ክፍተትን ማጥበብ ማለት ምን ማለት ነው ?

Indigenous Australian family.jpg

አውስትራሊያ ረጅም እድሜን የሚኖሩ ሰዎች አሉባት ከሚባሉ አገራት መካከል አንደኛዋ ናት ።በአማካኝ አንድ አውስትራሊያዊ የ83ተኛ የልደት በአሉን ያከብራል። ነገር ግን የአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች ከተቀረው አውስትራሊያውያን የእድሜ ጣራ ጋር ሲነጻጸሩ የእድሜያቸው ጣሪያ በስምንት አመት አመት ያንሳል። ይህንንም ለመቀየር ክፍተትን ማጥበብ የሚለው ሀሳብ በብሄራዊ ደርጃ የተቀረጸ ነው። የቀደምት ነዋሪዎችን ጤና እና ደህንነት በማሻሻል ፤ ሌሎች ነባር ያልሆኑ አውስትራሊያውያን የሚኖሩቱን ጥራት ያለው ህይወት እና እድሎችን እንዲያጣጥሙ ማድረግ ይቻላል።


አንኳሮች
  • • ክፍተትን ማጥበብ የተጀመረው በ2008አም አላማውም የቀደምት ነዋሪዎችን ጤና እና ደህንነት በማሻሻል ፤ ሌሎች ነባር ያልሆኑ አውስትራሊያውያን የሚኖሩቱን ጥራት ያለው ህይወት እና እድሎችን እንዲያጣጥሙ ማድረግ ነው።
  • • በ2020አም አስራሩ ማሻሻያ የተደረገበት ሲሆን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ከአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች ጋር በጋራ ማደረግ ተችሏል፤
  • • አምስት በሚሆኑት የማሻሻያ እርምጃዎች ላይ የተገኙት ውጤቶች በመስመር ላይ ያሉ ሲሆኑ ፤ በእስር ቤት ባሉ ዜጎች ቁጥር እና የራስን ህይወት በማጥፋት ዙሪያ ግን ከመሻሻል ይልቅ ተባብሷል፤
  • • በአላማ ከተያዙት 19 ግቦች መካከል 5ቱ ብቻ በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ይገኛሉ።

በቀደምት ጊዜያት የነበረው የእኩልነት ጥሪ


በ2007 አም መጀመሪያ የአቦርጅናል እድሜ ባለ ጸጋ የሆኑት ፕሮፌሰር ቶም ካልማ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠውንና በማህበረሰባዊ ፍትህ ዙሪያ ያጠነጠነውን ሪፖርት አቀርቡ ። በውስጡም ለአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች የጤና እኩልነት እንዲረጋገጥ ጥሪ አቀረቡ።

ሪፖርታቸው በበርካታ ሰዎች ዘንድም ተቀባይነትን አተረፈ። በ 2007አም እዉቋ የኦሎምፒክ አሸናፊ አትሌት ካቲ ፍሪማን እና ኢያን ትሮፕ አዲሱን ዘመቻን ተቀላቀሉ ።

“ ይህ ማለት እርስ በእርስ ለመረዳዳት በጋራ የምናደርገው ነገር ነው። አንዳችን አንዳችንን መርዳት። ” ካቲ ፍሪማን በክፍተቱን ማጥበብ ዘመቻ ላይ የተናገረቸው ነበር ።


Stolen Generations Accept Apology From Kevin Rudd On Sorry Day
CANBERRA, AUSTRALIA - FEBRUARY 13: Australian Prime Minister Kevin Rudd meets with Raymattja Marika after delivering an apology to the Aboriginal people for injustices committed over two centuries of white settlement at the Australian Parliament. Rudd's apology referred to the "past mistreatment" of all Aborigines, singling out the "Stolen Generations", the tens of thousands of Aboriginal children taken from their families by governments between 1910 and the early 1970s, in a bid to assimilate them into white society. (Photo by Andrew Sheargold/Getty Images) Credit: Andrew Sheargold/Getty Images

የመጀመሪያው ክፍተትን የማጥበብ መመሪያ ተመሰረተ


በ2008አም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስት ኬቨን ራድ ክፍተትን ማጥበብ የሚለውን አካሄድን ይፋ አደረጉ ፤ በዚያው አመትም ለተሰረቁት ህዝቦች(Stolen Generation ) በብሄራዊ ደረጃ ይቅርታን ጠየቁ ።

የመጀመሪያው ክፍተትን ማጥበብ የሚለው መመሪያ በሰባት ቁልፍ ነጥቦች ላይ ትኩረትን ያደረገ የነበረ ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል ረጅም እድሜ መኖር ፤ የህጻናት ሞትን ማስቀረት ፤ ትምህርት እና ስራ የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው ። ተስፋውም የነበረው በ 10 አመታት ውስጥ የሚጨበጥ ለውጥን ማምጣት ነበር።

በየዘመኑ ያሉ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እነዚህ እቅዶች የት እንደደርሱ የሚያሳዩ መረጃዎች በየአመቱ ሲደርሳቸው ቆይቷል ።

በ2019 አም ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመናቸው ያለው ክፍተት የ12 አመታትን ያህል እንደነበረ ገልጸው ነበር ።

“ ከተረት ያላለፍ ተስፋ ፤ ተስፋን የሚያስቆርጥ እና የማይጭበጥ ነው ፤ የጥሩ መመኝት ተረት ። ምኞቱ መልካም ቢሆንም ውጤቶቹ ግን አመርቂ የሚባሉ አይደሉም ። ይህ በሚያሳዘን ሁኔታ አሁንም ድረስ ያለ እውነታ ነው ።

ለረጅም ጊዜ ሊሰራ የሚችን መሰረት የያዘ አሰራርን ዘርግተናል ፤ እንዲህ ያለውን ለውጥ ለማምጣትም ነው ከነባር አውስትራሊያውያን ጋር በመሆን መስራት የያዝነው ። ”

የመጀመሪያው መመሪያ ይፋ ከሆነ ከአስር አመታት በላይ ሆኖታል። በግልጽ የሚታየው ግን ነገሮች በታቀደላቸው መሰረት እየሄዱ እንዳልሆነ ነው ።


SCOTT MORRISON CLOSING THE GAP PRESS CONFERENCE
SCOTT MORRISON CLOSING THE GAP PRESS CONFERENCE Credit: AAPIMAGE
This was more than a decade after the original strategy was launched. It was clear that things weren’t working, as only two of the original targets were on track, and the life expectancy gap was widening.

መመሪያው እንደገና መቀየር አለበት የሚለው ደርጃ መድረሱ


መመሪያው መቀየር ነበረበት ። ስለሆነም ማሻሻያ ተደርጎበት ስሙም ተቀይሮ ክፍተትን የማጥበብ ብሄራዊ ስምምነት ተብሏል። መንግስት በመሪነት የሚይዘው የመፍትሄ ሂደት ከመሆን ባሻገርም ፤ የነባር ህዝቦች የማህበረሰብ አባላት በጋራ እንዲሳትፉበት ሆኗል ።

የተቃዋሚው ፓርቲን ጨምሮ 80 የሚሆኑ እና በአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች ማህበረሰብ የሚመሩ ድርጅቶች ተመርጠው አዲሱን አሰራር በመቅረጽ ላይ ተሳትፈዋል ።

ይህ ቀላል እና ግልጽ የሆነ ነገር ነው፤ ፖሊሲዎች ለማህበረሳቦች ተሰርተው መሰጠት የለባቸውም ፤ ይልቁንም ከማህበረሰቡ አባላት ጋር በጋራ መሰራት አለባቸው።

አዲሱ ስምምነት 19 የተለዩ ግቦችን የያዝ ሲሆን በ 2031 አም ግቡን ይመታል ተብሎም ይጠበቃል። ከነዚህ መካከል ፦

· ህጻናት ጤነኛና ጠንካራ ሆነው እንዲወለዱ

· ተማሪዎች የመማር አቅማቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲጠቀሙ

· ወደ እስር ቤት የሚሄዱ የወጣት አጥፊዎችን ቁጥር መቀነስ

ከዚህም የሰፋ እና ሁሉን አቀፍ አካሂድን የሚከተል ፤ በጤና ላይ ብቻ ሳይሆን የመኖሪያ ቤትን ፤ ፍትህን ፤ ባህልን እና የኢኮኖሚ ተሳትፎን በአንድ ላይ የሚያካትት ነው ።

 


MALARNDIRRI MCCARTHY CLOSING THE GAP PRESSER
Lead Convener of the Coalition of Peaks Pat Turner speaks to the media during a press conference at Parliament House in Canberra. Source: AAP / LUKAS COCH/AAPIMAGE

በአሁን ሰአት ምን ደረጃ ላይ እንገኛለን ?


ቶም ካልማስ የለውጥ ጥሪን ማሰማት ከጀመሩ የአንድ ትውልድ ዘመን ተቆጠረ። በዛን ዘመን በህይወት የመኖር የእድሜ ክፍተቱ በነባር ህዝቦች እና ነባር ባልሆኑት አውስትራሊያውያን መካከል 11 አመታትን ያህል ነበር ።

ዛሬ 8 አመት አካባቢ ደርሷል ። ነገር ግን አሳሳቢ በሚባል ሁኔታ ነገሮች ወደ አሉታዊ አቅጣጫ እየተጓዙም ነው።

በቅርቡ በወጣው , ከ19ኙ እቅዶች መካከል 11 ያህሉ መሻሻልን ያሳዩ ቢሆንም አምስት ያህሉ ብቻ በታሰበላቸው እቅድ መሰረት እየተጓዙ እንደሆነ አሳይቷል ።

ሌሎች ተጨማሪ አበረታች ለውጦችም ታይተዋል ፤ለምሳሌ ህጻናት በሚፈለገው ጤናም ክብደት ጠንካራ ሆነው መወለድ ጀምረዋል ፤ በርካታ ወጣቶች የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያን ወይም ተመጣጣኝ ደረጃ ላይ መድረስ ችለዋል ።

በተቃራኒው ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እና የጎልማሶች በእስር ቤት የመቆየት ቁጥር መጨመርን አሳይቷል ።

“ በተያዙት ግቦች ላይ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ” ያሉት ፓት ተርነር ከተቃዋሚው ፓርቲ ናቸው።

“ ክፍተትን ማጥበብ ማለት እንዲሁ አሀዛዊ መረጃን ለማቅረብ ብቻ መሆን የለበትም ፤ መሆን ያለበት እውነተኛና ጠንካራ የሆነ ቤተሰብን መመስረት እና ብሩህ ተስፋን ማስፈን ላይ ነው ትኩረት መደረግ ያለበት። ልጆቻችን ጤናማ እና ኩሩ እንዲሁም ከባህላቸው ጋር የተገናኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ማለት ነው። ”

Subscribe or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.   

Do you have any questions or topic ideas? Send us an email to [email protected]


Share