ኮሮናቫይረስ በሕክምና ባለሙያዎች ላይ እያሳደረ ያለው ተፅዕኖ በኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን ነርሶች አንደበት

Ethiopian - Australian Nurses #COVID - 19

Ayantu Bayu (T-U), Lula kibreab (L), Hiwot Barega (C), and Markos Bogale (R) Source: Supplied

የኮሮናቫይረስ ዓለምን በሲቃ ሰቅዞ በያዘበት በአሁኑ ወቅት የግንባር ተፋላሚ ረድፍ ላይ የሚገኙት የሕክምና ባለሙያዎች ናቸው። እንደ ባለሙያ በሥራ መስክ፤ እንደ ቤተሰብና ማኅበረሰብ አካልነታቸውም በማኅበራዊ ሕይወታቸው ከሌሎች ለየት ብለው ይፈተናሉ። ነርስ አያንቱ ባዩ (ከሜልበርን)፣ ነርስ ማርቆስ ቦጋለ (ከሲድኒ)፣ ነርስ ሕይወት ባረጋ (ከፐርዝ) እና ነርስ ሉላ ክብረአብ (ከሜልበርን) በኮሮናቫይረስ ፍልሚያ ውስጥ የነርስ የሙያ ግዴታቸው ስላሳደረባቸው ስጋትና የሙያ ሚና ይናገራሉ። በSBS አማርኛ ዝግጅት ክፍል ስም በመላው አውስትራሊያ ላሉ የሕክምና ባለሙያዎች፤ በተለይም በዚህ ፈታኝ ወቅት ለሙያ አስተዋፅዖዋቸው ራሳቸውን ለሰጡቱ ኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የሕክምና መስክ ሠራተኞች በሙሉ ምሥጋናና ከበሬታችንን እንገልጻለን። ሥራቸው ሞገስ እንዲሆንላቸውም እንመኛለን።



Share