አንኳሮች
- አውስትራሊያ ውስጥ ለተወሰኑ ነገሮች ሕጋዊ ዕድሜ 18 ቢሆንም፤ በክፍለ አገራትና ክፍለ ግዛቶች የዕድሜ መብቶችና ኃላፊነቶች የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ።
- የማኅበራዊ ደኅንነት ክፍያዎች ብቁነት ለወጣቶችና ቤተሰቦቻቸው 18 ዓመት ላይ ይለወጣል።
- ነፃ ሆኖና ራስን ችሎ መኖርን አካትቶ በሕይወት ውስጥ ለስኬት መብቃት የሚቻለው አዝጋሚ በሆነ የጉልምስና ሽግግር ነው
ከሕግ አኳያ ዕድሜያቸው 18 ለሞላ ወጣቶች ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ወላጃዊ ኃላፊነት አይኖርባቸውም።
ኬት ሪችድሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ነፃ የሕግ መረጃ አገልግሎት ለኦንላይን ማኅበረሰብ የሚሰጠውና ዕድሜያቸው ከ25 በታች ለሆኑ ወጣቶች እገዛ የሚያደርገው የወጣቶች ሕግ አውስትራሊያ ገዲብ የሕግ ባለሙያ ናቸው።
ከሕግ አኳያ አንድ ጎልማሳ ሰው እንደምን እንደሚፈረጅ ያስረዳሉ።
እንደ አንድ ጎልማሳ፤ እርስዎ ራስዎን የቻሉ ነዎት። ያም ማለት ለራስዎና ለባሕሪይዎ ኃላፊነቱ የእርስዎ ይሆናል ማለት ነው። ከ18 ዓመት በታች ሳሉ በተወሰነ መልኩ የልጅነት ወይም የወጣትነት ብቁነት ከሕግ አኳያ ዝቅ የሚሉባቸው ሁኔታዎች አሉ።ኬት ሪቻርድሰን፤ የወጣቶች ሕግ አውስትራሊያ ገዲብ የሕግ ባለሙያ
ሕጋዊ ዕድሜና ጎልማሳ መሆን
በመላው አውስትራሊያ 18 ዓመት ሲሞላ በምርጫ ወቅት ድምፅ መስጠት ግዴታ ነው። ይህ ዕድሜ ቁማር የመጫወት፣ ሲጋራዎችን የመግዛትና ፈቃድ ካላቸው ሥፍራዎች አልኮል የመግዛት ወይም የመጠጣት ህጋዊ ዕድሜም ጭምር ነው።

Cultural and family practices may vary, but generally in Australia the 18th birthday makes the list of milestone celebrations, followed by one’s 21st and 30th. Credit: Getty Images/BFG Images
ወ/ሮ ሪቻርድሰን አክለውም “አልኮል በወላጅ ወይም በአሳዳጊ ካልተሰጠ፤ በወላጅ ወይም በአሳዳጊ ፈቃድ ከተሰጠው በስተቀር።
“በክፍለ አገራትና ክፍለ ግዛቶች ዘንድ በተለይ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በአዋቂዎች ተቆጣጣሪነት መጠጥ መጠጣትን አስመልክቶ አነስተኛ የሆኑ ልዩነቶች አሉ” ብለዋል።
ስቲቨን ሮበርትስ በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ማኅበራዊ ፍትሕ ፕሮፌሰር ናቸው። ከተጠበቡባቸው የምርምር መስኮች አንዱ የወጣቶች ወደ ጉልምስና ሽግግር ነው።
መጠጥ የመጠጣትን ኃላፊነት ጨምሮ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሚደግፉባቸው መንገዶች አንዱ ስለሆነው የዕድሜ ሽግግር መልካም የሚሏቸውን የትግበራ ተምሳሌቶች አስመልክተው አተያያቸውን ያጋራሉ።
“ምናልባትም ልጆቻቸው በጓደኛ ቡድናቸው ውስጥ አንዳቸው አንዳቸውን የመርጃ መንገዶች በማፈላለግ በቡድናቸው ውስጥ መከባበርንና መከባከብን እንዲያዳብሩ ሊያነጋግሯቸው ይሹ ይሆናል። በእዚህ ጠቃሚ መገናኛ ላይ ልየታ፣ መረዳትና ተግባቦት ወሳኝ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ።”
የሴንተርሊንክ ክፍያ በ18 ዓመት ዕድሜ
ለጎልማሳነት የበቃ ልጅ ቤተሰቡ ያገኝ በነበረው የማኅበራዊ ደኅንነት ትሩፋቶች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል።
ሃንክ ጆንገን የአውስትራሊያ አገልግሎቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ ልጆችን ለማሳደግ የወላጆችን ወጪ በሁለት ክፍሎች ስለሚደጉመው ያስረዳሉ።
ክፍል ሀ ለእያንዳንዱ ልጅ 12ኛ ክፍልን ሲጨርስ ወይም ተመጣጣኝ ደረጃ ያለውን ትምህርት ሲያጠናቅቅ የሚቆም ክፍያ ሲሆን፤ ክፍል ለ በቤተሰብ የሚከፈል ክፍያ ነው።
“እንደ እውነቱ ከሆነ የክፍል ሀ እና ክፍል ለ ክፍያ ቀጣይነት እንደ ቤተሰቡ ሁኔታ የሚወሰን ሲሆን፤ ግምገማው የሚካሔደው በተናጠል ነው” ይላሉ አቶ ጆንገን።

Meeting an income test is among requirements to get the Family Tax Benefit. Credit: Getty Images/Traceydee Photography
ይሁንና የክፍያ ብቁነትን አስመልክቶ በሚደረግ ግምገማ ወቅት እንደ ጥገኛ ተወስደው ሊታዩ እንደሚችሉም አቶ ጆንገን ያስረዳሉ..
እንደ ሙሉ ጊዜ ተማሪ ወይም ሥራ ፈላጊ ዕድሜያቸው 22 እስኪሞላ ድረስ በጥገኝነት ይታያሉ። ያም ምን ማለት ነው ስለ ብቁነታቸው የወላጆቻቸውን ገቢ ግምገማ ውስጥ እናካትታለን።ሃንክ ጆርገን፤ የአገልግሎቶች አውስትራሊያ ዋና ሥራ አስኪያጅ
አቶ ጆርገን ዕድሜያቸው 18 የደረሱ ወጣቶች እንዲከፍቱና መረጃውንም በመጠቀም በኦንላይን ማመልከቻዎቻቸውን እንዲያስገቡ ያበረታታሉ።
“እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋችሁ ከሆነና እርዳታን የምትሹ ከሆነ በ 131 202 ልትደውሉልን ትችላላችሁ። ከ200 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የነፃ አስተርጓሚ አገልግሎት ያለው ነው።"

Young people aged 16 to 24 doinga full time Australian Apprenticeship may be eligible for Youth Allowance. Credit: Getty Images/JohnnyGreig
ወደ ጉልምስና የሚደረግ ጉዞ አዝጋሚ ነው
አውስትራሊያ ውስጥ አንድ ትንሽ ልጅ አድጎ 18 ዓመት ሲሞላው ለጉልምስና ይበቃል። ከክፍለ አገር ክፍለ አገር ቢለያይም ለተወሰኑ ነገሮች ሕጋዊ ዕድሜ ነው። መኪና መንዳት ለመጀመር ከዚያ ያንሳል።
ፕሮፌሰር ሮበርትስ ቀደም ብሎ ለመብቶችና ግዴታዎች መብቃት የጉልምስና ሽግግሩን አዝጋሚና አንዳንዴም ውስብስብ እንደሚያደርገው ይናገራሉ።
“ለምሳሌ፤ የ16 ዓመት ወጣቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ወሲብ መፈፅም ይችላሉ፤ ይሁንና 18 ዓመት ዕድሜ እስከሚሞላቸው ድረስ ግልፅ ወሲብን ያካተቱ ፊልሞችን መመልከት አፈቀድላቸውም። እንዲሁም፤ 18 ዓመት የሞላቸው ወጣቶች ዕድሜያቸው 16 እና 17 በነበረበት ወቅት ያገኙ ከነበረው ደመወዝ ከፍ ያለ ክፍያ የማግኘት መብት ቢኖራቸውም ሙሉ የጎልማሳ ደመወዝ ክፍያ ማግኘት የሚችሉት ግና 21 ዓመት ሲሞላቸው ነው።”
ፕሮፌሰር ሮበርትስ አያይዘውም፤ ባለፉት ትውልዶች ማኅበራዊ ተፅዕኖ አሳዳሪዎች ዘንድ የተለመደው የሙሉ ጊዜ ሥራ፣ ራስን ችሎ ወይም የራስ ቤተሰብን መሥርቶ መኖር የሚለው አሁን 18 ዓመት በሞላቸው ወጣቶች ዘንድ ቅቡልነቱ ዝቅ ያለ እንደሆነ ያመላክታሉ።
በማኅበራዊ ተፅዕኖ አሳዳሪዎች ዘንድ ጉልምስና ላይ በ20ዎቹ ወይም በ30ዎቹ መድረስ የተለመደ አተያይ ሆኗል።ስቲቨን ሮበርትስ፤ በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ማኅበራዊ ፍትሕ ፕሮፌሰር
ከሕግ አኳያ 18 ዓመት ላይ መድረስ ማለት የተወሰኑ ነገሮችን ለመከወን ሁሌም አስፈላጊ አይደለም።

Prof Roberts says there are growing numbers of young people who not only delay the attainment of social markers, like getting married, but reject them altogether. Credit: Getty Images/FatCamera
“እኒህን ለመፈፀም የ18 ዕድሜ ላይ መድረስን ግድ አይልም…
- ወሲብ መፈጸም
- ሥራ መሥራት
- የራስ የባንክ አካውንት መክፈት
- ትምህርት ለማቋረጥ
- ቤትን ለቅቆ ለመውጣት
- በወንጀል ለመከሰስ
- ያለ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የሕግ ምክርን ለማግኘት
- ለሕክምና ፈቃደኝነትን ለመግለጥ”
“ለምሳሌ፤ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ሐኪሙ የሕክምናውን ትሩፋቶችና ጎጂነቶች ተረድተው ከውሳኔ ላይ መድረስ ይችላሉ ብሎ ካሰበ በሕክምናው ለመቀጠል ፈቃደኝነታቸውን ለመስጠት ይችላሉ። ሐኪሙ እዚያ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባል” ሲሉም ሪችድሰን ይናገራሉ።
ለተለየ ሁኔታ ሕጋዊ ዕድሜን አስመልክቶ ይህ ነው የሚል ድንጋጌ በሚያሻዎ ወቅት ሁሌም ከእርስዎና ከልጅዎ ሁኔታዎች አኳያ ተገቢ ነው ተብሎ የሚመከረውን ማጣራቱ ይመከራል።
እርዳታን የሚሹ ወጣት ወይም ወላጅ ነዎት?
- የወጣት ጎልማሶችን መብቶች አስመልክቶ አጋዥ መረጃዎችን በ
- የተወሰኑ ክፍለ አገራት በተለይ ለወጣቶች የሕግ አገልግሎቶች አሏቸው , እና ን ጨምሮ።
- ሕጋዊ ችግሮችንና ለወጣቶች ምክርን በተመለከተ ድረ ገጽን ይጎብኙ።
- በልጆች ላይ ሕግ እንደምን እንደሚፈፀምና በአውስትራሊያ መንግሥት ከሚደጎመው የኦንላይን የወላጆች መረጃ ምንጮችን እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ለሚሹ ወላጆች .
- ዕድሚያቸው ከ 5 – 25 ሆኖ ነፃ የስልክና የኦንላይን ምክር አገልግሎት ለሚሹ በ 1800 55 1800 መደውል ይችላሉ።