"የአገሮቻችንን ባሕላዊ ዕሴቶች ማስተዋወቅ በመቻላችን ደስተኞች ነን" አፍሪካውያን አውስትራሊያውያን
![2022 Afri Festival.jpg](https://images.sbs.com.au/dims4/default/a92afdc/2147483647/strip/true/crop/1280x720+0+0/resize/1280x720!/quality/90/?url=http%3A%2F%2Fsbs-au-brightspot.s3.amazonaws.com%2Fbc%2F41%2F38a798664f48aa25e6a70ecfb093%2F2022-afri-festival.jpg&imwidth=1280)
2022 African Music and Cultural Festival (AMCF) at Federation Square on 20 November 2022 in Melbourne, Australia.
ከ35 በላይ አገራት በፌዴሬሽን አደባባይ ሜልበርን ከተማ ውስጥ ከዓርብ ሕዳር 9 አንስቶ ለሶስት ቀናት የተካሔደው የአፍሪካ ሙዚቃና ባሕል ፌስቲቫል እሑድ ሕዳር 11 ተጠናቅቋል። በዝግጅቱ ላይ የተሳተፉት አፍሪካውያን - አውስትራሊያውያን በአንድ በኩል ደስተኝነታቸውን ሲገልጡ፤ በሌላም በኩል በአፍሪካውያን ዝግጅት ላይ አፍሪካውያን በዝተው አለመታደማቸው ግር ያሰኛቸው መሆኑን ገልጠዋል።
Share