የአውስትራሊያን የወደፊት ዕድል መቅረፅ ይሻሉን? ድምፅ ለመስጠት እንደምን መመዝገብ እንደሚችሉ እነሆን

Australia Explained: How to Enrol to Vote

Voting is compulsory in Australia, but there are some requirements that you will first need to meet. Credit: David Gray/Bloomberg via Getty Images

በእዚህ ዓመት ሌላ የፌዴራል ምርጫ ሊካሔድ ተቃርቧል፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅዎን ከመስጠትዎ በፊት ሊከዉኗቸው የሚገቡ እርምጃዎች አሉ። ድምፅዎን በመስጠት የሀገራችንን የወደፊት ዕድል ለመቅረፅ ለምዝገባ እገዛ የሚያደርጉልዎ በርካታ ምንጮች አሉ።


አንኳሮች
  • አውስትራሊያ ውስጥ የምርጫ ድምፅ መስጠ ግዴታ ነው፤ ሆኖም ድምፅ ለመስጠት መመዝገብ ይኖርብዎታል።
  • ለመምረጥ የአውስትራሊያ ዜጋ መሆንና ዕድሜዎ ቢያንስ 18 ዓመት መሆንን ግድ ይላል።
  • በኦንላይን ወይም የወረቀት ቅፅ በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ።
  • የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ድረ-ገፅ በተለያዩ ቋንቋዎችና በቀላል እንግሊዝኛ የተፃፉ መመሪያዎችን ያካተቱ መረጃዎችን ይሰጣል
የአዲሲቷን ሀገርዎ አውስትራሊያ ሕይወት ለመቃኘት ያስችልዎታል፤

ድምፅዎን በመስጠት የአውስትራሊያን መንግሥት ለመምረጥ የፌዴራል ምርጫ አንዱ ዕድል ነው።

አውስትራሊያ ውስጥ መምረጥ ግዴታ ነው፤ ይሁንና በቅድሚያ ሊያሟሏቸው ግድ የሚሉ መመዘኛዎች አሉ። ከእነዚያም ውስጥ አንዱ የአውስትራሊያ የምርጫ ኮሚሽን (አምኮ) ዘንድ መመዝገብ ነው።

ለመመዝገብ ብቁ ነኝን?

ምንም እንኳ ለአያሌ አውስትራሊያውያን የምርጫ ድምፅ መስጠት ግዴታም ቢሆን፤ ብቁነትዎን ማረጋገጥ ግድ ይላል።

የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን (አምኮ) ቃል አቀባይ ኢቫን ኢኪን-ስሚዝ “ማንኛውም ዕድሜው 18 እና ከእዚያ በላይ የሆነ ሰው ለመመዝገብና ድምፅ ለመስጠት ብቁ ነው”

“ሆኖም፤ ለመምረጥ ካሹ መመዝገብ ግድ ይልዎታል” ይላሉ።

መመዝገብ የሚገባኝ መቼ ነው?

ሁሉም አውስትራሊያውያን ዜግነት እንደተቀበሉ ፈጥነው እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ፤ በአውስትራሊያ መጪ ዕድል ላይ ድምፅ እንዲኖራቸው።

የምዝገባ ማብቂያ ጊዜ የምርጫ ቀን ከተቆረጠበት ቀን አንስቶ ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው። ከወዲሁ ተመዝግበው ያሉ፤ የአድራሻ ወይም የስም ለውጥ ካደረጉ እርስዎም በአንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ አዲሱን አድራሻዎንና ስምዎን ሊያስመዘግቡ ይገባዎታል።

“ይሁንና ምርጫ እስኪጠራ ድረስ መቆየት የለብዎትም፤ ከወዲሁ አሁኑኑ ሊከውኑት ይችላሉ” ሲሉ አቶ ኢኪን-ስሚዝ አክለው ይገልጣሉ።

እርግጥ ነው፤ ከቶውንም ለመመዝገብ ዕድሜዎ 18 እስኪሞላም መጠበቅ እንደሌለብዎት የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ምክትል የምርጫ ኮሚሽነር ካዝ ግሊሰን ሲናገሩ፤

“በ16 ዓመት ዕድሜ መመዝገብና 18 ሲደረስ የምርጫ ድምፅ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ይቻላል” ይላሉ።
Australia Explained: How to Enrol to Vote
MELBOURNE, AUSTRALIA - MAY 18: A view from entrance of a polling station during general elections to elect its parliament and prime minister in Melbourne, Australia on May 18, 2019. Source: Anadolu / Recep Sakar/Anadolu Agency/Getty Images

መመዝገብ የምችለው እንደምን ነው?

ቀላል የኦንላይን ቅጽ በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ። ሌላው ቀርቶ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክዎን በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ። በቀላሉ ወደ ያምሩ።

ምርጫዎ ከሆነና የኢንተርኔት ተደራሽነት ከሌለዎ፤ ከማናቸውም የአምኮ ጽሕፈት ቤት የወረቀት መመዝገቢያ ቅፆችን ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ቅፁ በፖስታ ቤት አድራሻዎ እንዲላክልዎ 13 23 26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የማንነት ማረጋገጫ ያስፈልግዎታል። ማንነትዎን ለማረጋገጥም የማንነት መለያዎን ይያዙ። ተጨማሪ መረጃ ማያያዝ አያሻዎትም፤ ማሳየት እንጂ።

ወ/ሮ ግሊሰን፤ የማንነት ማረጋገጫ በተለያዩ መልኩ መቅረብ ይችላል፤ በርካታ መረጃዎች በ በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅተው እንደሚገኙ ያስረዳሉ።

አክለውም “በርካታ ሰዎች የመንጃ ፈቃዶቻቸውን ይጠቀማሉ፤ ይሁንና ፓስፖርትዎን ወይም የሜዲኬይር ካርድዎን ሊጠቀሙ ይችላሉ”
Australia Explained: How to Enrol to Vote
A ballot box is seen inside the voting centre at Collingwood in Melbourne, Saturday, October 14, 2023 Credit: CON CHRONIS/AAPIMAGE
“እኒህ ነገሮች የሌለዎት ከሆነ የጋራ ብልፅግናው የምርጫ መዝገብ ላይ ሠፍሮ ያለ አንድ ምስክር መጠቀም ይችላሉ” ብለዋል።

አዲስ ዜጎች ምዝገባ ለማካሔድ የዜግነት የምስክር ወረቀት ይጠየቃሉ።

አንዳችም ዓይነት መታወቂያ የሌለዎት ከሆነ ወይም የት እንዳስቀመጡት ልብ ካላሉ ወይም ጠፍትዎቦት ከሆነ፤ ምትክ እንዲያገኙ ቀደም ብሎ ማመልከቱ ጠቃሚ ነው። ምትክ የማንነት መለያን ለማግኘት ክፍለ አገር ከክፍለ አገር የሚለያይ በመሆኑ፤ አንዳንዴ በተወሰነ ሁኔታ ምትክ ለማግኘት እስከ አራት ሳምንታት ሊፈጅ ይችላል።

ለእያንዳንዱ ምርጫ መመዝገብ ይኖርብኛልን?

አንዴ የምርጫ ምዝገባ ካካሔዱ በማናቸውም የፌዴራል፣ ክፍለ አገርና የአካባቢ የወደፊት ምርጫዎች መምረጥ ይችላሉ።

ለእዚህም ነው ወቅታዊ አድራሻና የስም ለውጥ ካደረጉ ያንን በወቅቱ ማሳወቁ አስፈላጊ የሚሆነው።
Australia Explained: How to Enrol to Vote
Social media, connection and woman typing on a phone for communication, app and chat. Web, search and corporate employee reading a conversation on a mobile, networking and texting on a mobile app Credit: Delmaine Donson/Getty Images

ቤት ከቀየርኩስ?

የምርጫ ቀን ከተቆረጠ በኋላ ወቅታዊ አድራሻዎን ለማሳወቅ የአንድ ሳምንት ጊዜ አለዎት።

ኢኪን-ስሚዝ “ለምሳሌ ያህል፤ ቤት የመቀየርዎ ዳታ ከደረሰን ማሳሰቢያ እንልክልዎታለን”

“ይሁንና ቤት ወይም ስም በቀየሩ ቁጥር ለውጥ ማድረግዎን ማሳወቁ ጠቃሚ ነው” ይላሉ።

በቀላሉ ድረ-ገጽን በመገብኘት ለውጥ ማድረግዎን ያሳውቁ።

ቀደም ሲል ለምርጫ መመዝገብ አለመመዝገብዎን እርግጠኛ ካልሆኑ ድረ-ገጽን ይጎብኙ ወይም እገዛ ማግኘት ካሹ በ 13 23 26 ስልክ ይደውሉ።

ለመመዝገብ ማን ሊያግዘኝ ይችላል?

የአምኮ ድረገጽ የምዝገባ ብቃትና መመሪያዎችን በቋንቋዎ አካትቶ ይዟል። እንዲሁም የስልክ አስተርጓሚ አገልግሎትና በቀላል የእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ ‘ቀላል የንባብ መመሪያዎች’ ተካትተው ይገኙበታል።

የፍልሰተኞ ዕገዛ ማዕከላትና ሌሎች የአካባቢ መድብለባሕላዊ ድጋፍ አገልግሎቶች ለመጀመሪያ ጊዜ መራጮች እንደምን እንደሚመዘገቡ እገዛ በማመላከት ይረዳሉ።

ማናቸውም አዲስ አውስትራሊያውያን ለመምረጥ ብቁ ከሆኑ አንስቶ ምዝገባ ለማካሔድ በእራስ የመተማመን ስሜት ሊያድርባቸው ይገባል። ማንም ይሁኑ ማን ድምፅዎ እንደሚቆጠር አይዘንጉ።

ድምፅ ለመስጠት ሳልመዘገብ ብቀርስ?

አውስትራሊያ ውስጥ ድምፅ መስጠት ግዴታ ነው፤ እናም ሳይመርጡ መቅረት ቅጣትን ያስከትላል። የግድ መምረጥ ያለብዎት የመሆኑን እውነታ ወደ ጎን እንበልና የምርጫ ድምፅዎን ባለመስጠትዎ ድምፅዎን የማሰማት ዕድል የሚጎድልብዎ መሆኑን ያሰላስሉ።

ድረገጽን ይጎብኙ ወይም ወደ አውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ቢሮ ለ2025 የፌዴራል ምርጫ ለመመዝገብ ያምሩ።
ስለ አዲሱ የአውስትራሊያ ሕይወትዎ ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃና ፍንጮች ለማግኘት የአውስትራሊያ ስትገለጥ ፖድካስትን ይከተሉ አሊያም ደንበኛ ይሁኑ።   

ጥያቄዎች ወይም ርዕሰ ሃሳቦች ካለዎት? ኢሜይል ይላኩልን።

Share