አንኳሮች
- አውስትራሊያ 'በደል ማሳያ የለሽ ፍቺ' አላት። ከተጋቢዎች አንዳቸው ያለ ሌላኛዋ / ሌለኛው ፈቃድ ወይም ማብራሪያን ለማቅረብ ግድ ሳይሰኙ ለፍቺ ማመልከት ይችላሉ።
- በርካታ ተፋቺዎች የወላጅነትና የገንዘብ ጉዳዮችን አስመልክቶ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ዕልባት ያበጃሉ።
- የአውስትራሊያ ሕግ ሥርዓት ተፋቺዎች ከፍርድ ቤት ሙግት ይልቅ በሽምግልና እንዲዳኙ ያበረታታል።
ፍቺ በቀላሉ ሲገለጥ የትዳር መፍረስ ነው። ይሁንና ፍቺ የሚያስከትላቸውን ብርቱ የመንፈስ ሁከት፣ የወላጅነትና የገንዘብ እንድምታን ተከትሎ ቤተሰቦች በአብዛኛው ያለ ውጪ እርዳታ ከግብብነት ላይ የሚያደርስ የገንዘብ ክፍፍል ላይ ለመድረስ ይቸገራሉ።
አውስትራሊያ ውስጥ ባለ ትዳሮች ለፍቺ ሲያመለክቱ ትዳራቸው ከማይጠገን ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከ12 ወራት በላይ መለያየታቸውን፣ በወላጅነትና የገንዘብ ስምምነት ላይ የደረሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ግድ ይላቸዋል።
በርካታ ተፋቺ ጥንዶች ወደ ፍርድ ቤት ከማምራታቸው በፊት የወላጅነትና የገንዘብ ጉዳዮችን አስመልክቶ በወጉ ከስምምነት ላይ ለመድረስ መሞከር ይጠበቅባቸዋል።
ይህንኑ አስመልክተው ኢሊኖር ላዩ የላንደርና ሮጀርስ የሕግ ባለ ሙያ ሲያስረዱ፤
“ወላጆች ልጆችን በተመለከቱ ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት ከማምራታቸው በፊት የቤተሰብ አለመግባባት መፍቻ ላይ መሳተፍ ግድ ይላቸዋል። ሁነቱ በዘላቂነት ልጆችን በተመለከተ ከስምምነት ላይ መድረስ ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሁ ለመመልከት በቤተሰብ አለመግባባት ባለሙያ የሚካሔድ የሽምግልና ሂደት ነው።"
“ገንዘብን አስመልክቶ ሁለቱ ግለሰቦች ያልተግባቡትን ጉዳይ ለመፍታት በቅድሚያ አማራጭ ሙከራን እንዲያደርጉ እናበረታታለን። ፍርድ ቤቶች በአሁኑ ወቅት ተፋቺ ጥንዶች ሙግት ከመግጠማቸው በፊት ቢያንስ አስቀድመው የመደራደር ሙከራን እንዲያደርጉ ይሻሉ" ብለዋል።

According to the Australian Bureau of Statistics, the median age for divorces in 2020 was 45.6 for males and 42.8 for females. The median duration of marriage to divorce was 12.2 years, and almost half of the divorces granted were of couples with children under 18. Credit: fabio formaggio / 500px/Getty Images
ሽምግልናው እንደምን እንደሚሠራ
ወደ ፍርድ ቤት ማምራት ወራቶችንና በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚፈጅ ሲሆን፤ ሽምግልና ከጊዜና ወጪ አኳያ የተሻለ ነው።
የቤተሰብ አለመግባባት መፍትሔ ዕውቅና ያላቸው ባለሙያዋ ቫለሪ ኖርተን፤ 90 ፐርሰንት ያህሉ ተፋቺዎች ለሙግት ፍርድ ቤት ከመቅረብ ይልቅ አለመግባባቶቻቸውን የሚፈቱት ራሳቸው እንደሆኑ ይገልጣሉ።
ወ/ሮ ኖርተን ለሽምግልና ከመቀመጣቸው በፊት የስኬት መጠኑን ይገመግማሉ። በቅድሚያ ተፋቺዎቹ እያንዳንዳቸው ምን እንደሚሰማቸውና የሚገኙበትን ግላዊ ሁኔታዎች አስመልክተው በተናጠል ያናግራሉ።
በግምገማቸው መሠረት የአዕምሮ ሕመም፣ የቤት ውስጥ አመፅ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ወይም የአልኮል ችግሮች ከሌሉ፤ ለቤተሰብ አለመግባባቶች መፍትሔ ሂደት መቀመጥ እንደሚችሉ ከውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።
“ከዚያ በኋላ፣ ከውሳኔ ላይ እደርስና ‘መልካም፣ የተወሰኑ የጋራ ተመሳሳይነቶች አሉ። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከስምምነት ላይ የመድረስ አመቺ ሁኔታዎች አሉ' በማለት አንድ ላይ ተገናኝተን ጉዳዮቹን አንድ በአንድ በማንሳት እንወያይባቸዋለን” ብለዋል።

There are many considerations to balance when you are going through a divorce. Australian state, territory and federal governments fund several emotional, financial and legal support services to assist those going through a separation. Source: Moment RF / Kmatta/Getty Images
'ሽምግልና ማለፊያ ሥፍራን መፈለግ ነው። እንከን የለሽ አይደለም፤ በሁለቱም ወገን ሰጥቶ መቀበል ይኖራል። ሆኖም መቋቋም ይቻላል። ሁለቱም ያን መቀበል ይችላሉ። ሁለቱም ፍትሕዊ ውጤት ነው የሚል ስሜት ሲያድርባቸው ያ ማለፊያ ሽምግልና ነው'ቫለሪ ኖርተን፤ የቤተሰብ አለመግባባት መፍትሔ ባለሙያና የአዕምሮ ጤና ተጠባቢ
ተጨማሪ ያድምጡ

አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን ለፍቺ መብቃት ይቻላል?
የንብረትና ገንዘብ ክፍፍል ስምምነቶች
አውስትራሊያ 'በደል ማሳያ የለሽ ፍቺ' አላት። ይህም ማለት ከባለ ትዳሮቹ አንዳቸው ያለ ሌላኛው ፈቃድ ለፍቺ ማመልከት ይችላል / ትችላለች፤ እንዲሁም ትዳርን ለማፍረስ የፈለጉበትን ምክንያት እንዲዘረዝሩ ግድ አይሰኙም።
በተለምዶ እንደሚታመነው ንብረትና ቁሳ ቁሶችን እኩል የመካፈሉ ሁነት የሚሳካ አይደለም።
በዓለም አቀፍ የፍቺ ክፍፍሎሽ ልምድ ያላቸው የሕግ ባለ ሙያዋ ኢሊኖር ላዩ ተፋቺዎች የሕግ ምክር ሊጠይቁና ለተለየ መመዘኛ ሊያመለክቱ እንደሚገባ ሲያሳስቡ፤
“የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ የሚጋሯቸው ምን እንደሆኑ መለየት ይኖርብናል። እርግጥ ነው አውስትራሊያ ውስጥ ብቻ ያለውን ሳይሆን ባሕር ማዶ ያለውንም ጭምር።
“ግምገማ በምናደርግበት ወቅት ከግምት ውስጥ የምናስገባቸው የተለያዩ የአስተዋፅዖ ዓይነቶች አሉ። የገንዘብ፣ ገንዘብ ነክ ያልሆኑና እንዲሁም የቤት ውስጥ ሥራና የወላጅነት አስተዋፅዖዎችን እናካትታለን” ብለዋል።

The Australian legal system considers a number of variables to determine how property and assets are to be divided between separating parties. Source: Moment RF / boonchai wedmakawand/Getty Images
“አንዳችሁ አንድ ሚሊየን ዶላር ለኑሯቸሁ አምጥታችሁ ሌላኛው ዕዳ ይዞ መጥቶ ከሆነ፤ በምትለያዩበት ወቅት ያ ከግምት ውስጥ ይገባል። ሁለተኛው ነገር በጋራ ኑሮአችሁ ወቅት ያበረከታችሁት ገንዘብና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ አስተዋፅዖዎችቻሁ ናቸው” ይላሉ።
እኒህ አስተዋፅዖዎች ከእያንዳንዱ ባለ ትዳሮች ደመወዝ ባሻገርም ይሔዳል።
“በሥራ ገበታ ላይ የምን ያህል ገንዘብ ተከፋይ መሆንዎ አይደለም። ስለምን፤ የቤት ውስጥ ወላጅ ግምት ውስጥ የሚገባው አንድ ሚሊየን ዶላር በዓመት ከሚያገኝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እኩል ነውና። በአብዛኛው፤ ወላጆች ቤት እንዲገዙ ገንዘብ ሰጥተዎታልን? ወይም ለቤት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለመቆጠብ ከእነርሱ ጋር ኖረዋልን? ውርስ አግኝተዋል? እንዲህ ያሉ ነገሮች"
ተጨማሪ ያንብቡ

የአዕምሮ ጤና ሕክምናን ማግኘት
"ሶስተኛው በንብረት ክፍፍል ወቅት ግምት ውስጥ የሚገባው የእያንዳንዱ ተፋቺ ለወደፊት የሚያስፈልጉት ነገሮች ናቸው። ይህ ትንተና የእያንዳንዱን ተፋቺ ዕድሜ፣ የገቢ አቅም፣ ጠቅላላ የጤና ሁኔታ ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተያይዘው የንብረት ክፍፍሉ በምን ያህል ፐርሰንት ሊሆን እንደሚገባ የሚያስወስኑ ይሆናሉ።
“ይህ ማለት ምንድነው፤ በእዚህ ሁኔታ ውስጥ አንደኛውን ተፋቺ ወደፊት ለመራመድ በመጠኑ ከፍ ያለ ድርሻ እንዲኖረው ግድ የሚሉ ምክንያቶች ይኖራሉ?” በማለት ወ/ሮ ላዩ ያስረዳሉ።
“አንዱ የተለመደ ሁነት፤ አንደኛው ተፋች ከትዳር ተለይቶ በዋነኛ የልጆች አሳዳጊነት የተናጠል ኑሮውን መምራት በሚሻበት ወቅት ገቢ የማግኘት፣ ሥራ የመሥራት ወይም ወደ ሥራ ዓለም ዳግም ለመሠማራት ወይም ከሌላው ተፋቺ ያነሰ ገቢ እንዲኖረው ግድ ይሰኝ ይሆናል። እኒህ አይነት ምክንያቶች በንብረት ክፍፍሉ ላይ ለልጆች አሳዳጊው ተፋች ሚዛን ሊደፉ ይችላሉ።”
ተፋቺዎች በቤተሰብ ሽምግልና ወቅት የገንዘብ ወይም የወላጅነት ስምምነት ላይ መድረስ ይችላሉ። ጠበቃዎች በአብዛኛው የሂደቱ አካል በመሆን ደምበኞቻቸውን ያማክራሉ ወይም በውይይቱ ወቅት ተካፋይ ይሆናሉ። አንዴ ውል ላይ ከተደረሰ በኋላ የስምምነቱ ሰነዶች ሕጋዊ ሆነው በመዝገብነት ይያዛሉ።

Family Dispute Resolution Practitioners often work together with spouses and their lawyers during mediation to reach an agreement. Experts advise divorcing couples with children to consider their kids' wellbeing and needs during negotiations. Credit: Maskot/Getty Images
የሕግ ምክርና የስሜት መታወክ ድጋፍ
ወ/ሮ ላዩ መለያየት ለሚገጥማቸው ሰዎች የስሜት መታወካቸውን ወደ ጎን ብለው በተቻለ ፍጥነት የሕግ ምክር መጠየቅ በጣሙን እንደሚያሻቸው ልብ ሲያሰኙ፤
“አንዳንዴ ተፋቺዎች ዝግጁ ባለመሆናቸው ሳቢያ ፍቺያቸውን የሚያዘገዩበት ጊዜ አለ። ይሁንና የት ጋ እንደሚቆሙ፣ መብቶችዎና ግዴታዎችዎ ምን እንደሆኑ ማወቁ በጣሙን ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ። ከዚያ በኋላ ምን ማድረግ እንደሚሹ ለማሰቢያ ጊዜዎን መውሰድ ይችላሉ። በተቻለ መጠን ሕጋዊ ምክርን ማግኘቱ በጣሙን ጠቃሚ ነው። በተለይም ባሕር ማዶ ያለ ንብረት ካለ” ይላሉ።
አስገዳጅ የሆነ የገንዘብ ስምምነትን ከትዳር በፊት ወይም አብረው በመኖር ላይ ሳሉ መፈራረም ወደ ፊት መለያየት ሲገጥም የመንፈስ ጭንቀትን ለማቃለል ይጠቅማል። አስገዳጅ የገንዘብ ስምምነት በመጨረሻ ክፍፍል ወቅት ጠቀሜታ ይኖረዋል።

Family Dispute Resolution Practitioners are registered and certified professionals, accredited by the Australian Attorney-General's Office. Source: Moment RF / d3sign/Getty Images
ከፍ ያለ ሃብት የሌላቸውና በግል ጠበቃ ማቆም ወይም ሸምጋዮችን መጠቀም የማይችሉ ሰዎች የሕግ ምክርን ከሕግ እርዳታ ወይም የማኅበረሰብ የሕግ አገልግሎት ማዕከላት ማግኘት ይችላሉ።
እንዲሁም፤ በመንግሥት በመደጎም ለመለያየት ለተዳረጉ ቤተሰቦችን ውስን የሕግ አገልግሎቶችን የሚለግሰውን፣ በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ የሚያሸማግሉና ጥብቅና ከሚቆሙ ጋር በማገናኘት አገልግሎቶችን የሚሰጠውን ን ማነጋገር ይችላሉ።
“እንደ ግንኙነቶች አውስትራሊያ ባሉ አገልግሎት ሰጪዎች አማካይነት በኩል መሔዱ በቀጥታ ወደ ጠበቆች ዘንድ ቢሔዱ ያወጡ የነበረውን ወጪ ይቀንስልዎታል። እናም እርግጥ ነው፤ ወደ ፍርድ ቤት የሚያመራ የሕግ ወጪዎችን ከማውጣት ከዳኑ ሌሎች ነገሮችን ለመከወን የሚያግዝ ተጨማሪ ገንዘብ ይኖርዎታል” ሲሉ የ Relationships Australia ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኒክ ቴቢ ይመክራሉ።
ግንኙነቶች አውስትራሊያ ምንም እንኳ ደንበኞችን ፍርድ ቤት ቆሞ ባይወክልም የመንፈስ መታወክ እገዛንና የምክር አገልግሎችን በፍርድ ቤት ሙግት ላይ ላሉ ቤተሰቦች እንደሚቸር አቶ ቴቢ ሲገልጡ፤
“እኛ ሰጥቶ መቀበልን መሠረቱ ካደረገ አገልግሎት ሰጪ ከፍ ያልን ነን። ፍቺን ብቻ አንመለከትም፤ ማን ምን ሊደርሰው እንደሚገባ መፍትሔ አበጂዎችም ብቻ አይደለንም። መጠነ ሰፊ የሆነ ስሜታዊነትን የተላበሰ ጉዳይ አለ። ያንን የማብሰልሰልና የመወጣት ሁኔታ አለ። ልጆች ያሉበት ከሆነ ምንም እንኳ ትዳራቸው ቢፈርስም በወላጆች መካከል ዘላቂ የሆነ ግንኙነት ይኖራል” ይላሉ።
የሕግና የአዕምሮ ጤና ተጠባቢዎች ልጆች ያለዎት ከሆነ በፍቺ ወቅት ለወደፊት የሚያሻዎትንና ጤንነትን ከግምት ውስጥ ማስገባቱ ጠቃሚ ጉዳይ እንደሆነ ይመክራሉ።
አቶ ቴቢ፤ የግንኙነት ለውጥን መቀበል የማገገሙ ሂደት አካል እንደሆነ ሲያስገነዝቡም፤
“የተወሰኑ ግንኙነቶች እስከመጨረሻው ዘላቂ ሆነው የተመሠረቱ አይደሉም… ሰዎች ወደ ፊት መራመድ ይቻላቸዋል። እንዲሁም፤ ደስተኛና ስኬታማ ሕይወቶችን መመሥረት፤ ምናልባትም አዲስ ግንኙነቶችን መጀመር ይችላሉ።
“ያን በመቀበልና የፍቺን ሐፍረት አሌ በማለት አዘቦታዊ ሂደትን መከወን እንችላለን። ከስሜታዊነት የመወነጃጀል ሂደት ይልቅ ይበልጡኑ ግብር ላይ ሊውሉ ወደሚያሹን ሁነቶች ላይ ማተኮር ያስችለናል” ብለዋል።
ምንጮች
- Learn more about
- The