በአውስትራሊያ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን የት ማድረግ ይቻላል?

learning CPR.jpg

First aid can help someone feel better, recover more quickly, or even save lives.

አደጋ እና ድንገተኛ ህመም በማንኛውም ስፍራ ሊከሰት ይችላል ። የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን በመውሰድ የድንገተኛ አደጋ ሲከሰት የቆሰሉትን በማከም እና ህይወትን በማዳን ከፍተኛ ሚናን መጫወት ይቻላል።በአውስትራሊያ እንደፍላጎትዎ እና የገንዘብ አቅምዎ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን የሚያደርጉበት ምርጫዎች አለልዎት።


አንኳሮች
  • የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ መማር በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ውጤታማ ምላሽን በመስጠት ቁልፍ የሆነ ሚናን መጫወት ይችላሉ ።
  • የሲ ፒ አር ስልጠና በመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ትምህርት ውስጥ ዋነኛ የሚባል ሲሆን ፤ መመሪያውም የሚመሰረተው በአውስትራሊያ እውቅ ባለሙያዎች ነው ።
  • የስልጠና አማራጮች እንደ እርዝማኔው ፤ አቀራረቡ ፤ የትምህርቱ ይዘት እና የሚሸፍነው የስልጠና አይነት የሚለያይ ነው ።
በአውስትራሊያ ቀይ መስቀል 2017 ባደረገው ጥናት መሰረት , አምስት በመቶ አውስትራሊያውያን ብቻ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን የወሰዱ እንደሆኑ ተረጋግጧል ። ይህ አሀዝ በአለም አቀፍ ደርጃ ካለው ጋር ሲነጻጸር እጅግ በጣም አነስተኛ የሚባል ነው።
በሮያል ህይወት አድን መረጃ መሰረት The 60 በመቶ የሚሆኑት እና በቤት ውስጥ የሚከሰቱ የመቁሰል አደጋዎች ፤ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ የሚያሻቸው ሲሆን፤ ቢያንስ 20 የሚሆኑ አውስትራሊያውያን በልብ ስራውን ማቆም ሳቢያ በየቀኑ ህይወታቸውን ያጣሉ ።
accident during work.jpg
Australian estimates suggest that less than one in three employees feels confident to perform first aid in a workplace emergency.
በክ ሪድ የፓራሜዲክ ባለሙያ በመሆን ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ሲሆን ፤ በተጨማሪም በምእራብ ሲድኒ ሆስፒታል ፓራሜዲሲን አስተማሪ ናቸው ።

እንደእሳቸው አባባልም የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠና ፤ ሰዎች የህይወት አድን ተግባሮችን በቀላሉ እንዲከውኑ የሚያደርግ ሲሆን፤ በተጨማሪም በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ጠንካራ የሆነ የአእምሮ ዝግጀት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

“ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠና የሚያተኩረው እርዳታ ከመድረሱ በፊት ባለው ሂደት ላይ ነው ። በደንብ የተዘጋጁ ሰዎች ከጊዜ ይቀድማሉ ፤የተሻለ ስራንም ይሰራሉ “
በክ ሪድ ፤ ከምእራብ ሲድኒ ሆስፒታል
“ እርግጥ ነው አንድ ሰው በጣም ከታመመ ወይም ከቆሰለ ፤ በዙሪያው ያሉት ሰዎች ፓራሜዲክ እስኪደርስ ድረስ ሰከንድ ሳያባክኑ እርዳታን እንዲያደርጉ እንፈልጋለን ። ”

 ስልጠና ሰጪዎችን መምረጥ

የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠና ልብ ስራውን እንዳያቆም በመጫን መርዳትን CPR, እንዲሁም ለዚህ የተዘጋጀ ማሽንን defibrillator እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያስተምር ነው ።

እነዚህ ሁለቱም በጣም አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎች ሲሆኑ ፤ ልቡ ስራውን ሊያቆም የደረሰን ሰው ህይወት ሊታደጉ የሚችሉ ክህሎቶች ናቸው ።
ambulance.jpg
There were over 26,000 out-of-hospital cardiac arrests in Australia in 2019. It is estimated that 75% of cardiac arrests occur at home or in a private setting.
አቶ ሪድ እንደሚሉት የ CPR ስልጠናዎች የAustralian Resuscitation Council (ARC) መመሪያን መከተል አለባቸው ።
ARC የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠና በተሻለ ሁኔታ እንዴት መሰጠት እንዳለበት ድንጋጌን የሚያወጣ አካል ነው። ካውንስሉ 20 ከሚሆኑ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ ሲሆን ከእነዚህም መካከል College of Emergency Medicine, the Council of Ambulance Authorities and Royal Life Saving ይገኙበታል ።
“ የARC መመሪያዎች የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታን በተመለከተ የተሻለ የሚባለውን አሰራር የሚያቀርብ ሲሆን ፤ ሰልጣኞችም የሚወሥዷቸው ስልጠናዎች በዚሁ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ።”

ዶ/ር ፊናሊ ማክኔል የቀዶ ጥገና ሀኪም እና የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ኮሚቲ ሰብሳቢ ሲሆኑ የአውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ Australian Resuscitation Council የሚወክሉ ናቸው ።
adult learners.jpg
First aid training courses typically incorporate classroom simulations to prepare trainees to deal with emergency situations.
የሴንት ጆን አምቡላንስ ባለሰልጣን , በከፍተኛ ደርጃ የተዋቀረ እና የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን በመስጠት ልምድ ያካበተ ሲሆን በውስጡም የቀይ መስቀል ፤ , ሰርፍ ላይፍ አውስትራሊያ እና ሮያል ላይፍ ሴቪንግ አካቶ ይዟል።

በአንዳንድ ክልሎች እና ግዛቶች ስልጠናዎቹ በአምቡላንስ ባለስልጣናት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማትም ጭምር የሰጣሉ ።

“ በተጨማሪም የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን ለመስጠት የተመዘገቡ ድርጅቶች እና በአገልግሎት ላይ ካሉ ማንኛውም አይነት ድርጅቶች ስልጠናውን መውሰድ ሌላኛው አማራጭ ነው ።” ሲሉ ዶ/ር ማክኔል ያስረዳሉ ።

ትክክለኛውን የስልጠና አይነት መምረጥ

አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናዎች የሚሰጡት በአካል በመገኘት ሲሆን አንዳንዶቹ የስልጠና ክፍሎች በኦንላይን ሊሰጡ ይችላሉ ።
woman working on laptop.jpg
Some training providers offer one or more modules of first aid courses in video or webinar mode.
ዴብ ሎው በብሪዝበ ቀይ መስቀል የክልሉ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናን መሪ በመሆን የሚሰሩ ሲሆን ፤ የተለያዩ አይነት የስልጠና አካሄድ መንግዶችን መከተል የግለሰቦችን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ጥሩ አማራጮች ናቸው ይላሉ።

“ ባለዎት ጊዜ እና ቦታ እንዲሰሩት ይረዳዎታል ፤ በተጨማሪም መረጃዎችን እንዲከልሱ እና እንደገና እንዲያነብቡ እድሉን ይፈጥራል ፤ በተጨማሪም በተለያዪ ቋንቋዎ ተተርጉመው መረጃዎችን በኦንላይን እንዲያገኙ የሚረዱ አሰራሮችም አሉን ።”

ወላጆች እና ተንከባካቢዎች፤ ህጻናት እና ታዳጊዎችን ለመርዳት የሚያግዙ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ይፈልጉ ይሆናል ።

እነዚህ ስልጠናዎች በተለየ ሁኔታ የሚሸፍኗቸውም ፦
  • ለጨቅላ ህጻናት እና ታዳጊዎች የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ - ልብ ስራውን እንዳያቆም በመጫን መርዳት (CPR)
  • የቤት ውስጥ ደህንነትን መጠበቅ ፤ አደጋን መቀነስ ፤
  • ለጤና ችግር ቶሎ ምላሽ መስጠት ፤ የመታፈን ፤ መታነቅ፤ ትንፋሽ ማጣት አስማ አለርጂ እን የደም መፍሰስ የሚሉት ይካተታሉ ።

    እነዚህን ስልጠናዎችን የመውስዱ ዋናው አላማም ፤ ችግር በሚፈጠር ጊዜ አስቸካይ ምላሽን በሙሉ ልብ እንድንሰጥ ማድረግ ነው ። ተጨማሪም እርዳታዎች ካስፈለጉ እንደ ነርስ በስልክ , ያሉትን አገልግሎቶች መጥራት እንድንችል ማስተማር ማሳወቅ ነው ።” በማለት ወ/ረት ሎው ያሥረዳሉ።

በአውስትራሊያ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠና ማስረጃ በየሶስት አመት መታደስ አለበት። እንዲሁም የCPR ማጠናከሪያ ስልጠና በየአመቱ እንዲደረግ ይመከራል ።
ዶ/ር ማክኔል የማጠናከሪው ስልጠና ፤ልብ ስራውን እንዳያቆም በመጫን ህይወትን ማዳን (CPR) እንድንችል ይረዳናል ።

ልብ ስራውን እንዳያቆም በመጫን ህይወትን የማዳን (CPR) ተግባርን ደጋግመው ካልተጠቀሙበት እየደበዘዘ የሚሄድ ነው ።
ዶ/ር ፊናሊ ማክኔል የቀዶ ጥገና ሀኪም እና የአውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ Australian Resuscitation Council የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ኮሚቲ ሰብሳቢ
የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ ስልጠናዎች የጊዜ ርዝመት ሊለያይ ይችላል። አንዳንዶቹ ለተውሰኑ ሰአታት ወይም ጥቂት ቀናት ሊፈጁ ይችላሉ። የተወሰኑት በአገር አቀፍ ደርጃ እውቅና ያላቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹም ላይሆኑ ይችላሉ ።
son father.jpg
It is estimated that only 5% of Australians have a current first aid certificate.
አቶ ሪድ እንደሚያስረዱት ከስልጠናው በኋላ የእውቅና ማስረጃ ማግኘት በጣም አስፈለጊ ነው ፤ በተለይ ስልጠናው ለስራ ቦታ ተገቢ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ።
ነገር ግን የእውቅና ማስረጃ ለማይፈልጉ እና እውቀቱን ብቻ ለመጨበጥ ለሚሹ ሁሉ፤ ለትርፍ ያልተመሰርቱ በርካታ የማህበረሰብ ድርጅቶች እና የአምቡላንስ አገልግሎቶች ኮርሱን በነጻ ይሰጣሉ ።

ያሉትን የተለያዩ አማራጮች መመልከት ተገቢ ነው ሲሉ ይመክራሉ አቶ ሪድ ።

Further resources

  • ለጤና ምክር እና የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ፤ እንዲሁም መረጃዎችን እና ስልጠናን የት መውሰድ እንደሚቻል ለማወቅ
     ይጎብኙ ።
  • የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል ፤ ልብ ስራውን እንዳያቆም በመጫን ህይወትን የማዳን (CPR) መመሪያ የነጻ አፕ አለው።
  • የሴንት ጆን አምቡላንስ የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታን በተመለከተ ሊጫኑ የሚችሉ በርካታ መመሪያዎችን በአረብኛ ፤ቻይንኛ ፤ ግሪክ፤ ጣልያንኛ እና በቬትናም ቋንቋዎች አዘጋጅቷል ።
  • ህጻናትን የማሳደግ ህብረት Raising Children Network የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ መረጃዎችን ለጨቅላ ህጻናት , ታዳጊዎች , ሙአለ ህጻናት እና ትምህርት ቤት ላሉ ያዘጋጀውን መመሪያ ይመልከቱ ።

    ለድንገተኛ ጊዜ ሶስት ዜሮዎችን በመደወል የአምቡላንስ አገልግሎትን ይጠይቁ ። በስልኩ መስመር ላይ የሚያገኙትም ሰው የመጀመሪያ ጊዜ እርዳታ በማቅረብ ይረዳዎታል ።

Share