አንኳሮች
- በማንኛውም ትልቅ ጥቁር ሸረሪት መነከስ በአስቸኳይ የሕክምና ጉዳይነት ሊታይ ይገባል
- በማናቸውም ዓይነት እባብ መነከስ ለሕይወት አደገኛነቱ ታስቦ እንደ መጀመሪያ የሕክምና እርዳታ እንቅስቃሴን በሚገታ መልኩ ጥብቅ ብሎ ሊታሰር ይገባል
- አውስትራሊያ ውስጥ በርቀት ያሉ አካባቢዎችን አካትቶ በሁሉም ሥፍራ የድንገተኛ ሕክምና እርዳታን ማግኘት ይችላሉ
አውስትራሊያ መርዛማ እንሰሳትን አስመልክቶ አስፈሪ ስም አላት። ይሁንና ሸረሪቶችን በተመለከተ ሊያስጨንቀን የሚገባ አንድ የነፍሳት ዝርያ እንዳለ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የመርዞች መረጃ ማዕከል የሕክምና ዳይሬክተር ዳረን ሮበርትስ ያመላክታሉ።
“ያም ባለ ማንቆርቆሪያ ድር ሸረሪት ነው። እንዲሁም ስለ ባለ ቀይ ጀርባ ሸረሪት መርዛማነት ይነገራል። ለሕመም ሊዳርጉዎት ይችላሉ። ሆኖም የመሞት ወይም በብርቱ የመመረዝ አዝማሚያዎችን አስከትሎ ለሆስፒታል የመዳረጋቸው ሁነት ዝቅተኛ ነው። የተቀሩት ሸረሪቶች በሙሉ በጥቅሉ ዝቅተኛ ወይም መርዛማ ባለመሆን ይፈረጃሉ።"
![redback.jpg](https://images.sbs.com.au/cb/ce/eee0b5d546c281f59d43cebee3d6/redback.jpg?imwidth=1280)
Research has disproved previous concerns about redback spider bites. Although they contain venom, effects take hours to develop and do not require medical treatment, unless there are signs of infection or aggravated symptoms. Credit: Getty Images/Jenny Dettrick
ከአገሪቱ 172 የእባብ ዝርያዎች ውስጥ 100 ያህሉ መርዛማ ናቸው፤ የ እንደሚያሳዩት በዓመት አማካይ ሕልፈተ ሕይወቶች ሁለት ናቸው።
ዶ/ር ሮበርትስ “እኛ የምንኖርበትን ጨምሮ በመላው አውስትራሊያ እባቦች ይገኛሉ፤ ልንገጣጠምም እንችላለን። ሆኖም፤ በእባብ መነደፍ የሚገጥሙ ችግሮች በአንፃራዊነት እምብዛም ናቸው" ብለዋል።
![tiger snake.jpg](https://images.sbs.com.au/9a/d8/9a82eaa2452ca63edfcac9721141/tiger-snake.jpg?imwidth=1280)
“Snakes have very little reason to go into people's houses.” Professional snake catcher Gianni Hodgson says 90% of the calls he gets are for snake removals from a backyard. Credit: Getty Images/Andrew Balcombe / EyeEm
ለሸረሪት ነደፋዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና
አውስትራሊያ ውስጥ አብዛኛዎቹ የሸረሪቶች ነደፋዎች አነሰተኛ ጉዳት የሚያደርሱም ቢሆን፤ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው ለመነደፍ ቢዳረግ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ማወቁ ጠቃሚ ነው።
ዶ/ር ሮበርትስ ከማንቆርቆሪያ ድር ሸረሪት በስተቀር ለሌላ ሸረሪት ነደፋ ምክራቸውን ሲለግሱ “ዝም ብሎ የማየትና መጠበቅ ጉዳይ እንዳይሆን፤ የተነደፉበትን ዙሪያ በቁስል ማድረቂያ ያፅዱት፣ ጎጂ ሕዋሳት መከላታቸውን ደጋግመው ያረጋግጡ” በማለት ያሳስባሉ።
ለሕመም ምልክቶች ወይም የምረዛ ምልክቶች የሕክምና እርዳታ ይጠይቁ።
የተነደፉበት አካል ላይ ሕመም መሰማት የተለመደ ነው። በንፁህ ጨርቅ የተጠቀለለ የበረዶ አንኳሮችን በቀጥታ የተነደፈው አካል ላይ ተጭነው ለ15 ደቂቃዎች ያህል መያዝ ሕመምዎን ለማስታገስ ያግዝዎታል።
![red mark.jpg](https://images.sbs.com.au/d6/58/b5fdfb444c8484a94ce4ebd493c1/red-mark.jpg?imwidth=1280)
Spider bites (other than the funnel-web) can be so delicate that people don’t feel it until later, Dr Roberts says. Credit: Getty Images/Stefania Pelfini, La Waziya Photography
ማንኛውንም የትልቅ ጥቁር ሸረሪት ወይም የማንቆርቆሪያ ድር ሸረሪት ንክሻን ለአስቸኳይ የሕክምና አስፈላጊነት በማሰብ የአምቡላንስ ጥሪ ያድርጉ።
የማንቆርቆሪያ ድር ሸረሪት በአፍ አካባቢ የመደንዘዝ ስሜትን፣ ማቅለሽለሽና ትውከት፣ የሆድ ወይም የደረት ሕመምን ያስከትላል።ዶ/ር ሾን ፍራንሲስ፤ በኩዊንስላንድ የሮያል በራሪ ሐኪም እልግሎት
![funnel-web.jpg](https://images.sbs.com.au/30/db/3e64e46e4663a62915cbb63108a7/funnel-web.jpg?imwidth=1280)
Funnel-web spiders are found around Sydney and the east coast. Other big black spiders are found Australia-wide. Credit: Getty Images/Image Created by James van den Broek
- “በተነከሰው አካል አካባቢ በማሰሪያ ፋሻ አጥብቀው ይሠሩ፤ ከላይና ከታች ጭምር።
- አምቡላንስ እስከሚመጣ ድረስ የተነደፈው ግለሰቡ ተንጋልሎ መጠበቅ ይኖርበታል።
- መርዙ በሰውነት ውስጥ በፍጥነት ከመሰራጨት እንዲገታ፤ የተነደፉ ግለሰቦችን እንዳይራመዱ ያሳስቧቸው።
አምቡላንስ እስኪመጣ ድረስም የተነደፈው አካል አካባቢ ከእንቅስቃሴ እንዲገታ ይጣሩ።
![pressure immob bandage.jpg](https://images.sbs.com.au/c0/07/220c050f4bdabad16e472ea83855/pressure-immob-bandage.jpg?imwidth=1280)
A pressure immobilisation bandage, not a tourniquet, is used for funnel-web spider bites as well as venomous snakebites to stop the venom circulation in the body. Credit: Getty Images/Lisa Maree Williams / Stringer
ነደፋው የተፈፀመው ሩቅ ሥፍራ ከሆነስ?
ሾን ፍራንሲስ አውስትራሊያ ውስጥ በገጠርና የሩቅ ሥፍራ ማኅበረሰባት የአየር ሕክምና ትራንስፖርት፣ የጤና ክብካቤና የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጠው ትርፋማ ያልሆነው የኩዊንስላንድ ሮያል በራሪ ሐኪም ቅርንጫፍ አገልግሎት ሐኪም ናቸው።
ዶ/ር ፍራንሲስ፤ ርቀው ባሉ ሥፍራዎች የሸረሪት ንክሻ የተለመደ ሲሆን በአብዛኛው የትኛው ዓይነት ሸረሪት ንክሻ አንደሆነ እንደማይታወቅ ይናገራሉ።
መጀመሪያ ላይ፤ ንክሻው የደረሰበት አካል አካባቢ የህመም ስሜት ይኖራል፤ በትክክል የየትኛው ሸረሪት ንክሻ እንደሆነ በማይታወቅበት ሁኔታም የተወሰነ ቅላትና ዕብጠት ይኖራል።ሾን ፍራንሲስ፤ በኩዊንስላንድ የሮያል በራሪ ሐኪም አገልግሎት
የሥርዓታዊ ምልክቶቹ መከሰት የንክሻ ምረዛ አመላካች ናቸው። የአየር ሕክምና ትራንስፖርት የጤና ክብካቤ ጣልቃ ገብነትን ግድ እንደሚሉ ያስረዳሉ።
“ከሕመም ስሜት በላይ ከሆነ ከማላብ ይጀምራል ያኔ በጣሙን መስጋት እንጀምራለን። ለምሳሌ ያህል፤ የማንቆርቆሪያ ድር ሽረሪት ከሆነ በአፍ አካባቢ መደንዘዝን፣ ምናልባትም ማቅለሽለሽና ትውከትን፣ የሆድ ወይም የደረት ሕመምን ያስከትላል።
“ያም እኛን ጣልቃ ለመግባትና ተጨማሪ ክብካቤ ለማድረግ ያነሳሳናል። ከእባብ ነደፋ ጋር ሲነፃፀርም እኒህ ምልክቶች ባይኖሩም እንኳ ሕመምተኛውን ወደ ቀጣይ ክብካቤ እናሸጋግረዋለን” በማለት ዶ/ር ፍራንሲስ አበክረው ተናግረዋል።
![outback.jpg](https://images.sbs.com.au/83/18/327540d145e19ffbd7c7fee2cba4/outback.jpg?imwidth=1280)
In the outback, all emergency calls for snakebites trigger a medical response for suspected envenomation. Credit: Getty Images/kristianbell
ለእባብ ንክሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና
የተወሰኑ የእባብ ንክሻዎች ደረቅ ናቸው። ያም ማለት እባቡ ይናደፋል ሆኖም መርዙን አይረጭም።
ሆኖም የእባብ ንክሻ መርዛማ አይደለም ብሎ ማሰብ አደገኛ እንደሆነ፤ ሁሉም ዓይነት የተረጋገጡም ሆነ የተጠረጠሩ የእባብ ንክሻዎች ሕይወትን ሊቀጥፉ እንድሚችሉ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባም ያሳስባሉ።
ዶ/ር ፍራንሲስ ሶስት አስፈላጊ ደረጃዎችን ያመላክታሉ፤
- በፋሻ ይሰሩ
- ቢቻል የተነከሰውን አካል ለይቶ እንዳይንቀሳቀስ ያድርጉ
- 000 ይደውሉ
እንደ ፕሮፌሽናል እባብ አድኖ ያዢ ጂያኒ ሆድጅሰን አባባል መርዛማ ያልሆነ እባብ ንክሻ እንኳ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል።
“የቤት እንሰሳት ሊያገኟቸው፤ ሕፃናትም ሊነደፉ ይችላሉ። መርዛማ ባይሆኑ እንኳ ባክቴሪያ ሊኖራቸው ይችላል። ”
እባብ ሲገጥምዎት ሊያደርጉ የማይገባዎት
እባቦች ስጋት ወይም ፍርሃት ካላደረባቸው በስተቀር አይናደፉም። በርካታ ነደፋዎች የተከሰቱት ሰዎች ሊገድሏቸው ወይም ሊይዟቸው ሲሞክሩ ነው።
አቶ ሆጅሰን እባብ ሊያሳድዳችሁ ይችላል የሚለው አባባል የተለመደ የተሳሳተ ዕሳቤ እንደሆነ ያመላክታሉ።
እባብ ወደ እርስዎ የሚመጣበት ወቅት ቢኖር ወደ ደህና ሥፍራ ለማምራት ሲሞክርና እርስዎ መንገዱ ላይ ተደቅንው ሲገኙ ነው። ግማሽ ያህሉን እርስዎ እዚያ መቆምዎን እንኳ ልብ አይሉም።ጂያኒ ሆጅሰን፤ ሮፌሽናል እባብ አድኖ ያዥ
እባብ ሲገጥምዎት ምን ማድረግ እንዳለብዎ የተወስኑ ፍንጮችን እነሆኝ ይላሉ።
- “የጎላ ድምፅ አያሰሙ፤ ስለምን ቀርበውት ያሉ ከሆነ ወደ ተከላካይነት እንዲያመራ ያደርገዋልና።
- እየተንቀሳቀሱ እንደሆነና እየራቁ መሆንዎን ያሳውቁ።
- በአጋጣሚ እባቡ ላይ ቆመውበት ከሆነ ቀጥ ብለው ከእንቅስቃሴዎ ይገቱ። እንዲሄድ ያድርጉት። ወደ ሚሔድበት መሔዱን ይቀጥላል። እርስዎ እዚያ ያሉ መሆኑን ገና ልብ አላለምና።”
ከተነደፉ ማን ዘንድ እንደሚደውሉ
- በሸረሪት ተነድፈው ሳለ ምን ማድረግ እንዳለብዎት እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ወደ ብሔራዊ የመርዞች መረጃ ማዕከል በ 13 11 26 ይደውሉ።
- ለሁሉም የእባብ መነደፎችና ለማንኛውም ዓይነት አስቸኳይ ሁነት 000 ይደውሉ።
- ከሆስፒታል ርቀው ያሉ ከሆነ፤ የሮያል በረራ ሐኪም አገልግሎት ዘንድ በ 1300 My RFDS (1300 69 7337) ይደውሉ።