በቅርቡ ይፋ እንደሆነው መንግሥታዊ ሪፖርት ምልከታ፤ አመኔታ ማጣት፣ ሐሰተኛ መረጃ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ስለላና ማኅበራዊ ክፍፍሎሽ የአውስትራሊያን ዲሞክራሲ ተጋላጭ አድርገውታል።
የአውስትራሊያ የዲሞክራሲና ተጠያቂነት ተቋም ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ቢል ብራውኒ ሲናገሩ፤
"በመላው ዓለም ዲሞክራሲ የኋልዮሽ ምለሳ ጉዳት ያገኘው መሆኑ እርግጥ ነው። በተለያዩ አገራት የዲሞክራሲ ጥራትና መስፋፋት መለኪያዎች ተሞክሮም ነገሮች የኋልዮሽ መሄዳቸውን ለማረጋገጥ ሞክሯል" ብለዋል።
ይሁንና አቶ ብራውኒ አክለው ሲያስረዱ፤ አውስትራሊያ እንዲህ ካሉቱ የከፉ ለውጦች ተመክታ እንዳለች አመላክተዋል።
ለእዚያም ለታችኛውና የላይኛው ምክር ቤቶች ምርጫ ድምፅ መስጠት ዜጋዊ ግዴታ መሆንና የገለልተኛ ኮሚሽን መኖርን በጠቀሜታነት አንስተዋል።
“እንደማስበው በመላው ዓለም የዲሞክራሲን ጥራት ለማሻሻል ከአውስትራሊያ ሥርዓትና ከአውስትራሊያ የነገሮች አከዋወን የሚቀሰሙ ትምህርቶች ይኖራሉ" ሲሉ ለ SBS Examines ጠቁመዋል።
ይህ ክፍለ ዝግጅት፤ አውስትራሊያ ውስጥ ዲሞክራሲ ምን ይመስላል? አክሎም እያሽቆለቆለ ነውን? ሲል ይጠይቃል።