የአውስትራሊያን የመንጃ ፈቃድ እንዴት ማግኘት ይቻላል?

Driver training exam.

Young girl taking lessons for driving on the road in Auckland, New Zealand. Credit: nazar_ab/Getty Images

መኪና መንዳት ነፃነትን የሚረጋግጥ ሲሆን ሥራ የመቀጠር ዕድልንም ያሰፋል። የመንገድ ደህንነት የማስጠበቅ ታላቅ ኃላፊነትም ይዞ ይመጣል ። በአውስትራሊያ አሽከርካሪዎች ሙሉ የመንጃ ፈቃዳቸውን ከማግኘታቸው በፊት የተለያዩ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ። አዲስ መጥ ሰፋሪዎች በአገራቸው የነበራቸውን የመንጃ ፈቃድ ወደ አውስትራሊያ መንጃ ፈቃድ የሚቀይሩበት አሠራር ያለ ሲሆን ፤ ሊዚሁ ሲባል የተዘጋጀውንም የመሽጋገሪያ ሂደትን ማለፍ አለባቸው ። ይሁን እና ይህ እንደ ግለሰቦቹ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል ።


Key Points
  • በአውስትራሊያ የሞተር መኪናዎችን ለማንቀሳቀስ የመንጃ ፈቃድ መኖር ግድ ይላል
  • የአውስትራሊያ ከተሞች እና ግዛቶች የመንጃ ፈቃድን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የሚወስኑ ሲሆን ህጉም በዚሁ ልክ የተለያየ ነው
  • ሙሉ የመንጃ ፈቃድን ከመገኘቱ በፊት አሽከርካሪዎች የተለያዩ ፈተናዎችን ማለፍ ይኖርናቸዋል
  • አዲስ መጥ ሰፋሪዎች በአገራቸው የነበራቸውን የመንጃ ፈቃድ ወደ አውስትራሊያ መንጃ ፈቀድ የሚቀይሩበት አሰራር ያለ ሲሆን ፤ ሊዚሁ ሲባል የተዘጋጀውንም የመሽጋገሪያ ሂደትን ማለፍ አለባቸው ። ይሁን እና ይህ እንደ ግለሰቦቹ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል ።
የመንጃ ፈቃድ ባለቤቱ ህጋዊ በሆነ መንገድ መኪናን እንዲያሽከረከር የሚሰጥ ይፋዊ ፈቃድ ነው ።

በአውስትራሊያ በስልጠና መልክ የመንጃ ፈቃድን ለማግኘት የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። በዚህም መሰረት ስልጠናው ሊያሽከረክሩት እንደፈለጉት የመኪና አይነት እና መጠን የተለያየ ይሆናል ።

የመጀመሪያው ደረጃም የመንገድ ህጎችን መማር ነው ።ከዚያም የተለማማጅ ፈቃድን ለማግኘት ለፈተና ማመልከት ይቻላል ፤ በተለምዶም ኤል (L ) ወይም ለማጅ በመባል ይታወቃል ። የለማጅ ፈቃድ ኤል (L ) ከአስተማሪ ጋር በመሆን መኪናን ለመለማመድ ይረዳል።

“ በኒው ሳውዝ ዊልስ የመንጃ ፈቃድን ለማግኘት ዝቅተኛው እድሜ 16 ነው። በተጨማሪም የአይን እይታ ምርመራን እና የእውቅት መመዘኛ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ ይላል ።” የእውቀት መመዘኛ ፈተናችን የመገገድ ህጎች ላይ የተመሰርቱ ሲሆኑ ይህንንም በማወቅዎም በመንገድ ላይ ደህንነትዎ የተጠበቀ ይሆናል ። ” ሲሉ ሉዪስ ሂገንስ ዊተን የኒው ሳውዝ ዌልስ የትራንስፖርት እና የመንገድ ድህንነት ስትራቴጂ እና ፖሊሲ ዲሬክተር ሲሉ ያስረዳሉ ።

Road Safety
Expert driving instructors are especially trained to teach learner drivers in a stress-free environment, L Trent's Frank Tumino says. Source: Getty / Getty Images
ለማጅ ሲሆኑ የሚከተሉት ማክበር አለብዎ ፦
  • ሁል ጊዜም ሙሉ የመንጃ ፈቃድ ያለው አሽከርካሪ ከአጠገብዎ በመገኘት ሊከታተልዎት ይገባል ፤
  • ለማጅ መሆንዎን የሚያሳይ ምልክት ከመኪናው ውጭ በግልጽ መቀመጥ አለበት
  • ከመንዳትዎ በፊት የአልኮል መጠጥም ሆነ አደንዛዥ እጽ መውሰድ አይችሉም
  • የተቀመጡትን የመንገድ ላይ የማሽከርከር ፍጥነት ገደቦችን ማግበር አለብዎት
  • የተንቀሳቃሽ ስልክን በፍጹም መጠቀም አይችሉም

ወደ ጊዜያዊ የመንጃ ፈቃድ ደረጃ ከፍ ማለት

ለማጅ አሽከርካሪዎች እንደ እድሜያቸው ደረጃ በለማጅነት ለተወስነ ጊዜ የግድ መቆየት ይኖርባቸዋል ። ብቻቸውን ለማሽከርከር እና የጊዜያዊ የመንጃ ፈቃድን ( P ) ለማግኘት የተግባር ፈተናን ማለፍም ይጠበቅባቸዋል ።

ፍራንክ ቱሚኖ በአውስትራሊያ ታላቁ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም አሰልጣኝ ሲሆኑ ፤ተማሪ አሽከርካሪዎች የባለሙያን እርዳታን እና የቤተሰብ እገዛን በከፍተኛ ደርጃ ያስፈልጋቸዋል ይላሉ ። ይህ እገዛም የለማጅ ፈተናን በቀላሉ እንዲያልፉ ያደርጋቸዋል ።

“ የአሽከርካሪዎች ትምህርትን ከፍሎ በመማር የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጅግ አስፈላጊ የሚባሉ ስልጠናዎችን ከመሰረቱ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ድረስ ለማወቅ ይችላሉ፤ ትክክለኛ የሆኑ የማሽከርከር ዘዴዎችን ከመሰረታቸው በመነሳት እውቀቱን ማዳበር እጅግ ጠቃሚ ነው ። ”


Driver lience,Indian driver
The Australian graduated licensing scheme ensures novice drivers slowly build up their driving and road safety skills before they are fully licensed. Source: Getty

የመንጃ ፈቃድን በተመለከት ከአዲስ መጥ ነዋሪዎች ጋር የሚደረግ ውይይት

አዲስ መጥ ነዋሪዎች ከመጡበት አገር የመንጃ ፈቃደን ይዘው ከመጡ ፤ ወደ አውስትራሊያ የመንጃ ፈቃድ በህጋዊ መንገድ መለወጥ አለባቸው ።

ሉዊስ ሂገንስ ዊተን እንደሚሉት ሂደቱ እንደ ሁኔታው ሊለያይ ይችላል ።

“ የሚከተሉት ሂደቶች እንደመጡበት አገር ፤ የመንጃ ፈቃዱ እንደተሰጠበት ቦታ ፤ ለምን ያህል ይዘውት እንደቆዩ ፤ እና በመጡበት አገር ያለው የመንጃ ፈቃድ አሰራር ላይ ተመስርቶ ሊለያይ ይችላል።
የመጡበት አገር የመንጃ ፈቃድ አሰራር በጣም የተለየ ከሆነ ፤ አብዛኛውን ጊዜ ተጨማሪ ፈተናዎችን መውሰድ ሊጠበቅብዎት ይችላል ፤ ፈተናዎችም እንደመጡበት አገር እና እንደሚወስዷቸ የመንጃ ፈቃድ አይነቶች ሊለያዩ ይችላሉ ። "
ሉዊስ ሂገንስ ዊተን - ከኒው ሳውዝ ዌልስ ትራንስፖርት
አንዳንድ ጊዜም ከውጭ አገር ህጋዊ የመንጃ ፈቃድን ይዘው መጥተው ወደ አውስትራሊያ የመንጃ ፈቃድን ለመቀየር ሲሹ ፤ ለፈተናው የሚሰጥዎት አንድ እድል ብቻ ሲሆን ፈተናውን ከወደቁም እንደገና ወደ ለማጅ አሽከርካሪ ዝቅ ሊሉ ይችላሉ ።

አቶ ቱሚኖ እንደሚሉት በሌላ አገር ማሽከርከርን ለምደው የሚመጡ አሽከርካሪዎ ፈተናውን በቀላሉ እንዲያልፉ የተለየ አይነት ስልጠና ያስፈልጋቸውል ።

“ ለአዲስ መጥ ነዋሪዎች የተለያየ አቀራረብ ያላቸው ስልጥናዎች አሉን ፤ ስለሆነም በመንገድ ህጎችን ላይ ሰፋ ያለ ትኩረትን እናደርጋለን ። እንዲሁም በነበሩበት አገር ያዳበሯቸውን ልማዶች ለመስበር ሰፋ ያለ ትኩረትን እንሰጣለን ። ግልጽ ከሆኑት እውነታዎች አንዱን ብንጠቅስ ፤ እዚህ የምንነዳው በመንገዱ የግራ አቅጣጫ ሲሆን ለአዲስ መጥ ነዋሪዎችም ዋነኛ ተግዳሮት ሊሆንባቸው ይችላል ።”

Enjoying travel. - Stock image
Migrants from countries with similar licensing systems to Australia can easily convert their driving permits. Those who hold overseas licences from less regulated countries may need to undergo further examinations. Credit: Deepak Sethi/Getty Images
የጊዜያዊ የመንጃ ፈቃድዎን ይዘው በምንም አይነት የአልኮል መጠጥን መጠጣት አይፈቀድልዎትም ፤ እንዲሁም የሚነዱበት ፍጥነትንም በተወሰነለት ደረጃ የግድ መጠበቅ አለብዎት ።
ወደ ሙሉ አሽከርካሪነት ፈቃድ ከመሸጋገርዎ በፊት የመንገድ ላይ የማስጠንቀቂያ ህጎች ፈተናን ማለፍ ሊጠበቅብዎት ይችላል ።
የቅጣት መጥሪያዎች ለከፍኛ ቅጣቶች ሊዳርጎት እና የመንጃ ፈቃድዎንም ለጊዜው ሊያዝብዎት ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊነጠቁ ይችላሉ ።
“ በአገር ደርጃ በከፍተኛ ደረጃ በህግ የታጠርን ነን ። ከተወሰነው የማሽከርከር ፍጥነት በላይ መንዳት እና ያልተፈቀዱ ነገሮችን ተጠቅሞ ማሽከርከር ከፍተኛ ቅጣትን ያስከትላል ። ” ሲሉ አቶ ቱሚኖ ያስጠነቅቃሉ።
NSW Police
Police in Australia conduct frequent roadside breath tests to ensure drivers are not intoxicated. Heavy fines apply for those who flaunt road rules. Credit: wikimedia commons

ለስደተኞች እና አዲስ መጥ ነዋሪዎች የተዘጋጀ ልዮ የአሽከርካሪዎች ስልጠና

በመላው አውስትራሊያ የሚገኙ የማህበረሰቦች እና የሰፈራ አገልግሎት ድርጅቶች ፤ በአነስተኛ ዎጋ ወይም በነጻ ለስደተኞች እና አዲስ መጥ ነዋሪዎች ተብለው የተዘጋጀ ፤ ልዮ የአሽከርካሪዎች ስልጠና መርሀ ግብሮች አሏቸው ። ዘ ግሬት ሌክ ኤጀንሲ ፎር ፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት TheGreat Lakes Agency for Peace and Development (GLAPD) ከማህበረሰቡ ጋር ሆነው ከሚሰሩ ድርጅቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን ፤ በባህል እና ቋንቋ ዝንቅ ከሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር
በቅርብ ይሰራል ።
የድርጅቱ ዋና ማናጀር ኢማኑኤል ሙሶኒ እንደሚሉት ፤ ይህንን መርሀ ግብር የጀመሩት ለማጅ አሽከርካሪዎች ፈተናቸውን በቀላሉ እንዲያልፉ ለመርዳት ሲሆን ፤ በርካታ አዲስ መጥ ብቸኛ እናቶች የህዝብ የመጓጓዣዎችን ብቻ የሚገለገሉ መሆናችውን ከተረዳን በኋላም ነው መርዳትን የጀመርነው ይላሉ ። ድርጅቱ የአሽከርካሪዎች አሰልጣኞችን የሚመርጠውምው ከማህበረሰቡ አባላት ውስጥ ስለሆነ ውጤቱ አመርቂ ነው ። “

አንዳንዶቹ ሲመጡ ምንም አይነት የመኪና ማሽከርከር እውቀት የሌላችው እና መሪን መጨበት እንኳ የማይችሉ ናቸው ፤ ስለሆነው አሽከርካሪው ትምህርቱን የሚሰጣቸው ከመነሻው ጀምሮ የመንጃ ፈቃዳቸውን እስክሚያገኙበት ደርጃ ድረስ ነው ።
Side View Portrait Of Cheerful Young Woman Sitting In Car
Being a fully licensed driver offers independence and opens up job prospects. Credit: Narong Jongsirikul / EyeEm/Getty Images/EyeEm
ሚሸሊን ኒያንታባራ የመርሀ ግብሩ ተጠቃሚ አዲስ እናት ናት ።

ወ/ሪት ኒያንታባራ በአገሯ ኮንጎ መኪናን በፍጽም አሽከርክራ የማታውቅ ሲሆን መሪን መጨበጥንም በጣም ትፈራለች ። ወደ ስራ ለመሄድ የህዝብ መጓጓዣን መጠቀም ጊዜዋን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚውስድባት ከተረዳች በኋላ መኪና ማሽከርከር መማር እንዳለባት ወስናለች ። በተለይም የህጻን ልጅን መግፊያን በህዝብ መጓጓዣዎች መጫን እና ማውረድ አዳጋች ነው ።

ምንም እንኳ የመንጃ ፈቃድ ልምምድን በአስተማሪ እና በጓደኛ በኩል ከዚህ ቀደም ያገኘች ቢሆንም ፈተናውን ግን ለሁለት ጊዜ ወድቃለች ። በመጨረሻም ከ (GLAPD) ጋር ልምምድን ካደረገች በኋላ ለማለፍ ችላለች ።

የውጤቷ ምንጭም ከእሷ አገር በመጣ አስተማሪ በመማሯ በመሆኑ ውለታው መውሰድ አለበት ትላለች ።

“ ምን እያለኝ መሆኑን በደንብ መረዳት እችል ነበር ፤ ሁለተኛው ነገር ደግሞ በጣም ጥሩ ልምድ አለው ። ”

እሷ እንደምትለውም የመንጃ ፈቃዷን ማግኘቷ የእሷንም እንዲሁም የልጇንም ህይወት ለውጦታል ።
“ አሁን መሂድ ካለብኝ ከማንኛውም ቦታ መሄድ እችላለሁ ፤ በፊት በጣም ከባድ ነበር ፤ አሁን የግሌ መኪና አለኝ ፤ ወደ ሰራ መሄድ ቀላል ሆኗል ፤ ልጄንም ይዤ ለመውጣት በጣም ቀላል ነው ። ህይወትን በጣም ያቀላል በተለይ ልጅ ላላቸው እናቶች ። ”
ወ/ሪት ኒያንታባራ ሌሎች እናቶች መኪናን የማሽከርከር ፍርሀታቸውን እንዲያስወግዱ ትመክራልች ። ምክንያቱም የሚገኘው ጠቀሜታ ህይወትን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀይር ነው ።

“ ሊያስፈራ ይችላል ፤ ነገር ግን ውጤታም ስትሆኑ ፤ የመንጃ ፈቃዳችሁን ስታገኙ ፤ ከዚህ ቀደም የሆነውን ፈጽሞ አታስታውሱትም ፤ ምክንያቱም ህይወታችሁን ቀይሮታልና ። “

የመንጃ ፈቃድን እንዴት ማግኘት ይቻላል


Share