የመኖሪያ ሥፍራዎን አረንጓዴያማ የማድረግ ጠቀሜታ

Bonding In The Garden

Father and son bonding in their garden and tending to their vegetable patch together. Credit: SolStock/Getty Images

አውስትራሊያውያን ለአረንጓዴያማ ሥፍራዎች ትልቅ ዋጋን ይሰጣሉ። ለግለሰብ፣ ማኅበረሰብና የተፈጥሮ ክብካቤ የዕፅዋት ሕይወት ያላቸው ትሩፋቶች አያሌ ነው። ለዚህም ነው በጓሮ እርሻዎቻችንና ጎዳናዎች ላይ ምን ማድረግና ማድረግ እንደሌለብን ልብ ለማሰኘት ድንጋጌዎች ለመደንገግ የበቁት።


አንኳሮች
  • ዕፅዋት ወደ ትውልድ አገርዎና የልጅነት ሕይወትዎ በምልሰት ያጓጓዝዎታል
  • ማዘጋጃ ቤቶች የእኛን ብርቅ የከተማ መከለያ ዛፍ ጠብቆ የማቆየት ደንቦች አላቸው
  • ቤት ተከራዮች በጓሮ እርሻ ላይ ሁነኛ ለውጥ ከማድረጋቸው በፊት ሁሌም ከቤት አከራይ ሥራ አስኪያጃቸው ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል
በቤትዎ ዙሪያ የጓሮ ዕፅዋትንና ቅጠላ ቅጠሎችን የመትከል ትሩፋቶችን ማበረታት አሌ የማይባል ነው።

“በሰዎችና በውጪው ዓለም ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ አያሌ የተካሔዱ ጥናቶች አሉ" ሲሉ የዕፅዋት ተጠባቢው ጀስቲን ካልቬርሊ ይናገራሉ።

አያይዘውም “በግንብ በተገነቡ ከተሞች እንዲያ ካለው አኗኗር ዘዬ ለመራቅ ብንዳዳም፤ ሁሌም በተፈጥሯዊው ዓለም በዕፅዋት ስንከበብ በጣሙን መልካም ስሜት እንደሚያድርብን ግና እናውቃለን" ብለዋል።
Apartment block in Sydney NSW Australia with hanging gardens and plants on exterior of the building at Sunset with lovely colourful clouds in the sky
Apartment block in Sydney, Australia with hanging gardens and plants on exterior of the building at Sunset. Source: iStockphoto / Elias/Getty Images/iStockphoto
የተክል ትሩፋቶች ጥላና ቅዝቃዜን ያካትትታሉ። እንዲሁም፤ ከበቀሉ ቅጠላ ቅጠሎች የተጣራ አየርም ይገኝበታል።

አቶ ካልቬርሊ ለአውስትራሊያ አዲስ ለሆኑ ሰዎች ተመሳሳይ የሆኑ ተክሎችን መመልከቱ "ወደ አገር ቤት በምልሰት ያጓጉዝዎታል፤ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል የሚል መንፈስ ማረጋጊያ ስሜትን ያሳድራል" ብለዋል።

ገንብተን ባለንባቸው አካባቢዎች ያሉ በርካታ ገፅታዎችና ድምፆች ሲመልከቷቸው፣ ሲዳስሷቸው፣ ሲልም ተክሎቹን ሲመገቧቸው እርስዎ ባደጉበት አካባቢ ያልተለመዱ ይሆናሉ። በተለይም፤ ሽታና ጣዕማቸው ወደ ትውልድ አገርዎ የልጅነት ጊዜ ሊያመራዎ ይችላል። ተክሎችና የጓሮ አትክልቶች እንዲህ ያለውን ይቸርዎታል።
ጀስቲን ካልቬርሊ፤ የሰዎችና ተፈጥሮ ግንኙነት ባለሙያ
McElhone Place Surry Hills, Sydney
McElhone Place Surry Hills, Sydney Credit: Richard Gurney
ምርታማ የጓሮ ተክል መትከል የንጥረ ምግብና እንቅስቅሴ ትሩፋቶችን ያስገኛል።

“ቫይታሚን ዲ ከፀሐይ" እንዲሁም "ከመሬት ጋር እየሠራን ቀላል አካላዊ እንቅስቃሴን እናገኛለን" ሲሉ አቶ ካልቬርሊ ይገልጣሉ።

የከተማ የዛፍ ከለላ ምንድነው?

በአብዛኛዎቹ የከተሞች አካባቢ ግንባታ የለሽ ሥፍራዎች ውስን ስለሆኑ፤ ዛፎች ለእንሰሳትና ለማኅበረሰባችን ወሳኝ እንደሆኑ በሜልበርን የፖርት ፊሊፕ ከተማ ከንቲባ ማርከስ ፐርል ልብ ያሰኛሉ።

የአውስትራሊያ ዛፎች በዛፎች ድንጋጌ አንቀፅና በአካባቢ ማዘጋጃ ቤት የዛፍ ጥበቃ ደንቦች ሕጋዊ ጥበቃ አላቸው።

Melbourne tree canopy_Mark Burban_Getty.jpg
Melbourne tree canopy Credit: Mark Burban / Getty Images
በመሆኑም፤ የከተማ ነዋሪዎች ከግል የጓሮ እርሻቸው እንኳ ቢሆን በርከት ያሉ ዛፎችን ለመክላት ከመነሳታቸው በፊት የማዘጋጃ ቤት ፈቃድን ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

ከንቲባ ፐርል ይህንኑ ሲያስረዱ "በበርካታ ሥፍራ ያሉ የከተማ ክፍለ ከተማዎች በርከት ያሉ ዛፎች እንዳይከሉ እገዳ አለባቸው። ስለምን፤ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች 'የከተማ ከለላ' ብለው የሚጠራቸውን ጥላና ዛፎች ጠብቀው ማቆየት ይሻሉና።

ማዘጋጃ ቤቶች በተለያዩ ቋንቋዎች በእርስዎ የመኖሪያ ንብረት አካባቢ ያሉ ዛፎችን አስመልክቶ ምን ማድረግ እንዳለብዎትና ምን ማድረግ እንደሌለብዎት የሚያስረዱ መምሪያዎች አሏቸው።

Darlinghurst Sydney_Nina Rose_Getty.jpg
Darlinghurst, Sydney Credit: Nina Rose / EyeEm / Getty Images

የተፈጥሮ ንጣፍ ተነሳሽነቶች

ለምሳሌ ያህል፤ የአካባቢው ነዋሪዎች መኖሪያቸውን እንዲያሻሻሉ ፖርት ፊሊፕ የተወሰነ ግንባታ አልባ ሥፍራ አለው።

የማኅበረሰብ ምክረ ሃሳብን ተከትሎ የማዘጋጃ የተፈጥሮ ንጣፍ አካባቢ ወይም የሳጥን ተክሎችን በቤቶቻቸው ዙሪያ እንዲተክሉ እገዳዎች እንዲነሱ መደረጉን ከንቲባ ፐርል ገልጠዋል።
በኮቪድ ወቅት የሆነው በእጅጉ አስገራሚ ነው። አያሌ ሰዎች በቤቶቻቸው ወይም አፓርትመንቶቻቸው ዙሪያ ያሉ የአካባቢያቸውን አጎራባች የተፈጥሮ ንጣፍ ሲከባከቡ ነበር።
ማርከስ ፐርል፤ በሜልበርን የፖርት ፊሊፕ ከተማ ከንቲባ
“እንዲህ ያለውን እንቅስቃሴ በፖርት ፊልፕ ከተማ እያስተዋወቅን ነበር። ስለምን፤ ለሁሉም ሰው ማራኪ ባሕላዊና ሕብረተሰባዊ ትሩፋት አለውና" ብለዋል።

ተከራዮች ምን ማድረግ ይችላሉ?

ተከራዮች ሣሮችን ማጨድና ቅርንጫፎችን መከርከምን አካትቶ፤ የጓሮ እርሻቸውን መከባከብ ይጠበቅባቸዋል።

አንድ ተከራይ ማሻሻል ቢፈልግ በእጅጉ ተቀባይነት ያለው መሆኑን በሲድኒ የንብረት ሥር አስኪያጅ ኢጊ ዳሚያኒ ይናገራሉ።

ይሁንና፤ ተለቅ ያሉ ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ወይም ለምሳሌ ያህል ዕይታዎችን ሊከልሉ የሚችሉ ዛፎችን መትከል ካሹ ግና ፈቃድ ለመጠየቅ ግድ እንደሚሰኙ ዳሚያኑ ሲያስገነዝቡ፤

“አንድ ተከራይ የጓሮ እርሻ ለውጦችን ማድረግ ሲሻ በለውጦቹ አከራዩ ደስተኛ መሆኑን ለማረጋግጥ ሁሌም የንብረት ሥራ አስኪያጅን ማነጋገር እንዳለበት ልብ ሊል ይገባል” ብለዋል።
Potted gardens_Adene Sanchez_Getty.jpg
"For migrants in Australia, there’s just something about seeing a familiar plant out of context", says horticulturalist Justin Calverley Credit: Adene Sanchez / Getty Images
የሸክላ ማሰሮ የጓሮ ተክል ለተከራዮች ትልቅ አማራጭን ይሰጣል።

አቶ ካልቬርሊ “አብረዎት ይዘዋቸው ሊሄዱ ይችላሉ። ወደ ፀሐይ ወይም ጥላ ሊያዘዋውሯቸው ይችላሉ። ድንቅ ነው" ብለዋል። በማከልም “ይሁንና በትንሹ ይጀምሩ። የሸክላ ማሰሮ የጓሮ አትክልት ትክክለኛ ተክልና ትክክለኛ የሸክላ ማሰሮን ይሻል። ስለሆነም፤ ትክክለኛ የሸክላ ማሰሮና ተገቢ ዝንቅ ተክሎች ያለዎት ስለመሆኑ አነስተኛ ምርምር ያድርጉ" ሲሉ ምክረ ሃሳባቸውን ቸረዋል።

አያይዘውም፤ የአውስትራሊያን አገር በቀል ተክሎች ከእሳቤ ማስገባቱ ጠቀሜታ እንዳለውና በተለይም፤ ለተለየ አካባቢ ተስማሚ የሆኑ አገር በቀል ተክሎች ይበልጡን ተመራጭ እንደሚሆን ሲያመላክቱ፤

“ከተቻለ የጓሮ ተክል ተከላ ሲጀምሩ፤ አገር በቀል ተክሎች ከአየር ንብረቱና አፈሩ ጋር የተዋደዱ በመሆናቸው እነሱን መትከሉ ከፍ ያለ ስኬትን ይቸርዎታል" ብለዋል።

Share