ባዮብሊትዝ ምንድነው? ሳይንስን ለማገዝ እንደምን መሳተፍ ይችላሉ?

Participants in the Walpole Wilderness BioBlitz. Image: Rebecca Meegan-Lowe

Participants in the Walpole Wilderness BioBlitz. Image: Rebecca Meegan-Lowe

አውስትራሊያ የተለያዩ በርካታ እንሰሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች መኖሪያ ናት። በባዮብሊትዝ መሳተፍ በተለይም በተወሰነ አካባቢ ስለሚኖሩ ፍጡራን ለመመራመርና ሳይንሳዊ ዕውቀትን ለማስፋት ያስችላል።


ቁልፍ ነጥቦች
  • ባዮብሊትዝ ሳይንሳዊ ዕውቀታችንን እና አካባቢያዊ ግንዛቤያችንን ለማዳበር ያግዛል
  • ማንኛውም ሰው በባዮብሊትዝ መሳተፍ ይችላል
  • በባዮብሊፅ ወቅት የተሰበሰበ መረጃ ለሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች መጠቀሚያነት የብዝሃ ሕይወት ዳታቋት ላይ ይጫናል
አውስትራሊያ ከበረሃዎች፣ ሙቀታማ የዝናብ ደኖች፣ በረዷማ የአልፕስ ተራራዎችና የባሕር ዛፍ ደኖች ብዝኅ ሕይወት የበለፀገች ናት።

ስላሉት እንሰሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች አብዝተን ብናውቅም፤ ስለ አካባቢያችን በይበልጥ በተረዳን ቁጥር የተሻለ ክብካቤ ማድረግ ይቻለናል።

ባዮብሊትዝ ማንኛውም ሰው ሳይንሳዊ ግንዛቤን በማጎልበት የሚሳተፍበትና አዲስ የዕፅዋት ወይም እንሰሳት ዝርያዎችን ፈልጎ ለማግኘት የሚያስችል ዕድልን የሚቸር የዜጋ ሳይንስ እንቅስቃሴ ነው።
Participants in the Walpole Wilderness Bioblitz - Image Daemon Clark.jpg
Participants in the Walpole Wilderness Bioblitz - Daemon Clark
በባዮብሊትዝ ወቅት የተሳታፊ ሕዝባዊ አባላት ከሳይንቲስቶች ጋር በመሆን በተመደበላቸው ሥፍራ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የቻሉትን ያህል የዕፅዋትና እንሰሳት ዝርያዎችን ይመዘግባሉ።   

ዶ/ር ዴቪድ ኤሞንድስ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ የእንሰሳት ሐኪም ሲሆኑ፤ ነዋሪነታቸው   በሚያስተባብሩበት የምዕራብ አውስትራሊያ ደቡብ ባሕር ዳርቻ ዎልፖል ነው።

"የዎልፖል ዊልድርነስ ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ እርጥባማ ከሆኑቱ አካባቢዎች አንዱ ሲሆን፤ በዓለም ላይ በሌላ ሥፍራ የሌሉ የተለያዩ ዝርያዎችና ሥነ ምሕዳሮች ያሉበት ነው። ገና ያልተዳሰሰ መጠነ ሰፊ አካባቢ አለ፤ የተወሰኑት ፍጥረታት ከዳይኖሶሮች በፊት ምን ያህል ጊዜያት የኋልዮሽ ዘልቀው የነበሩ እንደሆኑና እኒያ አካባቢዎች ምን እንደሆኑ እንኳ አናውቅም። በእጅጉ ጠቃሚ የብዝኅ ሕይወት አካባቢ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ባዮብሊትዝ ሳይንስን ለማገዝ ማኅበረሰብን ያሰባስባል

ልክ እንደ ዎልፖል ሰው አልባ አካባቢ በዘመናት ከተለወጡ መጠነ ሰፊ የአውስትራሊያ አካባቢዎች አሁንም የምንማራቸው አያሌ ነገሮች አሉ። ዶ/ር ኤድሞንድስ፤ ማኅበረሰብን በባዮብሊትዝ ማሳተፍ ሰዎችን አንድ ላይ ያሰባስባል፤ ሳይንሳዊ አረዳድን ስለሚያግዝ የአካባቢያዊ ተፈጥሮ ግንዛቤን እንደሚቸር ይናገራሉ።

"ባዮብሊትዝ በጣሙን ራስን አስቻይ ነው፤ ሰዎች ከሌሎች አስተሳሰበ መልካም ከሆኑቱ ጋር አውታረ መረብ እንዲዘረጉ ያስችላቸዋል። ይሁንና እያንዳንዱ የተመዘገበ ምልከታ ተፅዕኖ እንዳለውና በተጨማሪ መረጃም ዕውቀታችንን በመገንባት ወደ ተሻለ አሠራራዊ ውጤቶች እንደሚያመራን መገንዘቡ በጣሙን ጠቃሚ ነው" ሲሉም ዶ/ር ኤድሞንድስ ያስረዳሉ።
Dr David Edmonds examining plant species in the Walpole wilderness - Image by Phil Tucak.jpg
Dr David Edmonds examining plant species in the Walpole wilderness - by Phil Tucak
በአብዛኛው የባዮብሊትዝ ኩነቶች የሚከናወኑት በአካባቢ ማኅበረሰብ፣ የተፈጥሮ ጥበቃና የተፈጥሮ ሃብት አስተዳደር ቡድኖች ነው። የባዮብሊትዝ ተሳታፊዎች በተወሰነላቸው አካባቢ፣ በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ የተቻላቸውን ያህል ብዝኅ ሕይወት በምዝገባ ያሰፍራሉ።
ለተለያዩ የክህሎት ደረጃ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ስላሉ፤ ሰዎች ሩቅ ርቀት ወይም አጭር ርቀት በእግር መጓዝ የሚሹ ከሆነ መምጣት ይችላሉ። በመሠረቱ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ክህሎቶች አያሻቸውም። አብረዋቸው የሚሠሩት ሳይንቲስቶች እንደምን ምልከታ እንደሚያደርጉና የተመለከቱትን ስለሚለዩበት ሂደት ያመላክቷቸዋል።
ዶ/ር ዴቪድ ኤድሞንድስ
የሚያስፈልገው ሁነኛ ነገር የእርስዎን የምልከታ ኃይል፣ ማለፊያ አስተውሎትና ጮሌ ስልክ ነው። የባዮብሊትዝ ተሳታፊዎች የተመለከቷቸውን ዕፅዋቶችና እንሰሳትን እንደ የመሰሉ የኦንላይን ብዝኅ ሕይወት ዳታቋት ላይ ለልየታ የሚጫኑ ፎቶግራፎችን ያነሳሉ። እንዲሁም፤ መረጃው ሁሉም ሰው በነፃ ወደሚጠቀምበት   ይተላለፋል።

ዶ/ር ኤድሞንድስ ይህንንኑ አስመልክተው ሲናገሩ "ለመለየት የምንሞክረውን ነገር ፎቶግራፍ እናነሳለን፤ ያም ድረገፅ ላይ ይጫናል። ከዚያም በመላው ዓለም ያሉ ሳይንቲስቶች ይመለከቷቸውና ዝርያዎቹን በመለየት የምርምር ደረጃ ዳታ በመሆን ከመላው ዓለም ማንኛውም ሰው መረጃውን ማግኘትና ለየራሳቸው የምርምር ተግባራት ማዋል ይችላሉ" ይላሉ።
Online biodiversity database iNaturalist - Image David Edmonds and iNaturalist.png
Online biodiversity database iNaturalist - Image David Edmonds and iNaturalist

ሳይንሳዊ ዕውቀት እንዲስፋፋ ማገዝ

ሜሊሳ ሆው ዎልፖል አጠገብ የሚኖሩ ኢኮሎጂስት ናቸው። ቀደም ባለው የዎልፖል ሰው አልባ አካባቢ ባዮብሊትዝ፤ በምዕራብ አውስትራሊያ ሙዚየም እንደ ሸረሪቶች፣ ትሎችና ቀንድ አውጣዎችን የመሳሰሉ የጀርባ አጥንት አልባዎችን ያጠኑ ሳይንቲስቶች ከማኅበረሰብ በጎ ፈቃደኞች ጋር አንድ ላይ እንደሠሩ ተናግረዋል።
የጀርባ አጥንት የሌላቸውን ናሙናዎች በባዮብሊትዝ ሂደት ወቅት ከተለያዩ አካባቢዎች የተሳታፊዎች እርዳታ ታክሎበት አሰባስበዋል። ከናሙናዎቹ መካከል አንዱ ጥቂት ቆይቶ በአዲስ ዝርያነት የተለየውና ቀደም ሲል ተመዝግቦ የማያውቀው አንዱ 'ሱዶስኮርፒየን' ነው። ተሳታፊዎቹ በተጨማሪም አዲስ ለአደጋ ተጋልጠው ያሉ ቲንግል ፒግሚ ትራፕዶር ሸረሪት ማስረጃዎችን ፈልገው አግኝተዋል።
ሜሊሳ ሆው
እንዲህ ያለው የባዮብሊትዝ ታይታ ለሳይንስ ኩነቶች ሰፊ ትሩፋት አለው።

"እኒህ ግኝቶች በናሙናዎች ላይ ተጨማሪ ምርምር ለማካሔድና መዘርዝሮቻችው ላይ ሁነኛ መረጃን ለማበርከት ይረዳል። ምናልባትም የተለየ የመኖሪያ መመዘኛዎችና ልዩ ጥበቃን፣ በተለይም እንደ ምንጠራ፣ ልማት ወይም የደን ቃጠሎዎች ካሉ አዋኪ እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ ሕልውናቸው ላይ ስጋትን ሊያሳድር ይችላል" ሲሉ ሆው ያስረዳሉ።

ለዶ/ር ኤድሞንድስ፤ እንደ ዎልፖል ሰው አልባ አካባቢ ባዮብሊትዝ ማደራጀት የአካባቢውን ቅንጭብ የተፈጥሮ ጤና ሁኔታ ሊያመላክት ስለሚችል በጣሙን ጠቃሚ ነው።
Conservation veterinarian Dr David Edmonds in the Walpole wilderness - Image Phil Tucak.jpg
Conservation veterinarian Dr David Edmonds in the Walpole wilderness - Phil Tucak
"የተወሰኑት የዎልፖል ሰው አልባ አካባቢ ባዮብሊትዝ ግቦች ቀደም ሲል ያልተካሔዱ የአካባቢው የዳሰሳ ጥናት ማድረግ፣ አዲስ ሥነ ምሕዳርን መመልከትና ተመሳሳይ፣ የተለዩና ምናልባትም አዲስ የሆኑ ዝርያዎች መኖር አለመኖራቸውን ማጣራት ናቸው። እናም በጣሙን የምንሻው ማንኛውም ሰው መጥቶ ተፈጥሯዊ አካባቢን በማድነቅና ከመልክአ ምድር ጋር እውነተኛ አገራዊ ቁርኝት እንዲኖረው ነው"

"የባዮብሊትዝ ማለፊያ ውጤቶችስ ውስጥ አንዱ የማኅበረሰብ ተሳትፎ፣ ሰዎች መልካም አተያይ ካላቸው ሰዎች ጋር ጎን ለጎን ሆነው መሥራት ነው። አዎን፤ ከሳይንስ በርካታ ነገሮችን ያገኛሉ፤ ነገሮችን ይመለከታሉ፣ እንዲሁም፤ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይገናኛሉ፤ ከሳይንቲስቶችም ይማራሉ" ሲሉ ዶ/ር ኤድሞንድስ ይናገራሉ።

ማንኛውም ሰው በባዮብሊትዝ መሳተፍ ይችላል። አጠገብዎ ያለን ኩነት በኦንላይ ለእርስዎ ማኅበረሰብ፣ የአካባቢ ክብካቤ፣ መልክአ ምድር ወይም ተፈጥሯዊ ሃብት አስተዳደር ቡድን መፈለግ ይችላሉ።

Share