኢድ ሙባረክ ’ በትርጓሜውን ‘የደስታ ኢድ ’ ይሁንልን በማለት ሰላምታን ይለዋወጣሉ ።
ቤተሰቦች እና ጓደኞችም እርስ በእርስ የሚጠያየቁ ሲሆን ፤ ኢድን በህብረት ሰብሰብ ብሎ ማክበርም የተለመደ ነው ።
“ በአብዛኛው በቤተሰብ ደረጃ በጋራ የሚያከብሩት ፤ አንዱ ሌላውን የሚጎበኝበት እና ለበአሉ ተብለው የተዘጋጁ የተለያዩ ምግቦችን እና ጣፋጭ ኬኮችን እየተገባብዙ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በደስታ የሚያሳልፉበት ጊዜ ነው ። ” ሲሉ ፕርፕፌሰር ላቼር ይናገራሉ
ይሁንና በአውስትራሊያ የሚገኙ ከተለያዩ አገራት እና ባህሎች የመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች አካባበራቸው ይለያያል ።
![RAMADAN EID SYDNEY](https://images.sbs.com.au/c4/4f/5170fb764a5e807321f5d44ff854/20140728001003496059-original.jpg?imwidth=1280)
Large crowds filled the Mosque in Lakemba and lined the streets to mark the end of the holy month of Ramadan, Sydney. Source: AAP / JANE DEMPSTER/AAPIMAGE
እርሳቸው እንደሚሉት ከተለያየ አካባቢዎች በሚመጡት የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የባህል ልዩነቶች አሉ ። እንደ አውስትራሊያውያን የመድብለ ባህል ኢድ በአል አዘጋጅ ሰብሳቢነታቸው ስራቸውም የበአሉ ተካፋዮች ሁሉም በአንድነት ተሰባስበው እንዲያከብሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ።
“ አንዳንድ ሰዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ያበስላሉ ፤ እንዲሁም በኢድ ቀን የሚለብሷቸው የተለዩ አልባሳት አሏቸው ። ወደ በአሉ አከባበር ስንመጣም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ያሉ ሲሆን፤ የሚከናወኑ ክዋኔዎች የሚካተቱበት ይሆናል ። ” ሲሉ አቶ አዋን ያስረዳሉ ።
በኢድ በአል ወቅት የተለያዩ ክዋኔዎችን በአንድነት በማምጣት ለማካተተ እንሞክራለን ይህ ነው የአውስትራሊያ ውበት ፤ የተለያዩ ባህሎች በአንድ ላይ ማሳየት ።አሊ አዋን በአውስትራሊያም የመድብለ ባህል ኢድ በአል አዘጋጅ ።
ፕሮፌሰር ላቼር በዚህ የሚስማሙ ሲሆን አያይዘውም በአውስትራሊያ የሚደረገው የኢድ አከባበር ከሌሎች የእስልምና እምነት ተከታይ አገራት በበለጠ ዝንቅ እና ጠንካራ ነው ይላሉ ።
“ በአውስትራሊያ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ድንቅ የሚያደርጋቸው ፤ አብዛኛው በአላትን የሚከበሩት በማህበረሰብ መሰባሰቢያ ተቋማት እና የአካባቢ መስጊዶች ነው። ይህ ደግሞ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የማህበረሰብ አባላትን በአንድ ላይ እንዲሰባሰቡ ያደርጋል ። ” ብለዋል