በአልኮል ሱስ እየተሰቃዩ ያሉ ዘመድ አዝማድዎን እንደምን ማገዝ እንደሚችሉ

Alcoholism is a progressive disease.jpg

Alcoholism is a progressive disease. The disease gets worse if the person remains in active addiction, and vicious cycle takes over — more and more of the substance is required to get the same high.

የአልኮል መጠጥ የአውስትራሊያውያን አንዱ ባሕላዊ አካል ነው፤ በበርካታ ሰዎች ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥም የሚጫወተው ሚና አለ። ከመጠን በላይ አልኮል የሚጠጡ ሰዎች ራሳቸውንና ምናልባትም ሌሎችም ላይ ጉዳትን ሊያደርሱ ይችላሉ። በአልኮል ሱስ የተጠመዱ ዘመድ አዝማድዎን ለመርዳት እንደምን እንደሚችሉ እነሆን።


አንኳሮች
  • የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ በማርች 2022 ለሕትመት ባበቃው ዳታ መሠረት፤ ዕድሜያቸው 18 ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ አራት ሰዎች ውስጥ አንዱ በ2020-21 ከወጣው የልኮል መጠን መመሪያ ያለፈ ይጠጣሉ
  • የአልኮል ሱሰኝነት ከአካላዊና ስሜታዊ የአልኮል ቁራኛነት መላቀቅ አለመቻል ነው
  • ወደ አውስትራሊያ ፈልሰው የመጡ ሰዎች ከመጠን ያለፈ አልኮልን የመጎንጨታቸው ሁኔታ ዝቅ ያለ ነው
  • ዘመድ አዝማዶቻቸው በአልኮል ሱስ ለተጠመዱባቸው የቤተሰብ አባላት ሁነቶቹ አዋኪ ቢሆኑም፤ እርዳታዎች ግና አሉ።
የአልኮ ሱስ በመላ አውስትራሊያ ዘር፣ ዕድሜ፣ የማኅበራዊ ኑሮ ደረጃን ወይም የመኖሪያ ቀዬን ሳይለይ አያሌ ሰዎችን የጎዳ ስር የሰደደ ደዌ ነው።

በአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ማርች 2022 ለሕትመት በበቃው ዳታ መሠረት ዕድሜያቸው 18 ከዚያ በላይ ከሆኑት አራት ሰዎች አንዳቸው (25.8 ፐርሰንት ወይም 5 ሚሊየን ሰዎች) በ2020-21 ከአልኮል መምሪያው መጠን (10 መደበኛ መጠጦች በሳምንት) ያለፈ ጠጥተዋል።

በአውስትራሊያ የጤናና ደኅንነት መካነ ተቋም ዳታ መሠረትም ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅነት ያላቸው ማኅበረሰብ አባላት ከአልኮል በመራቅ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ከሆኑቱ ላቅ ያሉ ናቸው።

የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ከሆነው 19.2 ፐርሰንት ጋር ሲነፃፀሩ፤ ከግማሽ በላይ (53 ፐርሰንት) ያህል ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውጪ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑት አንድም ከአልኮል ሱስ የራቁ አለያም የቀድሞ ተጎንጪዎች ናቸው።


በአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ተያያዥ ምልከታ መሠረት "አውስትራሊያ ውስጥ የተወለዱ ባሕር ማዶ ከተወለዱት በሁለት እጥፍ ያህል የአልኮል መጠጥ መጠን (30.0 ፐርሰንት ለ 17.3 ፐርሰንት)" ባለፈ ጠጪዎች ናቸው።


ከዘመድ አዝማድዎ መካከል አንዳቸው ወደ አልኮል ሱስ እያመሩ መመሆኑን እንደምን መለየት ይችላሉ

ሄለን ጂለስ በአልኮል ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ቤተሰቦችንና ጓደኞችን የሚያግዘው የ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው።

ወደ አልኮል ሱስ እያመሩ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የባሕሪይ ለውጦችን እንደሚያሳዩ ሲያመላክቱ፤

"በቀላሉ ተናዳጅ ወይም ተቆጪ ይሆናሉ። በጣሙን የማይጨበጡና ምስጠረኛ ይሆናሉ። ሞገደኛ ወይም በጣሙን ጭምተኛና ራሳቸውን ያገለሉ ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል።

ቤተሰብና ጓደኞቻቸውም በሱስ የመጠመዳቸውን ምልክቶች ለመረዳት እንደሚቸገሩም አንስተዋል።

ሱሰኛ ጠጪ ሆነው፤ ግና ምንም የተለየ ሁኔታ የማይታባቸው በርካታ ሰዎች አሉ
ሄለን ጊለስ; የአል-ኑን የቤተሰብ ቡድናት አውስትራሊያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ወ/ሮ ጊለስ "በአልኮል ሱሳቸው ሳቢያ ለግብረ አካል ጉዳተኝነት ሊዳረጉ ይገባ የነበርና ሥራቸውን በውል የሚወጡና ጤናማ የሚመስሉ በጣሙን ፕሮፌሽናል የሆኑ አያሌ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን"

"በሥራቸው ዘንድ እንከን የለሽ መሆን ሲችሉ፤ ቤታቸው ገብተው ግና በጣሙን አዋኪ ይሆናሉ። እንዲያ ያለ ለውጥ የሆነ ነገር መዛባቱን አመልካች ነው" ብለዋል።

Having a parent that suffers from alcohol abuse issues may deeply impact a child's development and overall life.jpg
Having a parent that suffers from alcohol abuse issues may deeply impact a child's development and overall life. Credit: Richard Hutchings/Getty Images
ኢሊኖር ኮስቴሎ በመንግሥት የሚደጎመውና የአልኮልና አደንዛዥ ዕፆችን ጉዳት ለመቀነስ አልሞ ያለው የ የማስረጃ ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ሌላው አንድ ዘመድ አዝማድዎ ወደ አልኮል ሱስ እያመራ የመሆኑ ጉልህ ምልክት ቀደም ሲል በጣሙን ጠቃሚ አድርጎ ከሚያዘወትራቸው ተሳትፎዎች ራስን ማራቅ እንደሆነ ያመላክታሉ።

አክለውም፤ አንድን ነገር የማድረግ ፍላጎታቸው መጠን ከበፊቱ ሲቀንስ መመልከት እንደሚቻልም ይናገራሉ።

የአልኮል ሱስ ደረጃዎችና አካላዊ ምልክቶች

የአልኮል ሱስ በአንድ ጀምበር የሚፈጠር አይደለም። ከረጅም ጊዜ የአልኮል አለመጠን ጠጪነት ከፍ እያለ የሚመጣ ነው።

አምስት የአልኮል ሱስ ምዕራፎችን ለይተዋል፤

  1. አዘቦታዊ ያልሆነ ከመጠን በላይ ጠጪነትና አንዳንዴ ወንዶች እስከ አምስት ሴቶች እስከ አራት መለኪያዎች መጠጣት
  2. የመጠጥ መጠንን መጨመር
  3. አዋኪ አጠጣጥ
  4. የአልኮል ጥገኝነት
  5. ሱስ
የአልኮል ጥገኝነት ማለት የአንድን ግለሰብ አዘቦታዊ ክንዋኔ ወርሶ ለአልኮል ቁርኝት መዳረግ ነው። አንድ የአልኮል ሱሰኛ ምንም እንኳ ጎጂነቱን ቢያውቅም የአልኮል አወሳሰዱ ላይ ራሱን መቆጣጠር የሚችል አይሆንም።

ሌሎቹ የአልኮል ጥገኝነት አመላካቾች ለመጠጥ ተገዢነትና ራስን ማግለል ናችው።

ሱስ የአልኮለኝነት የመጨረሻው ደረጃ ነው። እዚያ ደረጃ ላይ ሲደረስ መጠጥን መጎንጨት ለመደሰቻነት መሆኑ ይቀርና የሚጠጣው ለአካላዊና ሥነ ልቦናዊ ፍላጎት ይሆናል።

አልኮሉ ሲበርድም ተፈላጊ ያልሆኑ ሁነቶች ይከሰታሉ፤
  • ከስካር አለመብረድ ጋር ያልተያያዘ ማቅለሽለሽ
  • የሰውነት መንቀጥቀጥ
  • ማላብ
  • ብርቱ ብስጭት
  • የልብ መምታት
  • ዕንቅልፍ የመውሰድ ችግር

አልኮልና የአዕምሮ ጤና

ወ/ሮ ኮስቴሎ በአልኮልና የአዕምሮ ጤና መካከል ያለው ትስስር በጣሙን ተቀራራቢና ውስብስብ መሆኑን ይናገራሉ። በርካታ የእዕምሮ ጤና እክል ያለባቸው ሰዎች አልኮልን የማምለጫ ብልሃት አለያም ራስን ማከሚያ ያደርጉታል።

በአልኮልና አደንዛዥ ዕፅ አላግባብ መጠቀምና የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች መካከል መያያዣ አለ።

የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች ግለሰቦች ከመጠጥ ራሳቸውን እንዳይገቱ ይበልጡኑ አዋኪ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ፤ ከፍ ላለ አዘቦታዊ ጠጪነት፣ ቁርኝትና ተጋላጭነት ይዳርጋሉ።

እንዲሁም፤ አልኮል የአዕምሮ ጤና እውክታዎችን መስፋፋትና ፍጥነትን ከፍ ያደርጋል፤ የዕውክታ ጊዜያትንም ያራዝማል።

ብርቱ አዋኪ ንግግርን እንደምን መነጋገር እንደሚገባ

ከዘመድ አዝማድዎ መካከል አንዱ የአልኮል ችግር እንዳለበት አመኔታ ካለዎት የመጀመሪያ እርምጃዎ የሚሆነው ማናገር ነው።

ይሁንና ጉዳዩ ቀላል አይሆንም፤ ፈጽሞ ሲሉ ሊክዱ ይችላሉና።

ወ/ሮ ጂለስ አልኮለኝነት "የሥነ ልቦና ደዌ ያህል ነው። ግለሰቡ በአልኮል ቁጥጥር ስር ሲወድቅ" እናም ከአልኮል ላለመለየት የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉም ሲያስረዱ፤

"ይዋሻሉ፣ ያታልላሉ፣ ይደልላሉ፤ የሚቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ ... ስለምን ሰውነታቸውን ያን ይሻልና" ይላሉ።

ቤተሰብና ጓደኞች በአልኮል ከተጠመዱ ጋር ከመነጋገራቸው በፊት ሙያዊ መምሪያን ማግኘት ይጠቅማቸዋል።

ወ/ሮ ኮስቴሎ የ ADF ድረገጽ በበርካታ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ሰዎች ምን ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ እንዳለባቸው ለመረዳትና የራሳቸውን ስሜት እንደምን ቃኝተው ዕቅድ ሊነድፉ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ እንዳሉት ያመላክታሉ።

አክለውም፤ የሚከባከባቸው እንዳለና በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች ላይ አመኔታን እንዲያሳድሩ ማድረግ ከቻሉ ግልፅ ሊሆኑልዎት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

"ምን ያህል እንደሚከባከቧቸው ... እርስዎ አብረዋቸው ያሉት በሕይወታቸው ውስጥ ስላሉ ማናቸውም ነገሮች ለመነጋገር እንደሆነ በውል ልብ ማለታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ"

ከልክ ያለፈ አጠጣጥ፣ ንዴትና የቤት ውስጥ አመፅ

በዓለም የጤና ድርጅት መሠረት የንዴተኝነት ባሕሪይ ከልክ ካለፈ አጠጣጥ ጋር በእጅጉ ተቀራራቢ ነው።

ወ/ሮ ኮስቴሎ ማንኛውም የቤተሰብ አባል ለአደጋ ተጋላጭ ከሆነ፤ ደኅንነትን ማስቀደም እንደሚገባ ሲያሳስቡ፤

"ለቤት ውስጥ ጥቃት ወይም ወይም ለማናቸውም ዓይነት አመፅ ሊያጋልጥ የሚችል ሁኔታ [ካለ] እና ... የሚቻልዎት ከሆነ ራስዎን ከሁኔታው ያግልሉ። ወዲያውኑ ሊከስት ለሚችል አደጋ የተጋለጡበት ሁኔታ ላይ ከሆኑ፤ ሁሌም 000 ይደውሉ" ብለዋል።

በሕይወትዎ ውስጥ ጠበኛ ወይም አመፀኛን ሰው ማኖሩ ተቀባይነት ያለው ሁኔታ አይደለም።

ወ/ሮ ኮስቴሎ ግለሰቡ ችግር እንዳለበት የማይቀበልና የሚክድ ዓይነት ከሆነ "ትኩረትን ከራሱ ላይ ዘወር ለማድረግ" ሁኔታዎችን አቅጣጫ ለማስለወጥ ይሞክራል"

"በአብዛኛውም ጣቱን በመጠቆም ከሁኔታው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን በማንሳት ‘ይህ የሆነው ቤቱ በአግባቡ ስላልፀዳ ነው', ‘ይህ የሆነው አንተ/አንቺ ብዙ ገንዘብ ስላጠፋህ/ሽ ነው' ‘ይህ የሆነው በዚህና በዚያ ምክንያት' ነው ይላል" ብለዋል።

Alcohol use disorder can be mild, moderate, or severe.jpg
Alcohol use disorder can be mild, moderate, or severe. Lasting changes in the brain caused by alcohol misuse perpetuate alcohol use disorder and make individuals vulnerable to relapse. Credit: Moment RF / Nuria Camps Curtiada/Getty Images

ተስፋፊ ደዌ

አልኮለኝነት ተስፋፊ ሲሆን፤ ሰዎች በሒደት ለግርታ ያዳረጋሉ።

ወ/ሮ ጂለስ "አንድ የአልኮል ሱሰኛ በየጊዜው የመጠጥ ዋንጫውን ባነሳ ቁጥር እየባሰበት ይሔዳል"

"ራስን መርሳት ይጀምራቸዋል፣ የባሕሪይ ለውጦች ያገኛቸዋል፣ ሥራ ቦታ ላይ ችግር ይገጥማቸዋል፣ የገንዘብ ችግር ይደርስባቸዋል፣ የፍቅር ሕይወት ግንኙነታቸው መታወክ ይጀምራል" ይላሉ።

ለረጅም ጊዜ ከመጠን ባለፈ መጠጣት የአዕምሮ ኬሚስትሪን ያዛባል፣ ከአንድ ነርቭ ሥርዓት ወደ ሌላው መልዕክት የሚያስተላለፍና የወጣቶች የአዕምሮ ዕድገት ላይ ተፅዕኖን ያሳድራል።

"አልኮልን በይበልጥ በጠጡ ቁጥር የሐዘን ስሜት ያሳድርብዎታል፤ ስለምን ተስፋ ያስቆርጥዎታልና ... እንዲሁም በአካልዎ ላይ መተሳሰርን ያስከትላል፤ የልብዎንም ምት ያፈጥናል" በማለት ወ/ሮ ኮስቴሎ ይናገራሉ።

የመጠጥ ሱስ ገና ጅማሮ ላይ ሳለ እርዳታን ማግኘት ውጤትን በማስመር ረገድ ያግዛል። ይሁንና፤ ለአልኮል ሱሰኞች ያለ ሕክምና እርዳታ ከመጠጥ መገታት አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል ወ/ሮ ኮስቴሎ ሲያሳስቡ፤

"ለሱሰኞች ፕሮፌሽናል እርዳታ ተመራጭ ነው። ፕሮፌሽናል እርዳታዎችም አሉ" ብለዋል።


ከ10,000 በላይ እርዳታና አገልግሎት ሰጪዎችን ዝርዝር አካትቶ ይዟል።

"እንዲሁም በርካታ ራስን በራስ መርጃ መረጃዎችንም አካትትቷል። ስለምን ሱሰኞች ምናልባትም ከሌሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ አልሆኑ ይሆናል፤ ሆኖም ለመነሻ ያህል ምን ማድረግ እንደሚችሉ ማየት የሚሿቸው ጥቂት ነገሮች ይኖሩ ይሆናል። እኒህ ድጋፍና አገልግሎቶችን የመሻት የመነሻ ደረጃ መወጣጫ ናቸው" ሲሉም አክለዋል።

እገዛ ለቤተሰቦች

ዘመድ አዝማድን ከልክ ባለፈ የአልኮል መጠጥ ሳቢያ ተለውጦ ማየት አሳማሚና ግርታም ፈጣሪ ሊሆን ይችላል።

ወ/ሮ ኮስቴሎ "እገዛ በማድረግ ዓመታትን ሊያስቆጥሩ ይችላሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ የቤተሰቡንም ደኅንነት ሊያውክ ይችላል"

"በብዙ ስቃይ ውስጥ ላለፈው ቤተሰብዎም ለዚያም ዕውቅናን መቸር ተገቢ ነው" ሲሉ አሳስበዋል።

ወ/ሮ ጂለስ የቤተሰብ አባላት ፕሮፌሽናል እርዳታን ማግኘት፤ ምናልባትም በሱስ የተጠመድን ዘመድ አዝማድም ለመበረታታት ሊያበቃ እንደሚችል ያመላክታሉ።

ይሁንና ምንም እንኳ አዋኪ ቢሆንም በጉዳዩ ተሳታፊ የሚሆኑ ሁሉ የየራሳቸውን ውሳኔ ሊወስኑ እንደሚገባ አጥብቀው ያሳስባሉ።

"ግለሰቡ ሊወስን ያሰበውን ውሳኔ ከመወሰን ለማስለወጥ አይቻልዎትም፤ ይሁንና አዋኪም ቢሆን ቤተሰቦች ከአዋኪ ውሳኔ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ"

"አንዱ በጣሙን አስቸጋሪ ነገር ቢኖር ለእነሱ ልዩ ፍቅር ያለን ሰዎች ሲሰቃዩ ማየት ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ማገገም እንዲችል ለእኛ ተገቢ ነገር ምን እንደሆነ ለይተን ከውሳኔ ላይ መድረስ አለብን" በማለት።

ስልክ ለመደወል ወይም ሊንኮችን ለመጫን፤















Share