በሜልበንርን በጋራ መኖሪ ቤቶች በሚኖሩ ዜጎች ላይ ለአምስት ቀናት ተደርጎ የነበረው እገዳ በዛሬው እለት ተጠናቋል ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሲባል በቪክቶሪያ መንግስት የተወሰደው ፈጣን እና ነዋሪዎችን ያላስጠነቀቀ እርምጃ ከመነሻው ጀምሮ በርካቶችን ያስቆጣ ነበር፡፡
“ ምንም እንኳን ምርመራው መደረጉን ባንቃወምም መንግስት የሄደበት መንገድ ግን ሙሉ መብታችንን ያልጠበቀ ነው፡፡ ” ሲሉ ሲሳይ ታደሰ እና ሜሮን አብርሃ ተናግረዋል ፡፡