Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 2

Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 2

Fikrou Kidane Source: Courtesy of FK

ፍቅሩ ኪዳኔ፤ በክፍል ሁለት የስፖርቱ መስክ ግለ-ሕይወት ትረካቸው፤ ከኮንጎ ዘመቻ ተሳትፎአቸው ተነስተው የቀድሞው የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ኹዋን አንቶኒዮ ሳማራንች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ዘመናቸው ድረስ ያወጋሉ።


ፍቅሩ፤ በጋዜጠኛነት ዘመናቸው አዲስ አበባ ተቀምጠው በጋዜጦች ላይ በመጻፍና በሬዲዮ በመናገር ብቻ አልተወሰኑም። ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በኮንጎ ዘመቻ ተሳትፈዋል። ለአስተዋጽኦዋቸውም የመቶ አለቃነት ማዕረግ አግኝተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አገልግሎት ሜዳልና የአገራቸውንም ከፍተኛ ኒሻን ተሸልመዋል። ሲልም፤ የመንግሥታቱ ድርጅት ተቀጣሪ ሆነው ዳግም ከኒው ዮርክ ኮንጎ ዘልቀዋል።
Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 2
Col. (later Lt. General) Teshome Ergetu (C), and Fikrou Kidane (R) Source: Courtesy of FK
ቆይተውም ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመለሱ። ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ተገናኝተው እንደገና የኢትዮጵያን ስፖርት ፈር ለማስያዝ አብረው መሥራት ጀመሩ። ግልጋሎታቸውንም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ፣ የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊና የሸዋ እግር ኳስ ሊግ ዋና ጸሐፊ በመሆን አበረከቱ። 

በዚያም ሳይወሰኑ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበርን ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ሆነው መሠረቱ።

 

ይሁንና የኢትዮጵያ የመጨረሻው የዘውድ ሥርዓት ሲያከትም ዕጣ ፈንታቸው ስደት ሆነ። እስካሁንም የሚኖሩባት አገረ ፈረንሳይ ማለፊያ መስተንግዶዋን ቸረቻቸው። የግል የስፖርት ጋዜጣ አቋቋሙባት።

“እልፍ ሲሉ ዕልፍ ይገኛል” እንዲባል፤ የፍቅሩ የስደት የማታ እንጀራ ሰፍቶ እ.አ.አ. ከ1980-2001 የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት የነበሩት ኹዋን አንቶኒዮ ሳማራንች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬተክር ለመሆን በቁ።
Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 2
Juan Antonio Samaranch (L), and Fikrou Kidane (R) Source: Courtesy of FK
ምንም እንኳ ከ42 ዓመታት የስደት ሕይወት በኋላ የወርቃማ ዕድሜ (የጡረታ) እፎይታ ዘመን ላይ የደርሱም ቢሆን፤ ለአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር በበርካታ አሠርት ዓመታት የተከማቹ የሙያ ተሞክሮአቸውን እንሆኝ በማለት እገዛና ድጋፋቸውን እየቸሩ ይገኛሉ።  


Share