አንኳሮች
- የዋና ትምህርት ራስን እንዴት ማዳን እንደሚቻል እና የደህንነት ክህሎቶችን መሸፈን አለበት
- ቁልፍ የሚባሉ የዋና ችሎታዎች በልጆች እድሜ የሚወሰኑ ናቸው
- የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዋና እና የውሀ ላይ ደህንነት ፕሮግራሞችን ክልሎች እና ግዛቶች በስፖርት መልክ ትምህርቱን ይሰጣሉ
በአውስትራሊያ በውሃ አካባቢ ማደግ አንደኛው የህይወት ክፍል ነው ፤ ይሁንና የውሀ ውስጥ መስጠም ለታዳጊ ህጻናትን የመቁሰል እና ሞት አደጋን በማድረስ ረገድ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ለመስጠም በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ ሲሆን ፤ በአውስትራሊያም በአማካኝ በአመት 23 ያህል ህጻናት ሲሞቱ ሌሎች 183 ሆስፒታል ይገባሉ ።
ይሁንና ይህን አሳዛኝ አደጋ የውሀ ላይ ደህንነት እና የዋና ትምህርቶችን በመማር መከላከል ይቻላል ።
“ ብዙ ጊዜ የምናስበው ‘ ይህ በእኔ አይሆንም ’ ብለን ነው ። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ ሊኖረን አይገባም ። በማንም ላይ ሊደርስ ይችላል ፤ በተለይም እድሜያቸው ከዜሮ እስከ አምስት አመት ባሉ ህጻናት ላይ ፤ ለጥቂትም ጊዜ ከልጆቻችን ላይ አይናችንን ካነሳን አደጋው ሊከሰት ይችላል ። ” የሚሉት በዌስትሚድ የህጻናት ሆስፒታል የቀዶሀኪም የሆኑት ዶ/ር ስቪ ሳውንዳፓን ናቸው ።
![Caucasian boy jumping from canoe into lake](https://images.sbs.com.au/17/85/6e4398014545a13c7b835b0c5d0e/boy-jumping-from-canoe.jpg?imwidth=1280)
Learning to swim and be safe around water can open the way to a range of outdoors recreation activities Credit: Mike Kemp/Getty Images/Tetra images RF
አውስትራሊያ ውሀ የሚወደድበት አገር ናት ፤ የውሀ ላይ ስፖርቶችን እንወዳለን ፤ የውሀ ዳርቻዎችን እና መዋኛዎችንም እንዲሁ ፤ ባለንበት ጊዜ ሁሉ ሰዎች በውሀ ዙሪያ የልጆቻቸው ደህንነትን እንዲጠብቁ ማሳሰባችንን እርግጠኛ መሆን አለብን ። “ዶ/ር ስቪ ሳውንዳፓን - በዌስትሚድ የህጻናት ሆስፒታል ሀኪም
ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ለመስጠም መቃረብ በራሱ የጤና ችግርን ሊያስከትል ይችላል በማለት የሚያስረዱት ዶ/ር ሳውንዳፓን ናቸው
ከውሀ ስር ለሶስት ደቂቃዎች እና ከዚያ በላይ ከቆዪ ከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት እንድሚደርስ ግልጽ ነው ፤ ነገር ግን ከዚህ ያነሰ ጊዜም በህጻናት ትምህርትን የመቀበል አቅም ላይ አሉታው ተጸኖ ሊኖረው ይችላል ።”
![Mother teaching her son how to swim](https://images.sbs.com.au/1f/30/030dbc7d422a8dbe532c5522ef32/mother-teaching-son-to-swim.jpg?imwidth=1280)
For young children, active supervision means an adult being in the water and within arm’s reach. Source: Moment RF / Yasser Chalid/Getty Images
የውሀ ዋናን ለመማር የተሻለው እድሜ የትኛው ነው ?
የሮያል ህይወት አድን ምርምር እና ፖሊሲ አገር አቀፍ ማናጀር የሆኑት ስቴሲ ፒጅን እንድሚሉት ከሆነ ፤ በውሀ ውስጥ የመስጠም አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ ።
እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑት ህጻናት ፤ ወላጆች በቅርብ ሆነው እንዲከታተሏቸው የሚያስፈልግ ሲሆን ፤ ወላጆችም የ CPR እና የመጀመሪያ ጊዜ አደጋ እርዳታ እውቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ህጻናቱ ወደ ውሀው በቀጥታ እንዳይደርሱ ገደብ ማስቀመጥ እና የውሀ ማለፊያዎችን መሸፍን ያስፈልጋል ።
በየትኛውም እድሜ ላሉ ህጻናት በዋና ትምህርት ወቅት የውሀ ላይ ደህንነት መካተቱን ወላጆች ማረጋገጥ እና መምረጥ ይኖርባቸዋል ።
“ ሰለዚህም ፤ እነዚህን የመሳሰሉትን ማለትም መንሳፈፍን መማር ፤ ከውሀ ስር መግባትን መማር ፤ ራስን አደጋ ላይ ሳይጥሉ ሌላውን እንዴት ማዳን እንደሚቻል እና ለ 000 መደወል ወይም ወደ ህይወት አድኖች መሄድ የሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል ። ”
![Children naturally curious around water](https://images.sbs.com.au/e8/b3/979eb5034877b0f1283a493b5685/boy-pool-fence.jpg?imwidth=1280)
“Anak-anak secara alami penasaran dengan air; namun mereka tidak memahami bahaya yang ditimbulkannya,” kata Dr Soundappan. Source: Moment RF / Isabel Pavia/Getty Images
ወ/ት ፒጅን እንደሚሉትም በሕጻናት እድሜ ውስጥም ሶስት ዋና ዋና ደርጃዎች ያሉ ሲሆን ይህውም 6 ፡12 አና 17 ናቸው ።
በ 12 አመት አንድ ሕጻን በ 50 ሜትር ውስጥ መዋኘት ፤ ለሁለት ደቂቃ ያህል መንሳፈፍ እንዲሁም ልብስን ሳያወልቁ ሌሎችን የማዳን እና ራስን የማዳን ክህሎት ሊኖሩት ይገባል።ስቴሲ ፒጅን የሮያል ህይወት አድን ምርምር እና ፖሊሲ አገር አቀፍ ማናጀር
“ ልጆች የአንደኛ ደርጃ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ እነዚህ ክሎቶችን መጨበጣቸውን እርግጠኞች መሆን አለብን።”
በመላው አውስትራልያ በትምህርት ቤት ያሉ ህጻናት የዋና እና የውሀ ላይ ደህንነት የትምህርት እድልን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው ያገኛሉ ። ወላጆችም ከክልሎች እና ግዛቶች የሚገኙ የስፖርት ቫውቸሮች መኖራቸውን እርግጠኞች መሆን አለባቸው ።
“ እያንዳንዱ ክልል በመጠኑም ቢሆን የሚለይ መመዘኛዎች ያሉት ሲሆን ፤ ሁለቱ ክልሎች የዋና እና የውሀ ላይ ደህንነት ፕሮግራሞች የተለያዮ ቫውቸሮች አሏቸው ።” በማለት ወ/ት ፒጅን ያስረዳሉ ።
![Swim Instructor Working with a Little Girl](https://images.sbs.com.au/cb/02/8bf942ca48c388ae25d3ac4ff9c4/swim-instructor-with-girl.jpg?imwidth=1280)
Parents are encouraged to ensure their children don’t drop out early from swimming classes before reaching minimum competencies for their age. Credit: FatCamera/Getty Images
የወላጆች ድርሻ
ብሬንደን ዋርድ የአውስትራሊያ የዋና አሰልጣኞች እና አስተማሪዎች ማህበር ዋና ሀላፊ ሲሆኑ
ህጻንነት ከስድስት ወር ጊዜ ጀምሮ ከውሀ ጋር ማለማመድ ይቻላል ። አንዳንድ የዋና ትምህርት ቤቶች ከዚያም በቀደመ ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣሉ ። “ አላማው ህጻናት በውሀ ላይ ፍርሀት እንዳይኖራቸው እና ዋናን መማር ሲጀምሩ መሰረታዊ ክህሎትን ቀድሞ በማስጨበጥ ለመማር ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ነው ።”
አቶ ዋርድ እንደሚሉት እድሜያቸው በሶስት እና በአራት መካከል ያሉት አብዛኞቹ ህጻናት መሰረታዊ የሚባሉ ክሂሎችን ማለትም የውሀ ላይ ደህንነት እንዲሁም መዋኘትን ያውቃሉ ። ወላጆችም ልጆቻቸው ደህንነታቸው የተጠበቀ ዋናተኞች እንዲሆኑ ቀጥተኛ የሆነ ሚናን የሚጫወቱ ሲሆን ፤ይህንንም ለማድረግ ህጎችን እና በአደጋ ጊዜ ስለሚወሰድ ጥንቃቄን በመከተል ነው ።
![Asian father and baby at swimming pool, happily clapping](https://images.sbs.com.au/74/74/c72edc3d4da68b2508c78ec254d4/dad-and-bub.jpg?imwidth=1280)
Introducing your toddler to the feel of water can be a special parent-child bonding experience. Source: Moment RF / Navinpeep/Getty Images
አዋቂዎችም ልጆቻቸውን ለመከታተል ክህሎትን በማዳበር በውሀ ላይ ልበ ሙሉ መሆን እጅግ አስፈላጊ ነው ።
አንዳንድ ወላጆች አዋቂ ከሆኑ በኋላ ወደ አውስትራሊያ ሲመጡ በትውልድ አገራቸ የዋና ትምህርትን አልወሰዱ ይሆናል ።
እንደ ዶ/ር ሳውንዳፓን ግምት ከሆነም በውሀ ውስጥ የመስጠም አደጋ ከሚደርስባቸው ከአምስቱ ህጻናት አንዱ ወላጆቻቸው አዲስ መጤ የሆኑ ናቸው ።
እርሳቸውም አዋቂ ከሆኑ በኋላ የዋና ትምህርትን እንደመውሰዳቸው ሁለቱም ወላጆች በልጆቻቸ የዋና ትምህርት ጉዞ ውስጥ ቀደም ብለው መሳተፍ እንዲጀምሩ ያበርታታሉ ።
“ በውሀ ላይ መንሳፈፍን እንድችል የተውሰኑ ስልጠናዎችን ወስጃለሁ ፤ በርካታ አዲስ መጥ የህብረተሰብ ክፍሎች ወላጆቻቸው ዋናን የማይችሉ እንደሆነም ይታመናል ። ”
በአውስትራሊያ እድለኞችም ሆነን ልጆችን ደህንነቱ በተጠበቀ የውሀ አካባቢ ማቆየት እንችላለን፤ ለጨቅላ ህጻናት የሚሆኑ ትምህርቶች አሉ ። ስለሆነም ቀድሞ ማስጀመር ጠቀሜታው ጉልህ ነው ።
![Kids Entering the Pool](https://images.sbs.com.au/a5/d0/7eed04d349b2859aaba0dfcd99e6/kids-entering-pool.jpg?imwidth=1280)
Getting your child used to putting on their swim wear in the days before their first lesson can help them feel comfortable and excited about the upcoming class. Credit: FatCamera/Getty Images
አቶ ዋርድ ዋና ዋና በሚባሉ መመዘኛዎች ላይ የተወሰኑ ምክሮችን ያካፍላሉ
· የዋና ትምህርት ቤቱ የሰለጠኑ ባለሙያዎች አሉት ?
· አስተማሪዎቹ በስራ ልምዳቸው መልካም ስም አላቸውን ?
· የዋና ትምህርት ቤቱ የእርስዎን እሴቶች ያከብራል ?
· የዋና ትምህርት ቤቱ ንጹህ እና የተሰተካከለ ነው ?
· ለመልካም ስራቸው ምስክሮች እና ግምገማዎች አለ ?
ከክልሎች እና ግዛቶች የሚገኙ የዋና / የስፖርት ቫውቸሮች
Voucher Schemes for swimming/sports across states and territories
NSW
NT
QLD
SA
TAS
VIC
WA