40 ፐርሰንት ያህሉ የአውስትራሊያውያን እርግዝናዎች በዕቅድ የሆኑ አይደሉም። ከእነዚያም ውስጥ 30 ፐርሰንት ያህሉ ውርጃ ይካሔድባቸዋል። አብዛኛዎቹ ውርጃዎች የሚካሔዱት 12ኛ ሳምንት የእርግዝና ጊዜ ውስጥ ከመዝለቁ በፊት ነው።
ውርጃ በአውስትራሊያ የጤና ክብካቤ ሥርዓት አማካይነት ግብር ላይ የሚውል ሕጋዊነትን የተላበሰ ሂደት ነው።
በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ ሐኪም የሆኑት ፕሮፌሰር ዳኒዬሊ ማዛ ውርጃን አስመልክተ ሲናገሩ “ሕጋዊ ማድረጉ አንድ ነገር ነው፤ ለሴቶች ስንዱና ተደራሽ ማድርጉ ሌላ ነገር ነው” ይላሉ።
ለምሳሌ፤ ዛሬ ሴቶች የቀዶ ሕክምናና ሕክምናዊ ውርጃዎችን የማድረግ አማራጭ አላቸው። ይሁንና አስፈላጊ የሆነውን መድኃኒት ለማዘዝ የተመዘገቡ ጠቅላላ ሐኪሞች ቁጥር ግና 10 ፐርሰንት ብቻ ነው። እንዲሁም፤ በተወሰኑ የአውስትራሊያ ክፍሎች አገልግሎቶች ውስን ናቸው።
የውርጃ ድንጋጌ ከፍለ አገርን መሠረቱ ያደረገ በመሆኑ፤ እንደሚኖሩበት አካባቢ አነስተኛ የሆኑ ልዩነቶች ይኖራሉ።ዳንዬሊ ማዛ፤ በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የጠቅላላ ሕክምና ዋና ኃላፊ
ፕ/ር ማዛ የክፍለ አገራት ሕጎችን አስመልክተው ሲናገሩ “ሕጎችን በተመለከተ ቪክቶሪያ ከሁሉም የላቀ ተራማጅ ናት"
“ሌሎች ክፍለ አገራት፤ ለምሳሌ ውርጃን ለመፍቀድ ከእርግዝናው ጊዜያት አኳያ ውስንነቶች አሏቸው። ክፍለ አገራት እርግዝናው (20 ሳምንታትን ካለፈ) በኋላ ለውርጃ ማን ወሳኝ እንደሚሆን ደንቦች አሏቸው” ብለዋል።
![ས་གནས་སྨན་པར་བློ་འདྲི་བྱེད་པ།_Getty kupicoo.jpg](https://images.sbs.com.au/5a/fe/19941c9e481db17eb5b0de313563/talking-to-gp-getty-kupicoo.jpg?imwidth=1280)
It's important to speak with your GP or contact the service that is nearest to you. Credit: Getty/kupicoo
የጠቅላላ ሐኪምዎ ኃላፊነቶች
ፕ/ር ማዛ ጠቅላላ ሐኪምዎ ዘንድ ቀርበው ምክር ከጠየቁ፤ አገልግሎቱን ራሳቸው የማይሰጡ ከሆነ ወደ ተገቢው አገልግሎት ሰጪዎች ዘንድ እንደሚያስተላልፍዎት ይናገራሉ።
ሴቶች ውርጃን ለማካሔድ ወይም ውርጃን አስመልክቶ ለመወያየት በሃይማኖት ወይም በሌላ ተቃውሞ ካላቸው ሐኪሞች ወደ ሌላ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲያስተላልፏቸው ግድ የሚሉ በሕግ ውስጥ የሠፈሩ በጥንቃቄ የተመሉ የተቃውሞ አንቀጾች አሉን።ዳንዬሊ ማዛ፤ በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የጠቅላላ ሕክምና ዋና ኃላፊ
ለእርስዎ የሚሆኑ ምን ዓይነት የውርጃ ዓይነቶች አሉ?
ሴቶች ከዘጠኝ ሳምንታት በፊት በአፍ የሚወስድ የሕክምና ውርጃ ለመውሰድ መስፈርቶችን ያሟላሉ።
የሕክምና ውርጃ ከሕክምናዊ ፅንስ ማጨንገፍ ጋር ተመሳሳይ ነው። ጠቅላላ ሐኪምዎ ሂደቱንና እርግዝናዎም ከማሕፀን ውጭ አለመሆኑን አስመልክቶ ምክር ሊሰጥዎት ይችላል።
ከዚያ በኋላ እርግዝናው ለውርጃ የሚዳርግ መድኃኒት ሊያዙልዎ ይችላሉ። ሕክምናዊ ውርጃ ቤት ውስጥ ሊከናወን ይችላል።
ሕክምናው በግል ክሊኒኮች፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችና በቴሌጤና ስልክ ወይም ቪዲዮ ምክር ይከናወናል።
![གློག་པར་འཕྲུལ་ཆས།_Getty Catherine McQueen.jpg](https://images.sbs.com.au/09/c5/94aad3ea481d8e9108e7e0b8f333/ultrasound-getty-catherine-mcqueen.jpg?imwidth=1280)
Credit: Getty/Catherine McQueen
የቀዶ ሕክምና ውርጃ የቀን ክሊኒክ ውስጥ ወይም ሆስፒታል ውስጥ በማደንዘዣ ብርሃን ሊከናወን ይችላል። ከዘጠኝ ሳምንታት እርግዝና በኋላ ማከናወን የሚቻል ሲሆን፤ በአብዛኛው ከ12 ሳምንትታ በፊት ይከናወናሉ።
የአገልግሎት ማለፊያ መንገዶች
እንደ ዶ/ር ክሌየር ቦይርማ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የቤተሰብ ምጣኔ ሕክምና ዳይሬክተር አባባል አማራጮች አካባቢ ተኮር ስለመሆናቸውና በአብዛኛውም የሚከተሉት አንድ ግልፅ መንገድ የለም። ይሁንና ጠቅላላ ሐኪምዎ ሊመራዎትና እርግዝናዎም ምን ያህል እንደገፋ ሊያረጋግጥልዎት ይችላል።
ምን ዓይነት አማራጮች ለእርስዎ ያሉ መሆኑን በከፊል የእርግዝናዎ ጊዜ በምን ያህል እንደገፋ ሊወስን ይችላል። እንዲሁም፤ አለመታደል ሆኖ አገልግሎቶችን ለማግኘት ምን ያህል ርቀው ሊጓዙ ግድ እንደሚሰኙ የሚኖሩበት አካባቢ ያሉ አገልግሎቶችም ወሳኝነት አላቸው።ዶ/ር ክሌየር ቦይርማ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የቤተሰብ ምጣኔ ሕክምና ዳይሬክተር
![ཁ་པར་བརྒྱུད་ནས་འཕྲོད་བསྟེན་ལ་ལྟ་བ།_Getty AJ_Watt.jpg](https://images.sbs.com.au/b4/07/7d99cae243a7a184a913f04a3886/telehealth-getty-aj-watt.jpg?imwidth=1280)
Credit: Getty/AJ Watt
እንዲሁም፤ አንዱን አገር አቀፍ ወይም ከፍለ አገርን መሠረታቸው ያደረጉ አገልግሎቶችን ማነጋገር ይችላሉ።
- ነፃ ለ24 ሰዓታት ከተመዝጋቢ ነርስ ጋር በ 1800 022 222 ያገናኝዎታል።
- በመላው አውስትራሊያ የተለያዩ አገልግሎትችን ይቸራል። የቤተሰብ ምጣኔ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከ15 ሳምንታት በታች ለሆነ እርግዝና የሕክምናና ቀዶ ሕክምና አማራጭ ውርጃ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
- የመረጃ መስመር ለቪክቶሪያ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል፤ 1800 696 784
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ አገልግሎትን ይሰጣል፤1800 008 463
- በሕዝብ ሆስፒታሎች አማካይነትም ውስን የሆኑ የውርጃ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።
ውርጃ ምን ያህል ውጪን ያስከትላል?
አብዛኛዎቹ የውርጃ አገልግሎቶች የሚከናወኑት በግል ክሊኒኮች ነው። የክፍያ ዋጋዎቹ እንደ እርግዝናዎ ጊዜ፣ የሚያከናውኑት ውርጃ ሕክምናዊ ወይም ቀዶ ሕክምና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይለያያል።
በሜዲኬይር በኩል ወጪዎን ማስመለስ ቢችሉም፤ በአብዛኛው የክፍተት ክፍያዎች አሉ።
ለምሳሌ ያህል፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የቤተሰብ ምጣኔ የሕክምናና ቀዶ ሕክምናን የቅናሽና የጤና ካርዶች ያሏቸውን ሰዎች አካትቶ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ለቀዶ ሕክምና ከኪስ የሚወጡ ክፍያዎች ከ $350 እስከ $450 ይደርሳሉ።
![འདོད་པ་མེད་ཀྱང་མངལ་ཆགས་པ།_Getty milanvirijevic.jpg](https://images.sbs.com.au/5d/eb/3c547f204a0789883396522c0dfb/unwanted-pregnancy-getty-milanvirijevic.jpg?imwidth=1280)
Credit: Getty/milanvirijevic
የተወሰኑ ሆስፒታሎች በሜዲኬይር ካርድ ያለ ምንም ወጪ አገልግሎታቸውን እንደሚቸር ይናገራሉ። አለያ ግና፤ በግል ክሊኒክ በኩል የሕክምና ውርጃ ለማድረግ ከወደዱ ወጪው እስከ $500 ይጠጋል።
ሂዩግ “በዚያም ላይ በተጨማሪ የሐኪም ምክሮች፣ የደም ምርመራዎች፣ አልትራሳውንድ ሁሉ ወጪን ግድ ይላሉ። ወጪያቸውም እስከ $1000 ይደርሳል። በሰሜናዊ ክፍለ ግዛት እርግዝናዎን ዘግይተው ያወቁና የቀዶ ሕክምና ውርጃን ካሹ ወጪዎ እስከ $8,500 ይደርሳል” ብለዋል።
ወ/ሮ ሂዩግ የጤና ኢንሱራንስ ሽፋኖችም የተለያዩ መሆናቸውን ሲያመላክቱ
“አብረውን ከሚሠሩት አብዛኛዎቹ ሴቶች እንደተረዳነው፤ በጤና ኢንሹራንስ ያልተሸፈነ በመሆኑ ሙሉ የወጪ ክፍያ ለመፈጸም ግድ ይሰኛሉ” በማለት ገልጠዋል።
የውርጃ አገልግሎቶችን የሚቸሩ የተወሰኑ የዩኒቨርሲቲ የጤና ማዕከላት አሉ።
ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውርጃን የሚሸፍን አጠቃላይ የግል ጤና ኢንሹራንስ ቢኖራቸውም፤ በአብዛኛው የቀዶ ሕክምና ውርጃ በሚካሔድባቸው የቀን አገልግሎት መስጫዎች ግና ሽፋን የላቸውም።