ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርጫ፤ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እንደምን የዓለም ግዙፉ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ

Factchequado.png

This TikTok account uses an avatar to spread misinformation about US immigration issues in Spanish. Credit: Source: Factchequeado

ባለፈው ዓመት ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና አሳስች መረጃ ከ "ኮሙኒስት ካማላ" እስከ ቦሊውድ ድጋፎች በተወሰነ መልኩ በግዙፉ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ አጭር ፅሑፎች፣ ቪዲዮዎች፣ ምስሎችና ኦዲዮዎች የፖለቲካ ምርጫ ዘመቻዎች ላይ ሰርገው ገብተዋል።

ሕንድ ውስጥ፤ ሐሰተኛውን ከእውነተኛው ለመለየት በሚያውክ መልኩ የቦሊውድ ተዋናዮች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፋቸውን ሲሰጡ በድምፅ ሰጪዎች የማኅበራዊ አቅርቦቶች ውስጥ ተከስተዋል።

በርቅቀታቸው ሳቢያ ሐሰተኛውን ከእውነተኛ ምስሎች፣ ኦዲዮዎች፣ ቪዲዮዎችና አጭር ፅሑፎች መለየት አዋኪ መሆንን አስመልክተው የዘርፉ ተንታኝ ፓምፖሽ ሪያና "ኦዲዮቻቸው እውነተኛ ምስሎች፣ ኦዲዮዎች፣ ቪዲዮዎችና አጭር ፅሑፎችን ለውጠው ቀርበዋል፣ በተወሰነ መልኩም በእውነተኛዎቹ ቪዲዮዎች ላይ ያሉት ፍፁም ተቀይረው በትክክል አንዱን ፓርቲ ለይተው ድጋፋቸውን የቸሩ መስለው ቀርበዋል፤ እውነታው እንዲያ ባይሆንም እንኳ" በማለት አመላክተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካማላ ሃሪስ እንደ አንድ የሶቪየት መኮንን ለብሰው የሚያሳይ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተፈበረከ ምስል በተለይም በላቲን አሜሪካውያን መራጮች ዘንድ በሰፊው ተሰራጭቷል።

አና ማሪያ ካራኖ፤ "ሁነቱ ከላቲን አሜሪካ የመጡ በርካታ ስፓኒሽ ተናጋሪ ማኅበረሰባት ዘንድ ከአምባገነን መንግሥታት ጋር የነበራቸው ግንኙነት በጣሙን የተለየ ነውና እንዲያ ያለ ቁርኝትን አሌ የሚል የተለየ ልምድ አለ" ብለዋል። ።

በእዚህ ክፍለ ዝግጅት፤ SBS Examines በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ አሳሳች መረጃዎች እንደምን ተፅዕኖዎችን እንዳደርሱ ለመመልከት ፊቱን ወደ ሕንድና ዩናይትድ ስቴትስ አዙሯል።

Share