አውስትራሊያ ውስጥ ከየትኛውም ሥፍራ እንደምን አምቡላንስ መጥራት እንደሚችሉ

SG Photo Post_Call Ambulance.png

Ambulance. Credit: SBS

አውስትራሊያ ውስጥ በድንገተኛ የሕክምና አደጋ ወቅት አምቡላንስ ለማግኘት ፈጣኑ መንገድ 000 መደወል ነው። በሁሉም የአውስትራሊያ ክፍለ አገራትና ግዛቶች እንዴትና መቼ አምቡላንስ ማግኘት የሚያስችልዎን መምሪያ እነሆን። 


አንኳሮች
  • ሁሌም ለሕክምና ድንገተኛ አደጋ 000 ይደውሉ
  • ማንኛውም ሰው ከየትኛውም የአውስትራሊያ አካባቢ አምቡላንስ ደውሎ መጥራት ይችላል
  • በሚደውሉበት ወቅት ዝርዝርና የተለየ መረጃ ይስጡ
  • የአምቡላንስ አገልግሎቶች በሁሉም ክፍለ አገራትና ግዛቶች ነፃ አይደሉም
አምቡላንሶች ለታመሙና ለቆሰሉ ሰዎች ድንገተኛ ክብካቤ ለመስጠትና ካስፈለገም ወደ ሆስፒታል ለማድረስ የተሰናዱ ተሽከርካሪዎች ናቸው።

ዶር ሳይመን ሶውየር፤ የባለ ምዝገባ ፈቃድ ፓራሜዲክና የአውስትራሊያ ፓራሜዲክ ኮሌጅ የትምህርት ዳይሬክተር ናቸው። 

አምቡላንስ መቼ መጥራት እንዳለብዎ

ዶ/ር ሶውየር አንድ ሰው 000 ደውሎ አምቡላንስ ለመጥራት በሰፊና የተለያዩ አስባቦች ሳቢያ እንደሚሆን ያመላክታሉ።

በከፊል ነቅሰው ሲጠቅሱም፤  
  • የልብ ድካም ሲገጥመው ወይም እርስዎ የልብ ድካም አግኝቷቸዋል ብለው ሲያስቡ
  • ለመግለፅ የሚያውክ የደረት ሕመም ጭንቀት ሲገጥም
  • በድንገት ራስን መሳት ወይም ያልታሰበ ድካም፣ ወይም መዛል ወይም አካልን ማንቀሳቀስ አለመቻል
  • በአመፅ ድርጊት ሳቢያ የመወጋት ወይም የመቁሰል ሰለባ መሆን ሲገጥም
  • የአካል መቃጠል ሲገጥም፤ በተለይም ቃጠሎው ያገኛቸው ልጆች ከሆኑ አምቡላንስ መጥራት በጣሙን አስፈላጊ ነው
  • የሚጥል በሽታ፣ የአዕምሮ ጉዳት፣ ከክፍታ ሥፍራ በመውደቅ ራስዎን ለጉዳት የዳረጉ እንደሁ።
Worker Call an Ambulance While Senior Warehouse Manager Lying Down on Warehouse
You should call triple zero (000) if someone is seriously injured or needs urgent medical help. Credit: PixelsEffect/Getty Images
በአንዳድንድ ሁኔታዎች ሳቢያ ሕመምተኛን ፈልጎ ለማግኘት እንደሚያውክ ዶ/ር ሳውየር ይናገራሉ።
እርስዎን ፈልጎ ለማግኘት አዋኪ በሆነበት ሁኔታ፤ በትክክል የት እንደሚገኙ ካላስታወቁን የት እንዳሉ ማወቅ አንችልም።
ዶ/ር ሳይመን ሳውየር ባለ ሕጋዊ የምዝገባ ፈቃድ ፓራሜዲክና የአውስትራሊያ ፓራሜዲክ ኮሌጅ የትምህርት ዳይሬክተር 
ስለሆነም 000 በሚደውሉበት ወቅት በተቻለ መጠን ግልፅ መረጃ ለፓራሜዲክ መስጠቱ ጠቃሚ እንደሁ ዶ/ር ሶውየር ሲያስረዱ፤

"በሙዚቃ ትዕይንት መካከል፣ ትልቅ የገበያ አዳራሽ መካከል፣ ግልፅ የሆነ የመንገድ ምልክቶች የሌለበት የእርሻ ሥፍራ ወይም ቁጥር ያለበት የፖስታ ሳጥን የሌለበት ቦታ ከሆኑ የት እንዳሉ የማወቂያ መንገድ የለንም" ብለዋል።

ማንኛውም ሰው 000 መደወል ይችላል

000 የስልክ ጥሪ ነፃ ነው። በቀን ለ24 ሰዓታት፣ በሳምንት ለሰባት ቀናት ከማንኛውም የቤትና ቢሮ ስልክ፣ የክፍያ ስልክ ወይም የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልክ መደወል ይቻላል።

000 ለመደወል በቂ የስልክ መደወያ ክሬዲት ባይኖሮዎትም መደወል እንደሚችሉ ዶ/ር ሳይመን ሶውየር ሲገልጡ፤
ማንኛውም ሰው ወደ 000 አገልግሎት መደወል ይችላል። ቋሚ ተጠቃሚ መሆንን ወይም ዜጋ መሆንን ግድ አይልም። ልጆች መደወል ይችላሉ፤ አዋቂዎች መደወል ይችላሉ። አውስትራሊያ ውስጥ የትኛውም ሥፍራ ሽርሽር ላይ ሆነውም ሊሆን ይችላል።
ዶ/ር ሳይመን ሶውየር
መናገር ወይም መስማት የተሳናቸው ወደ 106 አጭር ፅሁፍ ወይም ቴክስት በመላክ የአገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
Calling for help
"You can be in a state you're not normally living in. You don't even need to be at home," says Dr Sawyer. Source: Moment RF / skaman306/Getty Images

000 ሲደውሉ ሂደቱ ምን ይሆናል?

የ000 ስልክ ጥሪዎን ተቀብሎ የሚመልሰው ሰው የእርስዎ ሁኔታ የድንገተኛ አደጋ ሁነትን ያሟላ እንደሁ ይወስናል።  

ለጥያቄዎቹ የሚሰጡት ምላሽ ወሳኝ መሆኑን ዶ/ር ሶውየር ልብ ሲያሰኙ፤

"በተቻለ መጠን ሁኔታው ላይ ያተኮረ ይሁኑ። እንደ ፓራሜዲክ ስናገር በትክክል ምን እንደሆነ ማወቁ ለተለያዩ ምክን ያቶች አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ያህል የመኪና አደጋ ገጥሞኛል፣ ፍቅረኛዬ አይተነፍስም / አትተነፍስም የደረት ሕመም ወዘተ..." ብለዋል።

አክለውም፤ ስልክ ተቀባዩ ምን ያህል ሰው እንደታመመ ወይም እንደ ቆሰለ ሊጠይቅ እንደሚችል ሲያስገነዝቡ

"ይህ በጣሙን ጠቃሚ ነው። ስለምን፤ አንድ ሰው ከሆነ አንድ አምቡላንስ በቂ ሊሆን ይችላል። ሶስት ሰዎች የቆሰሉ ከሆነ ግና አንድ አምቡላንስ ብቻ በቂ ሊሆን ስለማችል ተጨማሪ መላክ ሊኖርብን ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል።

የእድሜና ፆታ መረጃም እንዲሁ አስፈላጊ ነው። ያም ፓራሚዲኮች ሕክምና ለመስጠት የሚያስፈልጓቸውን ክብካቤ መስጫዎችና ቁሳቁሶች ይዘው ለመገኘት ያግዛቸዋል። ግለሰቡ ከአንድ ፆታ ወደ ሌላ ፆታ የተቀየረ ወይም ገና በሴትነት ወይም በወንድነት ያልተለየ ግልሰብንም ያካትታል።

ዶ/ር ሶውየር በተለይም የግልሰቡን ዕድሜ የማወቅ ጉዳይ አንስተው "ለምሳሌ፤ በጣም ትንሽ ልጅ፣ አረጋዊ ወይም በሁለቱ ዕድሜዎች መካከል ያሉ ስለመሆንዎ። ማወቁ ምን ዓይነት ሕክምና መስጫ መያዝና ምን ያህል የመድኃኒት መጠን መስጠት እንዳለብኝ ከግምት ውስጥ አስገባለሁ። በዚያ መልክ መሰናዶ ማድረግ ያስፈልገኛል" ሲሉ ያስረዳሉ።
EMERGENCY SERVICES WA
Ms Mackay says not all calls to triple zero result in an ambulance being dispatched. Source: AAP / RICHARD WAINWRIGHT/AAPIMAGE

ለእያንዳንዱ ጥሪ አምቡላንሶች አይላኩም

ሊንዲሴይ ማኬይ የአምቡላንስ ቪክቶሪያ ተጠባባቂ የኦፕሬሽን ኮሙኒኬሽንስ ዳይሬክተር ናቸው።

የሁሉም 000 ስልክ ጥሪዎች ውጤት አምቡላንስ የሚያስልክ አይደሉም ባይ ናቸው።
አውስትራሊያ ውስጥ ከአምስት አንዱ የስልክ ጥሪ የድንገተኛ አደጋ ደራሽ አምቡላንስ የሚያስልኩ አይደሉም።
ሊንዲሴይ ማኬይ፤ የቪክቶሪያ አምቡላንስ ተጠባባቂ የኦፕሬሽን ኮሙኒኬሽንስ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር
አክለውም "አንዴ መረጃዎን ለስልክ ጥሪ ተቀባዩ ከሰጡ በኋላ ሥርዓቱን ተከተለው ከውሳኔ ላይ ይደርሳሉ..." ያሉ ሲሆን፤

አያይዘውም፤ ጥሪውን በድንገተኛ አደጋ ውስጥ ካላከቱት ከሐኪም ከመድኃኒት ቤት ጋር ሊያገናኙዎት ይችላሉ። የቆሰሉ ከሆነ ሐኪም ወይም ነርስ ሊያስልኩልዎት እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ለአገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ ዓይነቶች

በርካታ የተለያዩ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ዓይነቶች አሉ። ሁሉም በተለየ መልኩ የሕክምና ቁሳቁሶች የተገጠመላቸው ናቸው። እነሱም፤
  • ቫኖች (በአብዛኛው የተለመዱት ዓይነት)
  • ፎር ዊል ድራይቭስ
  • ሞተር ብስክሌቶች
  • አውቶቡሶች
  • አውሮፕላኖች
  • ሂሊኮፕተሮች
Helicopter- Health Victoria
An ambulance helicopter lands at the Alfred Hospital in Melbourne, Thursday, June 9, 2022. Source: AAP / DIEGO FEDELE/AAPIMAGE

ጊዜያዊ ምርመራዎች

ፓራሜዲኮች አንዴ ከሥፍራው ከደረሱ ጊዜያዊ ምርመራን እንደሚያካሂዱ ዶ/ር ሳውየር ሲያስረዱ፤

“እኛ የከሆስፒታል ውጪ ኤክስፐርቶች ነን። ያለፈ የሕክምና ታሪክዎን አስመልክተን በርካታ ጥያቄዎችን እንጠይቃለን። አለርጂ እንዳልበዎትና መድኃኒት እየወሰዱ እንደሁ እንጠይቃለን። እኒያ ሁሉ መረጃዎች የምንጠቀመው ምን ገጥሞዎት እንደሆነ ለመረዳትና ጊዜያዎ ምርመራ የምንለውን ፈርጅ ለማስያዝ ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ በአብዛኛው አምቡላንስ ወደ ሆስፒታል የሚወስድዎት ቢሆንም፤ ሁሌም እንደማይሆን ግና ገልጠዋል።
Tasmanian Emergency Services vehicle
If you live in Tasmania, the state government waives the ambulance costs in most cases. Source: AAP / ROB BLAKERS/AAPIMAGE

ለአምቡላንስ ጥሪ ከፋዩ ማን ነው?

ሜዲኬይር የአምቡላንስ አገልግሎቶችን አይሸፍንም።

የአምቡላንስ ክፍያ እንደ አስተዳደር አካባቢውና እንደ ሕመምተኛው ሁኔታ ይወሰናል።

የመንግሥት አምቡላንስ አገልግሎቶች በጥሪ ወይም በኪሎ ሜትር ወይም በሁለቱም ያስከፍላሉ።
እንደ ኩዊንስላንድና ታዝማኒያ ያሉ ክፍለ አገራት ለሁሉም ነዋሪዎች ነፃ የአምቡላንስ ሽፋን አላቸው። በሌሎች ክፍለ አገራትና ግዛቶች ግና የአባልነት ክፍያ መክፈልን ግድ ይልዎታል። አባል ባይሆኑም አምቡላንስ ሊጠቀሙ እንደሚችሉና አገልግሎቱን ከተጠቀሙ በኋላ ግና ክፍያ እንደሚፈፅሙ ልብ ሊሉ ይገባል።
ዶር ሳይመን ሶውየር ባለ ምዝገባ ፈቃድ ፓራሜዲክና የአውስትራሊያ ፓራሜዲክ ኮሌጅ የትምህርት ዳይሬክተር
ዶ/ር ሶውየር የሚኖሩበት አካባቢን አምቡላንስ አገልግሎት እንዲያነጋግሩ ምክረ ሃሳባቸውን ሲቸሩ፤

"ድረ ገፃቸውን ሊጎበኙ ወይም ሊደውሉሏቸው ይችላሉ። 000 ሊደውሉ አይገባም። የአምቡላንስ አገልግሎቶች ዘንድ ደውለው አባል ለመሆን ግድ ይልዎት ወይም አይልዎት እንደሁ ሊጠይቁ ይችላሉ። እነሱም ምክራቸውን ይለግስዎታል" ያሉ ሲሆን፤

አክለውም "አባል መሆን የሚያሻዎ ከሆነም ክፍያው ርካሽ ነው። በአብዛኛው ለላጤ በዓመት $50 ወይም በቤተሰብ $100 ነው"
"የግል የጤና ኢንሹራንስ ያለዎት ከሆነም አንዳንዴ የአምቡላንስ ክፍያ በዚያው የሚሸፈን ይሆናል" ብለዋል።

ስለ ክፍያ ዋጋ ተጨማሪ መረጃ ካሹ የሚኖሩበትን ክፍለ አገር ድረ ገጽ ይጎብኙ።
በተወሰኑ ክፍለ አገራት የአምቡላንስ ክፍያዎያዎች ለጡረታ ቅናሽ፣ ለጤና ካርድ ቅናሽ ተጠቃሚዎችና የቀድሞ ወታደሮች ጉዳዮች ዲፓርትመንት የወርቅ ካርድ ባለቤቶች አንድም ክፍያቸው ዝቅ ያለ ነው፤ አለያም ከነአካቴው ከክፍያ ነፃ ናቸው።

አስተርጓሚዎች አሉ

ወ/ሮ ማኬይ እንግሊዝኛን አጣርተው የማይናገሩ ከሆኑ የአገልግሎት ፈቃድ ያለውን ከአንድ በላይ ቋንቋ ተናጋሪ አስተርሚን በየትኛውም ሂደት ደረጃ መጠቀም ይችላሉ።

“ሙሉ አገር አቀፍ የቋንቋ መስመር አለን። 000 በሚደውሉበት ወቅት እነሱን ያነጋግራሉ። እምብዛምም እንግሊዝኛ ባይችሉ እንኳ ቢያንስ 'I speak…' ብለው የሚናገሩትን ቋንቋ ዓይነት ሊናገሩ ይችላሉ። እናም ቋንቋዎን ከሚናገር የአስተርጓሚ አገልግሎት ሰጪ ጋር ያገናኝዎታል" በማለት አስረድተዋል።

Share