"በዕለተ ዕንቁጣጣሽ፤ ለሁላችሁም የደስታ፣ የሰላምና የተስፋ አዲስ ዓመት እመኝላችኋለሁ" የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ

gettyimages-1555609590-612x612.jpg

Anthony Albanese, Prime Minister of Australia. Credit: Bloomberg/Bloomberg via Getty Images

"ይህ ወቅት ለታሪክና ቅርሳችሁ ክብር መቸሪያና ታሪካችሁን የመንገሪያ ጊዜ ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ


ዕንቁጣጣሽን ለምታከብሩ ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ይህ ወቅት ለታሪክና ቅርሳችሁ ክብር መቸሪያና ታሪካችሁን የመንገሪያ ጊዜ ነው።

በእዚህ ዓመት መጀመሪያ ፐርዝ ላይ በማግኘቴ ደስታ የተሰማኝ የኢትዮጵያ ተወላጁ ኮሜዲያን ጆ ዋይት፤ ጥበብና ብልሃት በተመላበት ሁኔታ ስለ ቤተሰቡ ፍልሰትና የአውስትራሊያ ሠፈራ ሲናገር፤

ይህች አገር፣

"ለእኔና ለመላ የቤተሰቤ አባላት ተስፋና ማለፊያ ሕይወይትን ቸራናለች" ሲል ነበር የገለጠው።

አውስትራሊያ ማናቸውም ሰዎች ታሪካቸውን እንዲተርኩ፣ ማንነታቸውን እንዲያከብሩና ሕልሞቻቸውን እንዲያጋሩ ዕድል ትሰጣለች።

የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ለዘመናዊት አውስትራሊያ ብዝኅዊ ሽብርቆሽ የበለፀገና ያማረ አስተዋፅዖዎችን አበርክቷል።

በዕለተ ዕንቁጣጣሽ፤ ለሁላችሁም የደስታ፣ የሰላምና የተስፋ አዲስ ዓመት እመኝላችኋለሁ።

መልካም አዲስ ዓመት

የተከበሩ አንቶኒ አልባኒዚ፤ የምክር ቤት አባል

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር

መስከረም 1 ቀን 2016


Share