Key Points
- አሉታዊ ኪሳራ ባለሀብቶች ከገቢያቸው ላይ ተቀናሽ እንዲያገኙ ያደርጋል ።
- ጠቀሜታው -የቤት ኪራይ ዋጋ እንዳይጨምር ፤ የባለቤቶቹ የቤት ዋጋ በጊዜ ሂደት እንዲጨምር ያደርጋል።
- ጉዳቱ ፡ - ተጨማሪ የሚከራዩ ቤቶችን መግዛት እንዳይቻል ምክንያት ይሆናል ።
አሉታዊ ኪሳራ የሚከሰተው ባለሀብቶቹ ያከራዩት ቤት ወጪ ከፍ ሲል እና ገቢው በወጪ ሰሸፈን ነው። በተቃራኒው ባለሀብቶች ከቤት ኪራይ የሚያገኙት ገንዘብ ብድርን እና ወለድን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ሸፍኖ ሲገኝ አውንታዊ ጠቀሜታ ይባላል።
ባለሀብቶች መኖሪያ ቤቶችን የሚያከራዩበት ዋነኛው አላማ ትርፍን ለማግኘት ነው። ነገር ግን አሉታዊ ኪሳራ ባለሀብቶችን ተስፋ አስቆራጭ መሆን የለበትም ።
አሉታዊ ኪሳራ እና ዘዴዎቹ
ማክስዌል ሺፍማን የኢንትራፓክ ቤቶች ከፍተኛ ሀላፊ እንደሚያስረዱት አሉታዊ ኪሳራን እንዴት ማመጣጠን እንደሚቻል በቤት ማከራየት ላይ ለተሰማሩ አውስትራሊያውያን ግብር ከፋዮች የሚሆን ዘዴ አለ።
ይህ ዘዴም ለሚከራየው ቤት ያወጡትን ወጪዎች በሙሉ በማቀናነስ እና በማወራረድ ከገቢያቸው ላይ ቅናሽን እንዲያገኙ ይደርጋል።
በአውስትራሊያ የግብር ህግ መሰረት፤ ባለሃብቶች ቤታቸው የተከራየ ወይም ለኪራይ በገበያ ላይ ከዋል ፤ ብድራቸውን በሚከፍሉበት ጊዜ የወለድ ቅናሽን መጠየቅ ይችላሉ።
"እርግጥ ነው ያወጡት አጠቃላይ ወጪ ካስገቡት ገቢ የሚበልጥ ከሆነ ፤ ይህንን ተጨማሪ ወጪ ካስገቡት የኪራይ ገቢ ላይ ወይም ከሌላ ምንጭ ከመጣ ገቢ ላይ ማቀናነስ ይችላሉ። "ማክስዌል ሺፍማን የኢንትራፓክ ቤቶች ከፍተኛ ሀላፊ
አሉታዊ ኪሳራ ጠቀሜታዎቹ እና ጉዳቶቹ
አሉታዊ ኪሳራ እንደማንኛውም ሀብትን የማምጫ ዘዴዎች ሁሉ የራሱ የሆነ ጥቅም እና ጉዳቶች አሉት ።
አንዱ እና ዋነኛ ጠቀሜታው ፤ የቤት አከራዮች ከኪራይ ከሚያገኙት ገቢ ላይ የሚያስወጣቸውን ወጪ በመቀነስ ፤ የሚከፍሉትን ግብር መጠን ይቀንስላቸዋል።
በተጨማሪም የቤት ገዢዎች ከአሉታዊ ኪሳራ የሚገኘውን የግብር ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተጨማሪ የሚከራዩ ቤቶችን እንዲገዙ እንዲበረታቱ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ የቤታቸው ዋጋ ከፍ እንዲል ያደርጋል።
![GettyImages-1144776052 (1).jpg](https://images.sbs.com.au/e1/a1/1fd737c8448cb522ca49ebd1c148/gettyimages-1144776052-1.jpg?imwidth=1280)
Negative gearing encourages investment in property to meet rental demands and prevent housing affordability issues.
ፒተር ኩሊዞስ በአደላይድ ዪኒቨርሲቱ የማስተር ኦፍ ፕሮፐርቲ ፕሮግራም ዳይሬክተር እንደሚሉት ፤ አሉታዊ ኪሳራ የባለሀብቶችን የመበደር አቅም በማዳከም ተጨማሪ ቤቶችን እንዳይገዙ እንቅፋት ሊሆንባቸው ይችላል።
"እንበል እና አሉታዊ ኪሳራው የተከሰተው ትርፍ ሊያስገኝ ከማይችል የሚከራይ ቤት ፤ ለምሳሌ በቅርቡ የተሰራ አዲስ አፓርታም ከሆነ ፤ ባለበት ወቅት ምንም አይነት የዋጋ እድገት አያሳይም።ስለሆነም ኪሳራን ያመጣል። በዚህም ሳቢያ ባለሀብቶቹ የሚከስሩት በየሳምንቱ ከሚያገኙትን የቤት ኪራይ ብቻ ሳይሆን የተጠራቀመ ጥሪት ሀብትንም ጭምር ነው። "Pፒተር ኩሊዞስ በአደላይድ ዪኒቨርሲቱ የማስተር ኦፍ ፕሮፐርቲ ፕሮግራም ዳይሬክተር
![GettyImages-1161056312 (1).jpg](https://images.sbs.com.au/d6/bb/32e2795d45159b6bce937fa0b4f2/gettyimages-1161056312-1.jpg?imwidth=1280)
Negative gearing can reduce rental costs for landlords and attract buyers due to tax benefits.
በገበያው ላይ ያሉ የሚከራዪ ቤቶች የሚፈጥሩት ተጸእኖ
ስቴፈን ማይክንበርገር የገንዘብ አገልግሎት የቡድን መሪ እና የካንስታር ከፍተኛ ተንታኝ አሉታዊ ኪሳራ በገበያው ላይ ያሉ የሚከራዪ ቤቶች ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ተጽእኖ ያስረዳሉ ።
መንግስት ለአሉታዊ ኪሳራ የሚደረገውን ተቀናሽ በማድረጉም ሳቢያ፤ ባለሀብቶች በመኖሪያ ቤቶች ላይ ገንዘባቸውን እንዲያፈሱ በማበረታታት በቂ የሚከራዩ ቤቶች እንዲኖሩ ያደርጋል።
"መንግስት ለአሉታዊ ኪሳራ የሚደረገውን ተቀናሽ በማድረግ ባለሀብቶች በመኖሪያ ቤቶች ላይ ገንዘባቸውን እንዲያፈሱ እና በቂ የበቤት ኪራይን ፍላጎት የሚያሟሉ የሚከራዩ ቤቶች እንዲኖሩ ያበረታታል።"ስቴፈን ማይክንበርገር የገንዘብ አገልግሎት የቡድን መሪ እና የካንስታር ከፍተኛ ተንታኝ
ለአሉታዊ ኪሳራ የሚደረገው ተቀናሽ ከተነሳ ፤ የቤት ኪራይ ዋጋ እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን የቤቶች እጥረትም እንዲከሰት ያደርጋል።
የቤት አከራይ መሆን የረጅም ጊዜ ጠቀሜታው
ፒተር ኩሊዞስ እንደሚሉት ባለሀብቶች ምንም እንኳ ከመነሻው አሉታዊ ኪሳራ ቢኖርባቸውም ወደፊት ንብረቱን በሚሸጡበት ጊዜ ለሚገኘው የተጠራቀመ ትርፍ ከፍተኛ አስተዋጻኦ በማድረግ ይጠቅማቸዋል።
በሚከራዩ ቤቶች ላይ ገንዘብን ማዋል ማለት በረጅም ጊዜ የሚሰበሰብ ሀብትን ማጠራቀም እንደማለት ነው ።ባለሀብቶቹም በመንግስት ጡረታ እና ድጋፍ ላይ ተጠዋሪ የመሆን እጣ ፈንታቸውን ይቀንሳል ሲሉ አቶ ኩንሊዞስ ያክላሉ ።
“ አንድ የሚከራይ ንብረት ቢኖርዎ እና ዋጋውም $ 500,000 ቢሆን ፤ እዳውንም ቀስ በቀስ የጨረሱት ከሆነ ፤ እርስዎ የአረጋውያን ጡረታን ላይከፈልዎ ይችላል።ወይም ደግሞ ግማሹን ብቻ ይከፈልዎት ይሆናል ። ስለሆነም በመንግስት ላይ የመደግፍ እድልዎ በጣም ያነሰ ነው።”
The Australian financial year ends on June 30, and tax returns for the previous financial year must be filed between July 1 and October 31.