በአውስትራሊያ አነስተኛ ዋጋ ያለውን የህክምና አገልግሎት እንዴት ማግኘት ይቻላል?

Happy female gynecologist looking at smiling man touching stomach of pregnant woman in clinic

Credit: Maskot/Getty Images

ሜዲኬር አብዛኛዎቹን መሰረታዊ የህክምና አገልግሎቶች የሚደጉም ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል ሀኪም ጋር ክትትል ማድረግን ፤ የደም ምርመራን ፤ ኤክስሬ እና የተወሰኑ የቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን ያጠቃልላል። ከዚህ በተጨማሪም አመታዊ የአይን ምርመራን እና የህጻናት ክትባትን ይሸፍናል ።


Key Points
  • Medicare and the Pharmaceutical Benefits Scheme are part of Australia’s subsidised universal healthcare system
  • Medicare card holders pay little to no money on many medical services
  • If you visit a medical practise that ‘bulk bills’, you will not have to pay anything out of pocket
  • Medicare card holders may sometimes need to pay the difference between the full cost of a product or service and the amount the government subsidises
የአውስትራሊያ ዜጎች፤ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው እና ስደተኞች የነጻ ወይም አነስተኛ ዋጋ ያለውን የህክምና ክብካቤን እና መድሀኒቶችን የሜዲኬር አገልግሎትን በመመዝገብ ፤ አገር አቀፍ የሆነውን የጤና አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ።

ሜዲኬር ቅናሽ መድሀኒትን ከሚያስገኘው አሰራር ጋር በመጣመር ለመድሃኒቶች ዋጋ ድጎማን ያደርጋል ።

አገልግሎቱን ለማግኘትም በቀዳሚነት የሚያስፈልገው በ.በኩል , መመዝገብ ነው ።

“ አንድ ጊዜ በሜዲኬር ከተመዘገቡ ሰርቪስስ አውስትራሊያ የሜዲኬር ካርድዎን ይልክልዎታል ።ካርዱንም ወደ ሀኪም ጋር ሲሄዱ ይዘው መሄድ ይኖርብዎታል ።” ሲሉ የሰርቪስስ አስውስትራሊያ የመረጃ ኦፊሰር ይናገራሉ ።

መድሀኒቶችን በቅናሽ ዋጋ ለመግዛት ወይም አነስተኛ በሆነ ዋጋ ህኪምን ለማየት ወይም ቅድመ ክፍያ የማይጠይቁ ሀኪሞችን ሙሉ ለሙሉ በነጻ ለማየት ሜዲኬርን መጠቀም ይችላሉ ። ”

LISTEN TO
SG Calling an Ambulance Podcast image

How to call an ambulance anywhere in Australia

SBS English

20/12/202209:50

ጤንነት ካልተሰማዎት ምን ማድረግ አለብዎ ?

በአውስትራሊያ ጤንነት ካልተሰማዎት፤ በቅድሚያ የአጠቃላይ ሀኪሞችን በጤና ተቋማት ወይም ክሊኒክ ማየት አለብዎት ።ይሁን እና ህመምዎ ድንገተኛ ከሆነ ግን በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና ክፍል መሄድ አለብዎ ።

በአብዛኛው ጊዜ የሚሆነው ሰዎች ጤንነት ሳይሰማቸው ሲቀር ወይም አጠቃላይ ምርመራን ሲፈልጉ እንደ ዶ/ር ዳግላስ ሆር ያሉ የአጠቃላይ ሀኪም ጋር መሄድ ነው ።ዶ/ር ሆር በሲድኒ ሰሜናማ ቀበሌዎች በሀኪምነት ከአስርት አመታት በላይ አገልግለዋል።
በአውስትራሊያ ህሙማን ወደ ሀኪም ቤት የሚሄዱባቸውን ከ 80- 90 በመቶ የሚሆኑ የጤና ችግሮችን የሚሸፍኑት አጠቃላይ ሀኪሞች ሲሆኑ ፤ ወደ ተቋማቸው ማንም ይምጣ ማን ሁሉንም ያክማሉ ።
“ የበሽታዎትን ስሜቶች በማድመጥ ችግሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይሞክራሉ ፤ ለማከምም ምን መደረግ እንዳለበት በማሰብ ለህሙማኑ ያስረዳሉ ። ህሙማን ቀድሞ ያለባችውን የጤና ችግሮች በማጤን ፍቱን ህክምናን በማድረግ አጠቃላይ ሀኪሞች የተሻሉ ናቸው ይላሉ ፤ ”ዶ/ር ሆር
አጠቃላይ ሀኪሞች ህሙማኖቻቸውን ወደ ልዩ ሀኪሞች ለተጨማሪ ግምገማ ሊልኩም ይችላሉ፤ ይህውም ወደ አእምሮ ጤና ሀኪሞች ወይም ሆስፒታልን ሊያጠቃልል ይችላል ። አጠቃላይ ሀኪሞች ለህሙማኖቻቸው የመድሀኒት መግዣ ማዘዣዎችን መስጠት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ሰዎች ክትባትን እንዲከተቡ ምክርን መለገስ ይችላሉ ።

ያለክፍያ ህክምናን እንዴት ያገኛሉ ? የከፈሉትንስ ገንዘብ እንዴት ማስመለስ ይችላሉ ?

አንዳንድ የህክምና አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ በሚዲኬር የሚደጎሙ ወይም በከፊል የሚደጎሙ አሉ ። ይህ ማለት ህሙማን አልፎ አልፎ ለሚያገኙት አገልግሎት ልዩነቱን መክፈል ሊጠበቅባቸው ይችላል ።

በሜዲኬር በኩል የአጠቃላያ ሀኪሞችን ክፍያ የሚደጉመው ጠቃሚው አሰራር የነጻ ህክምና ይባላል ።
ምንም ክፍያን ከማይጠይቁት የህክምና ጣቢያዎችን ጋር ሄደው ህክምና ከተደረገልዎት ክፍያን መፈጸም አይጠበቅብዎትም ።

“ እንደሚሄዱባቸው የህክምና ተቋማት፤እንደሚያዩት ሀኪም እና በምን አይነት ሁኔታ እንዳሉ የሚወሰን ሲሆን ፤ ከዚህ በተጨማሪም ሀኪምዎ ለሚሰጥዎት አገልግሎት ክፍያውን በተመለከተ ፤ ከመንግስት በቀጥታ በሜዲኬር በኩል ወይም ከህሙማኑ በቀጥታ ማስከፈልን በተመለከት የመወሰን መብት አለው ።

የነጻ ህክምናን ከሚሰጡ ሀኪሞች ጋር ከሄዱ ሀኪምዎ ክፍያውን ከመንግስት በቀጥታ በሜዲኬር በኩል ያገኛል፡፡ ማለትም እርስዎ ከኪስዎ መክፈል አይጠበቅብዎትም ። ”ዶ/ር ሆር


Healthcare worker at home visit
Seniors and low-income Australians may access additional discounts. Credit: filadendron/Getty Images
የነጻ ህክምናን የማይሰጥ ሀኪም ጋር ሄደው ህክምናን ካደርጉ ፤ የህክምናዎን ወጪ ሙሉ ለሙሉ መክፈል ሊጠበቅብዎ ይችላል። ይሁን እና ከከፈሉት ውስጥ የተውሰነውን በሜዲኬር በኩል ሊመለስሎት ይችላል።

በሜዲኬር በኩል የሚመለሰውን ገንዘብ በፍጥነት ለማግኘት የተሻለው አማራጭ በሀኪምዎ ቢሮ በኩል ነው ። የእርስዎን ተመላሽ ለሜዲኬር ሊያቀርቡልዎት ይችላሉ ።ከዚያም ሜዲኬር ተመላሽ ገንዝብዎትን ወደባንክው ይልከዋል ።ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ወደሜዲኬር በመሄድ በኦን ላይን ማስገባት ይችላሉ ።
ጀስቲን ቦት - ሰርቪስስ አውስትራሊያ
ግብር ከፋይ አውስትራሊያውያን ከገቢያቸው በሚወሰደው ግብር ሜዲኬርን ይደጉማሉ።

ይህ ድጎማም የሚያበረክተው አስተዋጻኦ በእድሜ እና የቤተሰብ ሁኔታ አማካኝነት የሚወሰን ነው ።

ለችግር የተጋለጡ ፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸው አውስትራሊያውያን ፤ ቋሚ መኖሪያ ያላቸው ፤ የቅናሽ ካርድ እና የኮመን ዌልዝ ካርድ ባልቤቶች ተጨማሪ የሜዲኬር ጥቅማጥቅሞችን እና የመድሀኒት ቅናሽን ያገኛሉ ።

አቶ ቦት አያይዘውም የሜዲኬር አስራር እና የመድሀኒቶች ቅናሽ ገደብ አላቸው። እነዚህ ገደቦች ካለፉም ታካሚዎች የሚከፍሉት የህክምና ወጪ የሚቀንስላቸው ይሆናል ።

“ በአመቱ ውስጥ በቂ የሚባል የህክምና ወጪን ካወጡ ፤ የተቀመጠልዎትን ገደብ አለፉ ማለት ስለሚሆን ከዚያ በኋላ የሚከፍሉት ክፍያ አነስተኛ ይሆናል “

እንደ ቤተሰብ የተመዘገቡ ከሆነ ባል ፤ ሚስት እና ልጆች በአንድ ላይ ሲጣመሩ ገድቡ በቀላሉ ይደርሳል፤ በውጤቱም መድሀኒቶችንም ሆነ ሀኪም ጋር ሲሄዱ በቅናሽ እንዲከፍሉ ይረዳዎታል ፡”

ሜዲኬር እና የግል የጤና ኢሹራንስ

ህሙማን ከሚዲኬር የማያገኟቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት የግል ጤና ኢንሹራንስን ሊገቡ ይችላሉ።ከነዚህም መካከል የጥርስ ህክምና ፤ የአምቡላንስ አገልግሎት እና የተወሰኑ ክትባቶች ይጠቀሳሉ ።

የግል ጤና ኢንሹራንስን ህሙማን በግል ሆስፒታሎች እንዲታከሙ የሚጠቅም ሲሆን በተጨማሪም የማያጣድፉ የቀዶ ህክምናዎችን እና ሌሎች ምርመራዎችን በቶሎ ማግኘት እንዲቻል ይረዳል።

“ በመንግስት የጤና ተቋማት ስምዎ ከአጠቃላይ ህዝብ ዝርዘር ወስጥ የሚገባ እና ለወረፋ የሚቀመጥ ሲሆን ፤ ስምዎ መጀመሪያ ላይ ሰደርስ ቀዶ ህክምናው ይደረግልዎታል ፤ የግል ጤና ኢንሹራንስ ካለዎት ግን የራስዎን ሀኪም በግልም ሆን በመንግስት ሆስፒታል በመምረጥ ብዙም ወረፋን ሳይጠብቁ ቀዶ ህክምናዎን ማድረግ ይችላሉ ” በማለት ዶ /ር ሆር ያስረዳሉ

LISTEN TO
Here’s what you need to know about buying a private health cover image

Here’s what you need to know about buying a private health cover

SBS English

11/10/202107:13
በአውስትራሊያ ሀኪሞች እና የህክምና ተቋሞች የእንግሊዝኛ ቋንቋን መናገር ለማይችሉ ህሙማንን ምርመራዎችን ያደርጋሉ ።

ዶ/ር ሆር እንደሚሉት በሞባይል ስልክ ላይ ያሉ መተርጎሚያ አፖችን በመጠቀም መልእክትን እንደሚያደርሱ ይናገራሉ ። ነገር ግን ውስብስብ ለሆኑ ማብራሪያዎች በመንግስት የሚደጎሙትን የነጻ የአስተርጓሚዎች አገልግሎት እንደሚጠቀሙ ይናገርሉ ።

እዚያው ባለንበት ሆነን መደወል እንችላለን ። በመንግስት የሚደጎም የነጻ የአስተርጓሚዎች አገልግሎት ነው። አጠቃላይ ሀኪሞች እዚው ከጠረቤዛችን ላይ ስልኩን በድምጽ ማጉያ ላይ አድርገን በመደወል ህሙማኑ ሲናገሩ አስተርጓሚዎች ለሀኪሙ በማስተርጎም ችግራቸው ምን እንደሆነ ማስረዳት ይችላሉ ።”

Virtual medical consultation using a laptop
Telephone and online virtual consultations have become more common in Australia since the COVID-19 pandemic. Credit: Phynart Studio/Getty Images
ቴሌ ሄልዝ እና ኢ-ስክሪፕት (በስልክ የሚደረግ ምርመራ እና በስልክ መልእክት የሚላክ  የመድሀኒት ማዘዣ )

በርካታ ህሙማን ከሀኪሞቻቸው ጋር በአካል መገኘት ካልቻሉ በስልክ በሚደረግ ምርመራ እና በስልክ መልእክት በሚላክ የመድሀኒት ማዘዣ ተጠቃሚዎች መሆን ይችላሉ።

ይህ አገልግሎት በሜዲኬር እና የፋርማሲ አገልግሎት የሚሸፈን ነው ።

በስልክ ለሚደረግ ምርመራ ብቁ ለመሆን ሁሙማን ከሀኪማቸው ጋር ቢያንስ ለ12 ወራት ሲታከሙ የቆዩ መሆን ይኖርባቸዋል ።

“ በስልክ በሚደረግ ምርመራ ሀኪሞች ከሁሙማኑ ጋር በቀጥታ በስልክ ወይም በቪዲዮ በመገናኘት አገልግሎትን እንዲሰጡ ረድቷል ። ህሙማኑን ላማከም ችለናል ፤ ምክንያቱም በስልክ መልእክት የሚላኩ የመድሀኒት ማዘዣዎችን በኪው አር ኮድ አማካኝነት መላክ እንችላለን ፤ እንዲሁም በኢሜላቸው በመላክ ከሀኪሙ ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ሳይኖር ህሙማኑ ወደ መድሀኒት ቤት በመሄድ መድሀኒትን መግዛት ይችላሉ ። በማለት ዶ/ር ሆር ይናገራሉ።

 

Share